“ሰው ከሰይጣን ይሻላል ሰይጣን ከኢሳያስ ግን…!!!”
መርእድ እስጢፋኖስ
ኤርትራ አሁንም በውጭም በውስጥም እያተራመሰችን ነው። የኤርትራ ምሁራንም ክፕሬዝዳንት ኢሳያስ እኩል ማተራመሻ ፍኖተካርታውን እያቀበሉ ነው።የገልፍ አገሮች የቆየ ጥላቻ እና ሰለፊዝም ማስፋፋት አይዲዮሎጂ ኢትዮጵያ ሀገርችን ወደ ገደሉ አፋፍ እየመሯት ትገኛለች።
ኢሳያስ አፈወርቂን የሚያውቅ ስው ራሱ ኢሳያስ ብቻ ነው።በአፍሪካ አገሮች እና በአለም ዙሪያ ካሉ ነጻ አውጭዎች ጋር እንዲሁም አሽባሪ ድርጅት መረቦች ጋር ያለውን ትሥስር ዋና ዋናዎቹን ለማሳየት ሞከረናል።
ዛሬ ደግሞ በደቡብ ሱዳን የሚሰራውን እናያለን።
ሁለት በጣም ሀብታም አገሮች አሉ በአፍሪካ።የሁለቱም አገር ህዝቦች ግን እጅግ በጣም ድሀ ናቸው።የመጀመሪያዋ ሀገር በአለም በሀብት መጠን አንደኛ ነች።የUSA ሀብትን ሶዎስት እጥፍ ይሆናል።25 ትሪሊዮን የሚገመት የተፈጥሮ ሀብት አላት።ከህዝቧ መጠን ጋር ሲዛመድ እጅግ ብልጹግ አገር ያደርጋታል።ይህች አገር ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ትባላልች።በአለም የሁማን ደቨሎፕመንት ኢንደክስ ከአለም ከመጨረሻዎቹ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች 189 ኛ። ሀፕታሟ ኮንጎ ሞፕቱ ሲሴኮ ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ ኮንጎ እንደሀገር ትመራ እንጂ ጠንካራ መንግስት ኖሯት አውቅም።መንግስት ያሉትም corrupt ከመሆናቸው የተነሳ ከሌላ መንግስታት ጋር ይሰራሉ።ለምሳሌ ነጻ አውጭው አባቱን የተካው ጆስፍ ካቢላ። የኮንጎ ፓለቲካ የሚዘወረው በቴለቪቭ ነው።የእስራኤል ኩባንያዎች የሀገሪቱ 75% ሀብት ተቆጣጥረውታል።የእስራኤል መንግስት መሳሪያ ለተቃዋሚዎች እየሽጠ ከመንግስት ወርቅና ዳይመንድ ይወስዳል።የእስራኤልን ትራፊ ደግሞ ቻይና ተቆጣጥራዋለች።በኮንጎ ሰላም የማይኖርበት አይነትኛ ምክንያት ከሁሉም ምስቅልቅል ጀርባ ያለችው ትንሿ እስራኤል ስለሆነች ነው።
ሁለተኛዋ ሀብታም አፍሪካ ሀገር ደቡብ ሱዳን ትባላለች።12ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ አላት።ወርቅና አልማዝን ይዞ ተጨማሪ 9 አይነት እጅግ በአለም ተፈላጊ መአድን አላት።ለሚቀጥሉ መቶ አመታት የሚቀጥል የተፈጥሮ ነዳጅም አላት።ከሁሉ በላይ የተሟላ ለግብርና ምቹ የሆነ መሬት ባለቤት ነች።
በልማት ደረጃ የመጨረሻዋ ስትሆን በሁማን ደቨሎፕመንት ኢንዴክዴክስ ስትመዘን 186ኛ ደረጃ ትገኛለች።190 የአለም ኢኮኖሚ ናት።
ከካርቱም ሱዳን ጁላይ 9/2011 ነጻ ብትሆንም ልክ እንደ ኮንጎ ሁሉ ጠንካራ መንግስት የሌላት ከመሆኖአም በላይ ለሌላ መንግስት የሚያገለግል አመራር አንቋታል።የሚያስገርመው የደብቡ ሱዳን ፖለቲካ ታንቆ የተያዘው በአውሮፓውያን ሳይሆን በሶዎስት የአፍሪካ አገሮች ነው።ኤርትራ ኦጋንዳ እና ኬንያ ናቸው።
