>
5:21 pm - Monday July 20, 9446

የመለስና የልጁ የአቢይ ልዩነትና አንድነት ባጭሩ (አምባቸው ደጀኔ)

የመለስና የልጁ የአቢይ ልዩነትና አንድነት ባጭሩ

አምባቸው ደጀኔ


አሁን ጥቂት ዘና እንበል፡፡ የሚስያስጨንቅ ወሬ ዛሬ አልናገርም፡፡ ምክንያቱም ፈታ ብለን ይህችን ቀን ማሳለፍ አለብን ብዬ ስለማምን፡፡ ሰሞኑን አእምሮን የሚወጣጥሩ ብዙ ነገሮች ነበሩን፡፡ አሁን ለጊዜው እነሱን እንርሳቸው፡፡

እንጂ ማስጨነቅማ ብፈልግ ኖሮ በስድስቱም አቅጣጫ የተወደረብንን ቀስትና ፍላጻ በማነሳሳት አዳሜን ማስፈራራት አቅቶኝ አልነበረም፡፡ አቢይ በውስጥ መስመር ጃዝ የሚላቸው አክራሪ ወረሞች ማኅጸን ውስጥ ካለው ጽንስና ሽል ጀምሮ አማራውን ስሊ ስሊውን እየቀነጠሱ ኢትዮጵያን በንጹሓን ደም እያጨቀዩ መሆናቸውን መደበቅ አያስፈልገኝም ነበር፡፡ ግብጽና ወያኔ፣ ግብጽና አክራሪ ኦሮሞ፣ ግብጽና ምዕራባውያን … ሁሉም የአጋንንት ጭፍራ እየተናበበ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከዚህ ዘመንና ከዚህች የታሪክ አንጓ የበለጠ ምቹ አጋጣሚ አላገኝም ብሎ ያወጀውን ጦርነት መዘክዘክ ባልተሳነኝ ነበር፡፡ ያ ደደብ ሰውዬ እንኳን ሰሞኑን ስለግድቡ የተናገረውን አወሳ ነበር፡፡ ግን ይቅር፡፡ ስሙን ቄስ ይጥራውና ግብጽ ግድቡን ማፈንዳት እንዳለባት በሾርኒ ሳይሆን በግልጽ ያዘዘውን ዘገምተኛ ፈረንጅ በተመለከተ ምንም አልናገርም፡፡ በዚያ ሰሞን በጉራፈርዳ ስንትና ስንት አማራ ሲታረድ የአቢይ ዞምቤ የሆነው ብአዴን ከአቢይ ጋር በዕልቂቱ ሳቢያ በደስታ ሰክሮ ብርጭቆ ሲያጋጭ መክረሙን መናገር አቅቶኝ አይደለም፡፡ ከወያኔና ኦህዲድ ይልቅ ትልቅ የመከራ ድግስ የሚጠብቀው፣ አማራን እጅ እግሩን አስሮ ለጠላቶቹ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳው ብአዴን አማራ በሰልፍ ወጥቶ አትግደሉኝ ብሎ እንኳ እንዳይጮህ መከልከሉን መናገር ፈርቼ እንዳይመስልህ፡፡ ወደዚያ አልገባም ብዬ እንጂ፡፡

መለስ ዜናዊና አቢይ አህመድ ዘረኞች ናቸው፡፡ ቆይ ቆይ – ከትውልዳቸው ልጀምር፡፡ መለስ ዜናዊ ጎጃሜና ትግሬ እንዲሁም ኤርትሬ ነው፡፡ በዘር ሐረጉ አማራ አለበት፡፡ ግን ዋና አማራ ጠል ነው፡፡ የባንዳ ልጅ ነው – አማራ የመጥላቱ ምሥጢርም ባንዳነቱ ነው፡፡ ብዙ አማሮች በባንዶች ጥቃት ተሰውተዋል፡፡ ባንዶች የመንግሥትን ሥልጣን ይዘው እንደተፈጸመባቸው ያለ ቅጣት ግን ከዚህ ዘመን ውጪ አልተፈጸመባቸውም፡፡ የመለስ ሚስት አማራ ናት፡፡ የመለስ ልጆች አማራና ትግሬ ናቸው፡፡ “ቤተ ክርስቲያንን የሚደፍራት የሚያውቃት ነው” የሚባለው እውነት ነው፡፡ ብዙ የሚያውቅህ አጥቂህ እርሱ ነው – ይህም እውነት ነው፡፡ 

