>

ለተላላኪው አዴፓ/ብአዴን ከአንድ እናት የቀረበ ጥያቄ !? (መምህርት መስከረም አበራ)

ለተላላኪው አዴፓ/ብአዴን ከአንድ እናት የቀረበ ጥያቄ !?

መምህርት መስከረም አበራ

ብአዴኖች “ወደዚህ ዓለም የመጣንበትን ዓላማ፣ የተላላኪነታችንን እናሳልጥበት ሰላማዊ ሰልፍ ምናምን እያላችሁ አታናጥቡን” ብለዋል። “ጭራሽ እምቢ ካላችሁ በጥይት እንገባችኋለን” ብለዋል።
ሰልፉን የከለከሉበት ምክንያት ደግሞ አባይ ዓለማቀፋዊ አጀንዳ በመሆኑ እና የተፈጥሮ አደጋም በማንዣበቡ ነው ባዮች ናቸው።
 በነገራችን ላይ በአዴኖችን አሳስብ በወያኔ ዘመን አንዲት ሴት ራሳቸው ብአዴኖች በጠሩት ስብሰባ ላይ የተናገረችው ትዝ ይለኛል። ሴትዮዋ በወቅቱ ወያኔዎች በአፋቸው የሚናገሩባቸውን የበአዴን ባለስልጣናት እንዲህ አለቻቸው:-
“…እናንተ ግን ሱሪ ነው የታጠቃችሁት ወይስ ቀሚስ ነው ያገመደላችሁት?ወንዶች መስላችሁኝ? ወያኔዎችስ እንደ እናንተ የዘጠኝ ወር ልጆች መስለውኝ?እንደዚህ ቋንጃችሁን ቆርጠው እንደ ባሪያ ሲገዟችሁ የሚስማማችሁ ምን ቢሰጧችሁ ነው?ምንድን ነው እንደዚህ አሽከር ያደረጋችሁ ፣ከአንድ እንጀራ በላይ ትበላላችሁ? መገዛቱንስ ተገዙ እሽ እኛንም አስጠቁን ግን ወያኔዎች ብለው ብለው ከስልጣን ሲነሱ እናንተ ምን ልትሆኑ ነው? መቀሌ ይዘዋችሁኮ አይሄዱም….
•ዛሬ ይዟቸው የሚሄድ ጌታ አግኝተዋል
•አትረብሿቸው
Filed in: Amharic