>
5:31 pm - Thursday November 12, 7276

የተስፋዬ ገብረአብ መንገድና የአብይ አህመድ እርምጃ ...!!! (ሀብታሙ አያሌው)

የተስፋዬ ገብረአብ መንገድና የአብይ አህመድ እርምጃ …!!!

ሀብታሙ አያሌው

 

* ተስፋዬ ገ/አብ ከአንድ ዓመት በፊት ለአብይ አህመድ ምን መከረው ?
* አማራውን ምን አድርግ አለው ? 
*  በእስክንድር ላይ ምን አይነት እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበው ? 
* ለሽመልስ አብዲሳ ምን አይነት አቅጣጫ ሰጠው ??
* ዛሬ ምን እየሆነ ነው …??
~~~~~~~~~~~~~
(ተስፋዬ ገ/አብ)
===========
ስላም ወገኖቼ ፥ ጃዋር የኦሮሞን የ50 ዓመት ትግል በግልፍተኝነት እያበላሸው ነው። ቄሮ የከፈለውን መስዋትነት ደመ ከልብ የሚያደርግ የልጅ ዕልህ ባይገባ ጥሩ ነው።
ብልጽግና ፓርቲን ተውት ፥ አይሰራም መልሰው ቤታችን ይሻለናል ማለታቸው አይቀርም። አብይ በዘዴ የነፍጠኛውን አከርካሪ እየሰበረው ባለበት በዚህ ሰዓት የጃዋር መንቀዥቀዥ ነፍጠኛውን አሰባስቦታል አሁን ከፍተኛ ትግል ይጠይቃል ለመቀልበስ ለዛውም ከተቻለ ነው።
ኦፒዶኦ ህውሃት የሄደችበትን እና ወደ መቀመቅ የከተታትን ስልት፥ ዝፍጥ የሆኑ የሳይበር ቅጥረኞችን መጠቀሙ እና ጀማሪ ካድሬዎች ልምድ ባለመኖራቸው ኦፒዲኦን ከኦነግ ጋር አብሮ እንዲመታ አስተዋጾ ማድረጋቸው አይቀርም።
ጀማሪ ኦሮሞዎች እና ጀማሪ የኦነግ ካድሪዎች የኦሮሞን ትግል ከ50ዓመት በፊት እንደነበረው መመለሳቸው አይቀርም ካልተመከሩ።
ነፍጠኛው የሺ ዓመታት ልምድ ስላለው በ ጨቅላ ፖለቲከኞች እና በግልብ ካድሬዎች ማሸነፍ አይቻልም ፥” አከርካሪውን ሰብሬአለሁ ” ብትል ምላስህ ይሰበራል እንጅ ነፍጠኛን እንኳን በ2ዓመት ሰፈራ 100 ዓመትም ኦሮሞን ፊንፊኔ ውስጥ ብታሰፍረው መስበር አትችልም።
አብይ በቀስታ እየሄደ ልክ እያስገባቸው ነበር ፥ የልጅ ነገር ሆኖ ሽመልስ ግመሉ እና ጃዋር ትንፋሹን መቆጣጠር የማይችለው ግልቡ የኦሮሞን ትግል አራከሱት።
ከነ ሌንጮ መማር ያልቻሉ ብያቸዋለሁ።
* እስክድንር አካሄዱ በጣም የሰለጠነ እና ባጭር ግዜ ውጤት የሚያመጣ ነው። ኦፒዲኦ እስክንድርን ወደ ቀድሞው* ቤቱ ካልመለሰው እስክንድር በጥቂት ወራት ቄሮ በለው አብይ እና ለማን በዓለም አቀፍ አደባባይ ታዳኝ ሰዎች ሊያደርጋቸው የሚችል እንቅስቃሴ ነው የጀመረው። ይሳካለታል ፥ ምክንያቱም በቂ የቪዲዮ እና የምስል ማስረጃዎች ብሎም የሰብዓዊ ተቋማት ኦሮሚያ ውስጥ ሪፖርት ያደረጉት ስለሆነ እነዚህ ተጣምረው ጭዋታውን ይቀይሩታል።
መፍትሂው ፥ ጃዋር አርፈህ መቀመጥ ፥ ምርጫውን ዕርሳው የልጅ ጨዋታ ካልሆነ በስተቀር ፥ በአሜሪካ ፓስፖርት መወዳደር አትችልም አታምታታ ፥ ይልቁንም የነ አብይን የበሰለ አካሄድ አታስበላቸው።
ሽመለስ ከጃዋር ትዛዝ መቀበሉን ተወው ፥ አብይን ስማው ያለበለዚያ ቃሊቲ መግባትህ ነው። አብይ ፥ አታንቀላፋ ብልጽግናን ትተህ ፥ ብ አ ዴ ንን በስርህ አድርገህ ኢትዮጵያን ምራ ፥ ኦሮሞ በልኩ ኢትዮጵያን ያስተዳድራት። ለዛሬው አበቃሁ።
Filed in: Amharic