>
5:31 pm - Tuesday November 12, 7985

79 ብሔረሰብ ተረሳ ማለት ነው! መልዕክቱ ለማን እንደሆነ ግልፅ ነው...!!! (ታዬ ቦጋለ)

79 ብሔረሰብ ተረሳ ማለት ነው! መልዕክቱ ለማን እንደሆነ ግልፅ ነው…!!!

ታዬ ቦጋለ 

እኛ ግን፦
1. ኢሬቻ ላይ የፈጃችሁንን አንረሳውም!
2. አርቲስት ኤቢሳ አዱኛን ከነህይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ከመኪና ኋላ ጎትታችሁ መግደላችሁን አንረሳውም!
3. የደምቢ ዶሎዋን እናት ልጇ አስከሬን ላይ ማስቀመጣችሁን አንዘነጋውም!
4. ነቀምት የፈሰሰውን ደም አንዘነጋውም!
5. የአምቦን የ27 ዓመት የብቀላ ብትር እናስታውሰዋለን!
6. አዶላ ወርቅ ማዕድን የደረሰብን ግፍና ጠባሳ የትላንት ነው!
7. እንደ ህዝብ “ጠባቦች” ያላችሁን የአእምሮ ቁስል አልዳነም!
8. የኦሮሞን ገበሬ ከእርሻው እያፈናቀላችሁ ባለሀብቶቻችሁን አስፍራችሁ የበላችሁት ዛሬም ፍትህ አላገኘም!
9. ሞያሌ በጠራራ ፀሐይ በስናይፐር ንፁሃንን ለኮንትራባንድ ሌብነታችሁ መፍጀታችሁ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው!
10. ታየ ደንደአን ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ ለ10 ዓመታት አሰራችሁ። ኦሮሞ ሆኖ ዩኒቨርሲቲ መማር መረገም እስኪመስል ዋጋ ተከፍሏል!
11. እስር ቤት ውስጥ የኦሮሞ፦
# ሴቶችና ወንዶች ተደፍረዋል
# ብልታቸው ላይ ኮዳ ተንጠልጥሏል
# ጥፍራቸው ተነቅሏል
# ተገልብጠው ቶርቸር ተደርገዋል
# በማህፀናቸው ብረት ገብቷል
እግራቸው ተቆርጧል
ዐይናቸው ፈርጧል
በማንነታቸው ተሰድበዋል…
12. ከአብዲ ኢሌ ጋር በመሆን ከሶማሊ ሚሊዮን ኦሮሞ አፈናቅላችኋል!
13. ከሶማሊ የወቅቱ ሄጎ ጋር በመሆን ቦረናን በተደጋጋሚ ጨፍጭፋችኋል!
14. አንድ ከኦሮሞ፣ አንድ ከአማራ፣ አንድ ከትግራይ፣ አንድ ከደቡብ የሚለው የሥራና የአመራር ቅጥር መስፈርታችሁ፤ ከትግራይ ጋር ሲነፃፀር በቁጥር ስምንት እጥፍ የሚሆነውን ኦሮሞ ሥራ የማሳጣት ፕሮጀክት እንደነበር አንዘነጋውም!
15. ዓለማየሁ አቶምሳ፣ ወልደማርያም ዋቆንና አያሌ የኦሮሞ ምሁራንና መሪዎችን በስውር ገድላችኋል!
16. ኦሮሞ በስናይፐር ያልተጨፈጨፈበት ከተማ የለም ማለት ይቻላል!
17. ኦሮሞን፦ ከሶማሊ ከአማራ ከአፋር… ከማጋጨታችሁ አልፎ፤ ቦረናና ጉጂ ኦሮሞን በረቀቀ የአስተዳደር ሴራ እስካሁን ያልተፈታ ነቀርሳ ተክላችኋል!
18. ዛሬ በአንድ ቀዳዳ እንፀዳዳ ያላችሁት ኦነግ ላይ “የሳራ በረሀ ምሥጢር” በሚል ዘመቻ፤ ኦነግን ሳይሆን ንፁህ የኦሮሞ ልጆችን ጨፍጭፋችሁ ድራማ ሰርታችኋል!
19. የ27 ዓመታቱ መአት…
20. ኢትዮጵያ ለኦሮሞ ባለፉት 27 ዓመታት የአገዛዝ ዘመናችሁ የከፋች ሲዖል ነበረች።
በመሆኑም የኦሮሞ ወገን በእናንተ የሚጭበረበር ጅል አይደለምና ማላገጣችሁን አቁሙ!
Filed in: Amharic