አቢይ ትውልዱ አማራና ኦሮሞ ነው ይባላል፡፡ ሚስቱ አማራ ናት፡፡ ልጆቹ አማራና ኦሮሞ ናቸው፡፡ አቢይ በአንደበቱም በምግባሩም አማራ ጠል ነው (በጀታችሁን ለልዩ ኃይል ሥልጠና ታውላላችሁ ብሎ ደሴ ላይ በተናገረበት ቅጽበት ኦሮሚያ ውስጥ በብዙ ሽዎች የሚገመት ወታደር እየሰለጠነ እንደነበር አቢይ ሳያውቅ ቀርቶ ከመሰለህ ያዞረብህን አፍዝ አደንግዝ በጊዜ አስፈታ፤ 650 ወታደራዊ ተሸከርካሪ ለኦሮሚያ ሲሰጥ አቢይ አያውቅም ካልክ ጤንነትህን እጠራጠራለሁ…)፡፡ ይህ በሽታ ነው፤ ከግለሰብ ባለፈ አንድን ዘር ለይቶ መጥላት ህክምና የሌለው የበሽታዎች ሁሉ ንጉሥ ነው፡፡ በሽታ ደግሞ መልኩ ብዙ ነው፡፡ አንዳንድ ጅሎች “አማራ ሆኖ እንዴት አማራን ይጠላል?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ገነት ዘውዴ አማራ ሆና በመለስ ፍቅር ታለቅስ የነበረው መለስ የአማራን ጭፍጨፋ እንደሚመራ ሳታውቅ ቀርታ ወይም ውሽማዋ ሆኖ ሳይሆን (ይህንንስ አታስዋሹኝ አላውቅም) ብልሹ ጠባይዋ ከልሎባት ነው – ዥሌ!  ሆዳሙና አማራው ክፍሌ ወዳጆ ከርሱ(ሆዱ) አይጉደልበት እንጂ ከጸረ አማራው መለስ ጋር ሣምባና ሳልሳ ከመደነስም አልፎ በታኙን ህገ መንግሥት ተብዬ አርቅቆላቸዋል፡፡ ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ በወያኔ ፍቅር አብዶ በሀገረ እንግሊዝ በሚገኝ አማኑኤል ሆስፒታል መግባቱን በወቅቱ ሰምተናል፡፡ ስለዚህ አማራ ሆኖ አማራን አሳልፎ መስጠት የነበረ፣ ያለና የሚኖርም ነው – አንድ ሰው ራሱን የሚሰቅለው እኮ ራሱን ጠልቶ ነው፤ አይደለም እንዴ? የራስ የሆነን መክዳትና ለሞትና ለመከራ አሳልፎ መስጠት በይሁዳ አልተጀመረም፡፡ ከዚያም በፊትና አሁንም ድረስ በርትቶ ቀጥሏል፡፡ መካካድ የሚጠፋው ምናልባት አቶ ሆድ ሲጠፋ ነው፡፡ ብአዴን የአማራን ክልል በቁም እንጦርጦስ ዱሎ ይሄውና በሥጋዊ ድሎት ይምነሸነሽ የለምን? የክህደት መጨረሻ፡፡

መለስ በይልበጥ ክፉ የነበረው በንግግሩ ነው፡፡ ንግግሩ መርዝ ነበር፡፡ ስድቡ ኃይለኛ ነበር፡፡ ሰማይንና ምድርን የተቆጣጠረ ይመስለው ስለነበር ለአንደበቱ ልጓም አልነበረውም – ልክ እንደ ዶናልድ ኢዲየት ትራምፕ፡፡ ሲፈልግ “አማራ ቁጭ ብሎ ሲለምን ማየት እፈልጋለሁ” ይልሃል፤ ሲሻው “የአማራ ተረትና የሶማሌ በጀት በጠበጠኝ” ይልልሃል፡፡ ማታ ግን አማራ ሚስቱን አቅፎ ይተኛል – ሊያውም ተራው የርሱ ከሆነ፡፡ (ባለቤቴ ጉዝጉዝ እንዳትሰማኝ እንጂ አዜብ የቀረኋት እኔ ብቻ እንደሆንኩ በሠፈሬ ሲወራ እንደነበር የቅርብ ሰው ነግሮኛል – ቱ! ታዘብኳቸው፤ ባልጠፋ ሰው ከርሷ ጋር ሲያሙኝ ተናደድኩ፡፡)

