>

ሰልፉን መከልከል " አራጁ እኔነኝ " እንደማለት ያስቆጥራል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ሰልፉን መከልከል ” አራጁ እኔነኝ ” እንደማለት ያስቆጥራል…!!!

ዘመድኩን በቀለ
 

 

ስማኝማ ልንገርህ  !!
የብልጽግና መሪዎች በሙሉ አክራሪ ፕሮቴስታንትና አክራሪ ሙስሊሞች ናቸው። ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ኦርቶዶክስም ናቸው።  የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር አባላት (ኦነግና) ፀረ ኢትዮጵያ ኃይላትም ናቸው። የዐማራ ብልጽግናም በሙሉ ማለት ይቻላል የብልጽግና ወንጌል አማኞች ናቸው። በፊት የህወሓት አሁን የኦነግ ገሌና ወዶ ገብ አሽከሮችም ናቸው። ኮንፊዩዝድም ኮንቪንስም የተደረጉ ማቶዎች ናቸው።
•••
እናም የብልጽግና አሽከሮች ዘወትር መስማት የሚፈልጉት የማይነኳትን፣ የማይዳስሷትንና፣ የማይጨብጧትን ህወሓት የተባለች ፈጣሪያቸውን እንደ መንደር ሙጢ ሴት እንድትሰድብላቸው፣ እንድታዋርድላቸው፣ እንድታንጓጥጥላቸው እንጂ ገዳዩን፣ አራጁን፣ በቁም ዐማራን ጨፍጫፊውን ኦነግን እንድትቃወም፣ እንደታወግዝ አይፈቅዱልህም። በጭራሽ። በጭራሽ አይፈልጉም።
ወዳጄ ዐማራና ኦርቶዶክስ ከገዳዮች፣ ከጥቁር አፓርታይዶች ነፃ መውጣት አለበት። አከተመ። 
•••
በዐቢይ እውቅና የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራህን ከሚቀማህ ጴንጤ ምንም ቀና ነገር አታገኝም። የታቦት ማክበሪያ ስፍራህን ከሚያዋርደው፣ ከሚያቆሽሸው፣ ከሚያበሻቅጠው፣ የሽንት፣ የሰገራ መውጫ ከሚያደርገው፣ ከሚያግማማው፣ ከሚያከረፋው፣ ከሚያጠነባው ከሚያርድህ ኦነግ፣ ከሚያሳርድህ ብልፅግናም ምንም አታገኝም። መብትህን ማሰከበር የራስህ ፈንታ ነው። አለቀ።
•••
የዐማራ ልዩ ኃይል ከፀረ ዐማራው ብልጽግናና ከሚታረደው ወገንህ አንዱን ምረጥ። መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ ውስጥ ያላችሁ የዐማራ ልጆች ነገሩን በትኩረት ተመልከቱት። ነገዳችሁን አቅመቢስ አታድርጉት። ከወገናችሁ ጋር ቁሙ። ቤኒሻንጉል መተከልም፣ በኦሮሚያ በደቡብ በቤንች ማጂ ዞን በጉራ ፈርዳም፣ ዐማሮችን ያሳረደው ብአዴን መሆኑን ለማወቅ ከፈለክ ጥቅምት 18ን መጠበቅ ነው።
•••
ወቅቱ ሰልፍ የሚወጣበት አይደለም። ሆኖም ግን በደሉ አይደለም ሰልፍ ሰይፍ ብታነሱ አይፈረድባችሁም። እናም ሰልፍ የሚወጡት ልጆችን በዐማራ መሬት የሚገድል ካለ እሱ የኦነግ ሰራዊት መሆኑን ከወዲሁ እወቁት። እደግመዋለሁ። ሰልፍ ወጥቶ አትግደሉን ብሎ ወጥቶ መግባት መብቱ ነው። ህዝቡ ተንፍሶ በሰላም ወጥቶ ይግባበት። ይኸው ነው።
•••
ኦርቶዶክሳውያን ግን መብታችሁን በሰላማዊ መንገድ ለማስከበር ተዘጋጁ፣ በጸሎት እንዘጋጅ። ሞኝ ጅል ያለመሆናችንንም ለማሳየት እንዘጋጅ። ከብልጽግና አክራሪ ጴንጤ የሚሰጥህ አንዳችም መብት እንደሌለም ከወዲሁ እወቅ። በኢትዮጵያ ስም ማደንዘዙ ተነቅቷል። አዚሙም ከሽፏል።
መተከል • ጉራፈርዳ • ሙሉ ኦሮሚያ የታረደው ዐማራ ኦርቶዶክስና ሙስሊም ዐማራ ነው።
 የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የወላይታና የጉራጌ ኦርቶዶክሳውያንም በኦነግ ብልጽግናዎች ታርደዋል። ይሄን ለመቃወም ደግሞ አራጁን ማስፈቀድ አይጠበቅም። ሰልፉን መከልከል አራጁ እኔነኝ እንደማለት ያስቆጥራል።
•••
አሁን በደረሰኝ መልእክት መሠረት “የጉራፈርዳ አራጆቹ ወደ አጎራባች ወረዳ ፤ ደቡብ ቤንች ወረዳ አድስዓለም ቀበሌ በ1977 የሰፈሩ ዐማራዎችን ለማረድ ገብተዋል፡፡ ለወረዳውም ሆነ ለዞኑ ፀጥታ ሪፖርት ቢደረግም ሰምተው እንዳልሰሙ ዝም ብለው ህዝቡን ሊያስጨፈጭፉት ነው፡፡
ት/ቤቶች ተማሪዎች ከምትታረዱ በጊዜ ወደ ቤታችሁ ሂዱ እያሉ በትነዋል፡፡ ራሳቸውም ለህይወታቸው ተጨንቀዋል፡፡
•••
እነ ብርሃኑ ጁላ ሌላ ዐማራ ሊያሳርዱ ነው ማለት ነው። በሌላ በኩል ከ 15 ሚልዮን በላይ ዐማሮች፣ ኦሮሞ፣ አፋርና ትግሬዎች የከፋ ራብ ውስጥ መዘፈቃቸው ተነግሯል። አቢቹ ግን ዘና ፈታ ብሎ ይቀልዳል።
Filed in: Amharic