ከደደቢት እስከ መቀሌ የህወሀትን ነገር ሳስብ እንደው ግርርርርርም ይለኛል?!?
ዮናታን መንክር
1. የህወሓት ነገር
በ30 ዓመት ውስጥ 2 ጊዜ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጋር ተዋግቷል። 1 ጊዜ ከቀድሞ የትግል አጋሩ ሻዕቢያ ጋር በኢትዮጵያ ሠራዊት በኩል ሆኖ ተዋግቷል።
ግርምት 1
ደርግ ወንበዴው ይለው ነበር በኋላ መንግስት ሆነ
አሁን ተመልሶ ወንበዴው መባል ጀምሯል። ይሄ ሁሉ የሆነው እንግዲህ በአንድ የወጣት ሰው ዕድሜ ነው።
ግርምት 2
የህወሓት ጦርነቶች አምባገነን እና አሀዳዊ ነው ያለውን ደርግን ተዋጋ። አምባገነኑ የሻዕቢያ መንግስት እያለ የበረሀ ጓዱን ሻዕቢያን ተዋጋ።
አሁን ደግሞ ራሱ ያሳደጋቸውን ልጆች አምባገነን እና አሀዳዊ ናቸው ብሎ እየተዋጋ ነው። ይህ ሁሉ የሆነው በአንድ ወጣት ዕድሜ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ በ40 ዓመታት የተደረጉት ጦርነቶች ሁሉ ወይ ከህወሓት ጋር ነው ወይ በህወሓት ነው።
የመንግስቱ ኃ/ማርያም ዕድሜ
ግርምት 3
ጓድ መንግስቱ እንደው ያኔ ወንበዴ ሲላቸው የነበሩት ሕወሓቶች በኋላ መንግስት ሆነው አሁን ደግሞ የሱ ዕጣ ደርሷቸው ከመዲናዋ ሸሽተው መኖራቸውና ጭራሽ እሱው በሚጠራበት ስም ወንበዴ ሲባሉ ሲሰማ ምን ይሰማው ይሆን?
ግርምት 4
ህወሓት ከደርግ ጋር ሲዋጋ ደርግ የኢትዮጵያ ገዢ ስለነበር ጦርነቱ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር።
በኋላ ከሻዕቢያ ጋር ሲዋጋ ህወሓት የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኖ ተዋጋ። አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ ጦር ጋር እየተዋጋ ነው።
በ30 ዓመት ውስጥ ሁለቴ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጋር የተዋጋ ቡድን መሆኑስ አይገርምም?
ከዚህ ሁሉ በላይ የተገረምኩት በዕድሜ ነው። ለካ የቆየ ሰው ብዙ ያያል የሚባለው ለዚሁ ነው።
ምኞቴ ሰላም ነው።