አቢይ እስካሁን ባለው ሁኔታ እዚህና እዚያ የሚናገረው የሚጣረስና በውሸቱ ወደር የሌለው ይሁን እንጂ እንደመለስ ያን ያህል ክፍት አፍ አይደለም – ወይም ጊዜው ገና በመሆኑ ልቅ አፍነቱ ገና ጎልቶ አልወጣ ይሆናል – ምልክቱ ግን በተለይ አሁን አሁን እየታዬ ነው – ወንበሩ ጠበል ካልተረጨ ያባልጋል፡፡ አቢይ በንግግሩ እያቀለጠህ በተግባሩ ግን ያሻውን ይሠራል፡፡ ለንግግሩ ሲሆን ለነሽመልስ ያስረክባል፡፡ ማታ ታዲያ “አካሲ ኢጆሌ ኪያ ኦቦ ሽሜ፣ ሊኪ ሊኪ ጀቹን ናፍጣኞቲ … ውይ … በወሮምኛው ነካሁት አይደል እንዴ … ልመልሰው… ሽሜ የትግል ጓዴ… ሽሜ የኔ የኦሮሙማ ቅንጡ… አፌ ቁርጥ ይበልልህ … ነፍጠኞችን ልክ ልካቸውን ስለነገርካቸው በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ እንዲህ ነው ትግል ማለት! የፈለግኸውን እስከዶቃ ማሰሪያቸው ንገራቸው፡፡ ምናባታቸው ያመጣሉ… እንደለመዱት ተንጫጭተው ይተውታል፤ ለምደውታልም፡፡ ዋና ዋናዎቻቸውን ደግሞ አሥረናል፤ ብቅ ብቅ ካሉም እናስራቸዋለን፡፡ ሁሉም የኛ፤ ማንን ፈርተን? በርታ! እኔም ድራማውን እቀጥላለሁ፤ እናንተ ዕቅዶቻችንን በተግባር አውሉ…”

መለስ በንግግርም በተግባርም ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት ያህል አፈረሰ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ደግሞ እጅግ ጥበበኛ ነውና የዘራውን ፍሬ አሽቶና ተወቅቶ ሳይበላው መስክ ላይ እያዬ በጊዜ በጣጥሶ ወሰደው፡፡  ከርሱ ሞት የውሻ ሞት ይሻላል፤ ሥራው የማያምር ሞቱም እንደማያምር ፈጣሪ በመለስ አሳየን፡፡ ካሁኖቹ ደግሞ የርሱ አሟሟት የተሻለ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ዕንባቸውም ጦር ነው፤ ጀግንነታውም ወቅትን ጠብቆና አምላክን ይዞ ነው፡፡ በሚሸነፉበት ጦርነት አይገቡም፡፡ ነፃነት ቀርባለች! ሃሌ ሉያ፡፡… 

መለስ በማስመሰል ብዙም አይታወቅም፡፡ በውሸታምነት ግን ከልጁ አቢይ ብዙም አይተናነስም፡፡ አቢይ መልከ መልካም ነው፤ መለስ ግን እስከዚህም ነው፡፡ አቢይ ልቅሶ ቤት ከመሄድ ይልቅ ሠርግ ቤት መሄድን ይወዳል – ጭንቅ አይወድም፡፡ መለስ ግን ከቤቱ መውጣትን አይፈልግም፡፡ ከዚያ ይልቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ማደርንም ቢሆን ይመርጣል – በተለይ የአሰቦትና የገለምሶ ዛፍ፡፡ ሁለቱም ፈሪዎች ናቸው፡፡ ፈሪ የሚታወቀው በመግደልና በማሰር ነው፡፡ ጀግና መሐሪ ነው፤ ታጋሽ ነው፡፡ የለየለት ጠላቱን ሣይቀር አስተምሮና ገስፆ ለሥልጣንና ለኃላፊነት ያበቃል፡፡ እነመለስ ግን በሥልጣናቸው የመጣ የመሰላቸውን አይታገሱትም፤ ድራሹን ነው የሚያጠፉት፡፡ የፍርሀታቸው ምንጭም ሥልጣን ወዳድነታቸው ነው፡፡ ሥልጣንን ከምንም በላይ ይወዳሉ፤ የሚዋሹት፣ የሚቀጥፉት፣ የሚያስሩ የሚገድሉት … ያቺን መከረኛ ሥልጣን ለማስጠበቅ ነው – የሚገርመው ማርጀትን፣ መታመምን፣ ከዚህች ዓለም ማለፍን ጥንቅር አድርገው ይረሳሉ፤ ዘላለማዊ የሆኑ ያህል ይሰማቸዋል፤ በፍቅረ ንዋይና በፍቅረ ሥልጣን የነደደ ሰው ዋና ምልክቱ ደግሞ ይህ ነው፡፡ ሁለቱም የሀገር ፍቅር የላቸውም፡፡ ሥልጣናቸው ከሀገርም፣ ከትዳርም፣ ከጓደኛም፣ ከሰውም በላይ ነው፡፡ ለዚያ ሲሟሟቱ ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርገው ይተዋሉ፤ ያኔ ሀገርና ሕዝብ የት እንዳሉ እንኳን አያውቁም፤ ይረሷቸዋል፡፡ እነአጅሬ እንዲህ ናቸው፤ በቃኝ፡፡ 

Filed in: Amharic