>
5:29 pm - Wednesday October 11, 4930

አማራና ትግሬ (መስፍን አረጋ)

አማራና ትግሬ

መስፍን አረጋ 


አማራና ትግሬ በጥቅል ሐበሻ

ርስበርስ ተናክሰህ በምክኒያት ተልካሻ

ስትዳከምለት በስተመጨረሻ፣

ሥጋህን በጫጭቆ የኦነጉ ውሻ

ለሃች ይቀብርሃል እሶፍ ኡመር ዋሻ፡፡

 

የትግሬና አማራ በእሳት መንገብገብ

ያብይ እዳር ሁኖ እሳቱን ማራገብ

እንዲህ ይመሰላል ባንበሶችና ጅብ፡፡ 

በእኔ ነግስ እኔ ነግስ ውጊያ በመቀስቀስ

አንበሳና አንበሳ ተፋልመው እርስ በርስ

አንደኛው ድል ሆኖ የሞት ጽዋ ሲቀምስ

ሌላኛው ሲያጣጥር ግቢ ነፍስ ውጭ ነፍስ፣

የሞተን ተራምዶ የቆሰለን ገድሎ ጅቦ ሆነ ንጉስ፡፡ 

 

ያገርህ፣ የምነትህ፣ ያንተነትህ ዳራ       

ባንድኛችሁ እንኳ እንዲኖር ሲጠራ

ሳትጋደል በፊት ከወንድምህ ጋራ

የጋራ ጠላትህ መሞቱን አጣራ፡፡

 

መስፍን አረጋ :- EMAIL: mesfin.arega@gmail.com

                   

Filed in: Amharic