ዛሬ ደቡብ ሱዳን የሚፈጸም ማንኛውም ነገር ፕሬዝዳንት ሳልቫኬር ማያሪዲት የኤርትራን አምባሳደር አለም ነጋሽን ሳያማክሩ አይሰሩም።ከኢኮኖሚ እስከ ጦር አታቼ ድረስ ልዩ ኤርትራውያን አማካሪ አላቸው።ደቡብ ሱዳን ውስጥ ኢሳያስ አፈውርቂ ሳያውቁት የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም።በማቻርና በሳልቫኬር የነበረው የሰላም ሂደት አለመሳካት ከሳልቫኬር ጀርባሆኖ የሚመራው ኢሳያስ ስለነበረ ነው።ማቻር በኢትዮጵያ ይደገፋል የሚል ስጋትን በማጫር አብዛኛውን ጊዜ የማይተገበር ስምምነት ይፈጸማል።
በጁባ ዋና ከተማ አብዛኛው ባለሀብቶች ከኢንዱስትሪ እስከፋብሪካ ድረስ በኤርትራውያን ስም ተተከፈቱ የህግደፍ/የኢሳያስ / ሀብቶች ናቸው።ከነዚህም ውስጥ የዋና ከተማዋ የኤሊትርክ መብራት የሚቀርበው” እዝራ” ግሩፕ ነው። የእዝራ ገብርጊዮርግስ ኤርትራዊው ሳልቫኪር ይሉታል ፈላጭ ቆራጭ ከመሆኑ የተነሳ ።በሁልተኛ እና በሶዎስተኛ ደርጃ ኡጋንዳዎች እና ኪንያኖች ይከተላሉ።ኤርትራ በምቶዎች ኬሎሜትር የሚቀርብ የኡጋንዳ ወደብ የኬንያ ወደብ እያላት የምጽዋን ወደብ በመጠቀም ላይ ትገኛለች።ጋዘል አል ባህር የሚባል የለም የመስኖ መሬት ከመቶ ሺ ሄክታር በላይ የኢሳያስ ሰዎች ተመርተዋል።የተባበሩት ኢሜሬትም ከፍታኛ የመስኖ መሬት ምሪትን ስትውስድ የግብጽ ባለሀብቶችም በለም መሬት ወረራው ላይ እየተረባረቡ ይገኛሉ።በዚህ አካባቢ ያሉ ንዋርዎች የዲካ ጎሳዋች ናቸው።የሳልቫኪር ጎሳዎች መሆኑ ነው።ተሻግሮ ደግሞ ሲንትራል አፍሪካ ትገኛለች።ሌላዋ ኢሳያስ ያተራመሳት ሀገር።
ደቡብ ሱዳን በኢሳያስ የሚዘወረው ፖለቲካዋ እንድተውሳስበ በዚያው ቀርቷል እንደኮንጎ ሁሉ የደቡብ ሱዳን ፓለቲካ በአስመራ ይዘውራል።ደቡብ ሱዳን ሌላ የምትታዋአቅበት 475 በላይ ወታደራዊ ጀነራሎች አሏት።ይህም ከህብ ብዛቷና ከሰርዊቷ አኳያ ሲታይ ለትንሿ ሀገር “የሺ ጀነራሎች አገር የሚል ቅጽል ስም አሰጥቷል”።
ኢስያስ አሁን እንደ ደቡብ ሱዳን ደካማ እና እንደፈለገ ሊረጋት የምትችል አገር ኢትዮጵያ እጁ ላይ ገብታለች።ቀስ በቀስ መዋቅሩን እይዘረጋ ነው።የአልጄሪያ ታዋቂው አል ዋተን የተባለ ጋዜጣ ሀምሌ 20 /2020 በካይሮ ከአቶ ኢሳያስን ጋር በአስመራ ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበረ።
ስለአልጀርሱ የኢትዮ -ኤርትራ ስምምነት አፈጻጸም ተጠይቆ ሲመልስ “አሁን ካለው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተሻለ መግባባት ላይ ስለደረስን የአልጀርሱ ስምምነት ይበልጥ በተሻለ ሚቹ ስምምነት ተክተነዋል ብሏል”
ምን አይነት ስምምነት ይሆን ? አላሁ አለም!
