>

በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ህዝቦች  ማሰብም ሆነ መስማት የሰለቻቸው ፕ/ት ትራምፕንና ዶ/ር ዓብይን ነው...!!!  (አሌክስ አብርሃም)

በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ህዝቦች  ማሰብም ሆነ መስማት የሰለቻቸው ፕ/ት ትራምፕንና ዶ/ር ዓብይን ነው…!!! 

አሌክስ አብርሃም

* ደግሞ ብዙ የሚያመሳስላቸው ብዙ ነገሮች አሉ !
# ሁለቱም አገራቸው ላይ አንዱ በኮሮና አንዱ በብሔር ፍጅት ሰው እያለቀ እንዳልሰማ እንዳላየ ስለሌላ ጉዳይና በእነሱ የስልጣን ዘመን አገሮቻቸው እንዴት ስኬታማ እንደሆኑ ያወራሉ!
# ሁለቱም ሰው አያዳምጡም !
# ሁለቱም ጓዳቸው እየታመሰ ሌሎች አገራትን ካላረጋጋን የሚሉት ነገር አለ !
# ሁለቱም የህዳሴውን ግድብ የፖለቲካ ካርታ አድርገውታል
# በሁለቱም ዘመን የባለስልጣን ሹምና ሽር ለጉድ ነው
# ሁለቱም የዋህ ይመስላሉ ግን አደገኛ ናቸው !
# ሁለቱም ዓይናቸውም ጆሯቸውም የተደፈነ ካድሬዎች አሏቸው
# ሁለቱም የእምነት ሰዎች ከፈጣሪ እንደተላኩ አድርገው ይሰብኩላቸዋል !
# ሁለቱም ስለመጭው ምርጫ ከሚገባው በላይ ይጨነቃሉ !ስለምርጫ ያላቸው አቋም የተወዛገበ ነው!
# ሁለቱም ለጋዜጠኖችም ሆነ ለህዝባቸው ንግግር ሲያደርጉ እኔ ማለት ያበዛሉ
# ሁለቱም ምክር አይቀበሉም ምክር ግን ያበዛሉ
# ሁለቱም ለየአገሮቻቸው ጠላትም ችግርም የሆኑ መንግስታት ጋር አጉል
ወዳጅነት ያበዛሉ ! አንዱ የራሽያ አንዱ የኤርትራ መንግስት ጋር
# ሁለቱም ስላለፈው መጥፎነት እና ስለወደፊቱ ተስፋ እንጅ ስለዛሬ ማውራት አይፈልጉም!
# ሁለቱም የትምህርት መረጃቸው የውሸት ነው እየተባሉ ይታማሉ
# ሁለቱም ፈጣሪን እንደሚፈሩ አጥብቀው ይናገራሉ
# ሁለቱም የስልጣን ዘመናቸው በዜጎች ሞት ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዲሁም የተቃውሞ መዓበል እየተናወጠ ያለ ነው …አንበጣው የዘር ማጥፋት ወንጀሉ ኮረናው  ቃጠሎው…
Filed in: Amharic