>
5:28 pm - Friday October 10, 6347

"የአገሪቷን ጉዳይ በሚመለከት የሚወያይ፣ አገር (ሁሉን) አቀፍ ጉባኤ በአስቸኳይ ሊጠራ ይገባል...!!!" (አቶ ተማም አባቡልጉ- የሕግ ባለሞያ)

“የአገሪቷን ጉዳይ በሚመለከት የሚወያይ፣ አገር (ሁሉን) አቀፍ ጉባኤ በአስቸኳይ ሊጠራ ይገባል…!!!”

አቶ ተማም አባቡልጉ (የሕግ ባለሞያ)
——-

አሁን በኢትዮጵያ ያለው መንግሥት፣ “የሽግግር ወቅት ላይ ነን …” ብሎ ነበርና፣ ለብቻው መወሰን የማይችላቸው ነገሮች አሉ፣ ስለሆነም:-
1. የወደፊት አኗኗራችንን፣ አሁን ያለንንና ወደፊት የሚኖረን ግንኙነታችንን መልክ እና ዓይነት የሚለውጡ:-
1.1. እንደ ሕገ መንግሥት ለውጥ ያሉትን ሊያደርግ ስለማይችል፣ የሕገ መንግሥት ለውጥ ሊያደርግ አይገባም፣
1.2. ለትግራይ ክልል የሚሔደውን በጀት፣ በተለመደው መልኩ ሊላክላቸው ይገባል፣
2. በቋሚነት የአገርን ቅርፅ ሁኔታ መለወጥ ስለሌለበት፣ የክልልን ቅርፅ መለወጥ የለበትም፣
3. የአገርን ሀብት ይዞታ በቋሚነት የሚለውጡ ድርጊቶችን መፈጸም ስለሌለበት:-
3.1. ስለ ዓባይ፣ የቱንም ስምምነት መፈረም የለበትም፣
3.2. የሕዝብ ሀብት የሆኑት፣ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ቴሌኮሙኑኬሽን፣ መብራት ኃይል …ወዘተ. የሕዝብ አትራፊ የንግድ ተቋማት(ፐፕሊክ ኢንተርፕራይዝ)  ያሉትን፣ ለማንም ማስተላለፍ የለበትም፣
3.3. ሌሎች ወገኖችም ይህንኑ አውቀው፣ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉት ስምምነቶች፣ የማይጽኑና አስገዳጅነት የማይኖራቸው መሆኑን ተረድተው፣ ከዚህ ድርጊት ሊቆጠቡ ይገባል፣
4. የአገሪቱን ጉዳይ በሚመለከት የሚወያይ፣ አገር (ሁሉን) አቀፍ ጉባኤ በአስቸኳይ ሊጠራ ይገባል።
Filed in: Amharic