የተባበሩት አረብ ኢሜሬት ኢሳያስን እንደ አብሪ ጥይት በመጠቀም የቀይባህርን የንግድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ረጅም እጅችውን ዘርግተዋል።በጁባ ከወሰዱት ሰፋፊ የርሻ መሬት ሌላ በሱዳን ካርቱም የአግሮ እንደስትሪ ሜካንይዜሽን ጀምረዋል።በኬንያ ከአየር አቬሽን ጀምሮ የሊሙ ወደብን ለማልማትና በቱሪዝም ስራ ለመሰማራት እይተደራደሩ ነው።
ከጊዜ ጋር ሩጫ ላይ የሆኑት ይተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የነዳጅ ሀብታቸው 40-60 አመት ብቻ ሊያውላዳ የሚችል በምሆኑ በኢኮኖሚናበንግድ በወደብ አገግሎት በቱሪዝም እንድሁም የአካባቢውን ይፕለቲካ በሄጀሞኒ ለመቆጣጠር የሚስችላቸውን ካርታ 10 አመት በፊት ነድፈው ሲንቀሳቀሱ ነበር።እንቅፋት የሆነችው ኢትዮጵያ ነበረች ።አሁን 112 ሚልዮን ወደብ አልባ ህዝብ በቁጥጥራቸው ስር ሆኖላቸዋል።ከኢትዮጵያ በወደብ አገሎትና በትራንዚት አገግሎት ብቻ በብዙ ቢልየን ብር ገቢ ሊያገኙ እደሚችሉ አስቀድመው ጥናት አርገዋል።የኢስላሚክ የሰለፊዝም አይዶሎጂቸውንም በነጻነት በማራመድ ምቹ ሁኔታ ከመቸውም በላይ ተፈጥሮላቸው። ከጂቡቲ እስከ ሀርጌሳ ያሉ የባህር ወደብን በኪራይ ተቆጣጥረዋል።
ቀደም ባሉት የኢትዮጵያ መንግስታት የውጭ ፖሊሲ አላቸው።በተለይም የመለስ መንግስት አድናቂ እና ናፋቂ ባልሆንም ማንም እደሚያውቀው የመለስ መንግስት ከምስራቅ አፍሪካሀገሮች እስከመላው የአፍሪካ አገሮች ተጽኖ ፈጣሪ ለመሆን በቅቶ ነበር። ይህም ብቻ ሳይሆን በአለም መድረክም እንዲሁ።
የጠ/ሚ አብይ መንግስት ከመጣወዲህ ግንኙነቶች ሁሉ ወደግለሰባዊነት ተቀየሩ(one man play)።በቃ ህግም ስአርትም አሰራርም (deplomatic policy ,) አብይ ብቻ ሆነ።በህግና በፕሪንስፕል (international law and principles) የመመራት ሁኔታዎች ቀሩ።2009-2015 ድረስ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የወደብ ዋስትና ድርሻ እንዲኖራት ከጅቡቲ ጋር ስትደራደር ቆይታ የመጨረሻ ስምምነት ደርጃ ላይ ተደርሶ ነበር።አብይ ፊቱን ወደ ኢሳያስ በማዞሩ ስምምነቱ ሳይፈጽም ገደል ገባ ።ሀርጌሳ የፑንት ላንድ ወደብ 25% ድርሻ ሊፈረም አንድ “ሀሙስ”የቀረው የመጨረሻ ዙር ውይይት በሀይለምረያም ደሳለኝ መንግስት ተጠናቆ ነበረ። አብይ በኢሳያስ ሳንባ ልተንፍስ በማለቱና በሁለቱ ሱማሌዎች ጣልቃ በመግባቱ ሳይሳካ ቀረ።ኩሩዎቹ የፕንት ላንድ ሱማሌዎች “ሙአረስ”የሚል ስም ለአብይ ሰጥተውታል ።በቡና ግብዣ የሁለቱን ሱማሌ ችግር ለመፍታት በመሞከሩ።ያለ እውቀት እና ያለብስለት የሚደረግ ዲፕሎማሲይዊ ጣልቃ ገብነት ዝቅ ሲል ያቀያይማል ከፍ ሲል ዋጋ ያስከፍላል ሁሉ።
ሌላው በውጭ ሀገር የሚኖሩ አኤርትራውያን ምሁሮች በአብዛኛው ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው ናቸው።በአሁኑ ሰአት ስለራሳቸው ዲክታተር መንግስት ኢሳያስ አፈውርቂ ማውገዝ መቃወም ሳይሆን ስራቸው ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ መጽሀፍ ማሳተም ሆኖአል።በማህበራዊ በመገናኛ ዘዴዎችም እየተረባረቡ ነው።የጽሁፋቸው መነሻም መድረሻም “ኢትዮጵያ በገዳ” ብትተዳደር ይሻላታል የሚል ነው።”የነሞጋሳን” ታሪክ እንደተለመደው በሌለ ትርክት እርስበርስ የሚያጣላን እውነት እና ውሽት የቀላቀለ ታሪክ እያቅረቡልን ነው። ከዚሁ ሁሉ ጀርባ የሚገኙት ጥቅም ምንድነው? ብለን ስንጠይቅ በሀይማኖትና በቋንቋ የተከፋፈለች ኢትዮጵያ ጠንካራዋን የቀይባህርን 2 ግዙፍ ዋደብ የያዘችውን ትንሿን እስራኤል በአፍሪካ የመፍጠር የቆየ ሕልማቸው እንደሆነ በግልጽ ይናግራሉ.
ሁልተኛው የመጨረሻው ግብ ገልፍ አገሮች መውጫና መግቢያ ለሁልቱ ወደብ አልባ አገሮች ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ብቸኛ አማራጭ መሆን ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው በላይ የምስራቅ አፍሪክ ፖልቲካ በምያወላዳ መልኩ በቁጥጥር ስር ማዋል ይሆናል።
” ኢሳያስ የኢትዮጲያ መቅሰፍት”