>
5:28 pm - Tuesday October 10, 6113

አማራ ሆይ  ከስሜት ወደ ስሌት...! (ዘመድኩን በቀለ)

አማራ ሆይ  ከስሜት ወደ ስሌት…!

ከጦርነቱ መልስ “…ወልቃይትን፤ ጠገዴን ራያንም ልቀቅ” ላለመባልህ ምን ዋስትና አለህ???
ዘመድኩን በቀለ
         *~★★★~*

 “ ጠረጋው ገና አልተጀመረም። የከፋው ቀን ከፊታችን ነው። ጾም ጸሎት ምህላውም አይረሳ። የሞላላችሁ ንስሐ መግባት፣ ሥጋወደሙ መቀበልንም ቸል አትበሉ።  
 
የቤተ ክህነቱ ብልጽግናዎች ግዴላችሁም ቀዝቀዝ በሉ፤ አሁን ካለው ይልቅ እየመጣ ያለው አስፈሪ ነውና.  .  !?!
•••
“ መቼም ይሁን መች ለዚህ ሁሉ ሃገራዊ ውድቀት የዳረገችን ያቺ መርዘኛዋና ለኢትዮጵያም ካንሰር የሆነችው ጠንቀኛዋ ህወሓት ናት። ያሳደገቻቸው እባቦዘች መልሰው ዘንዶ ሆነው ውጠዋታል። ጋንግሪኗ ህወሓት ከላያችን ላይ ተቆርጣ መጣሏም አይቀርም። እሷ ከኢትዮጵያ ምድር ማኔ ቴቄል ፋሬስ ከተባለች ቆየች። ዕድል ፈንታዋ፣ ፅዋዕ ተርታዋም ከተዘጋ ቆየ። የእድሩ ድክመት እንጂ ህወሓት መቀበር የነበረባት ይሄ ነውጥ መጣ በተባለ ሰሞን ነበር። ያኔ ጄነራል ክንፈ ዳኘውን በሰንሰለት ቀፍድዶ በቢጫዋ ሄሊኮፕተር ያመጣው አካል በዚያው በነካ እጁ መቀሌ የመሸጉትን ካንሰሮች ለቃቅሞ ቢያመጣቸው ኑሮ አሁን ይሄ ሁሉ ውዝግብ ባልተፈጠረም ነበር። ብረትን እንደጋለ ነው የሚባለውን መጠቀምም ያኔ ነበር። አሁንም እንኳን ጭርሱኑ አልቀረ እንጂ መርፈዱም ምንም አይደል።
•••
አሁን እኔ የህወሓት ነገር ብዙም አያሳስበኝም። ለበሰበሰ መንጋ፣ የሞት አፋፍ ላለ ጨካኝ እግዚአብሔርም ቆርጦ ለጣለው ነውረኛ ቡድን የማስብበትም ጊዜ የለኝም። ህወሓትን ራቡም፣ ጭንቀቱም፣ ደምብዛት ስኳሩም ተደማምሮ ክልትው ያደርጋታል። እናም እሷ ብዙም አታሳስበኝም። አይደለም መብራት፣ ውኃ፣ የቴሌኮሚኒኬሽን ተዘግቶባት እንዲሁም የበሰበሰች ግንድ ናት። እናም ይሄ በፍጹም በፍጹም አያሳስበኝም። እኔ የሚያሳስበኝ ሌላ ነው።” ህዝቡ ያሳስበኛል። ከተቻለና ብልህ ከሆነ የትግራይ ህዝብ መርዛሞቹን የሀገር አራሙቻዎች እሹሩሩ እያለ አብሮ ከሚጎዳ በጊዜ አሳልፎ ቢሰጥና ቢገላገልም ብዬ እመርጣለሁ። በሰማይም በምድርም ለህወሓት ተብሎ የሚወረወረው እሳት አብሮ ከሚያቃጥለው በጊዜ ከተደበቁበት ጎትቶ እያወጣ አሳልፎ ቢሰጥም “ፅቡቅ ኔይረ” ብዬ እመክራለሁ። በደም የተገነቡ ከተሞች ሳይቃጠሉና ሳይፈራርሱ በጊዜ እጃቸውን ቢሰጡ ብዬ እመክራለሁ። ይሄን የምለው ለህዝቡ ስል ነው። አሊያ ግን ጎረቤት ሃገር ሻአቢያም አየር ኃይሉ ውስጥ ላለመኖሩ ዋስትና የላችሁም። መቼም የምለው ይገባችኋል። አስመራ በመቀሌ ጽዳት…
•••
ማነህ እንቶኔ አሁን እኔ ዘመዴን ዝምበል አንተ ሃድጊ፣ ነፍጠኛ፣ የደርግ ርዝራዥ፣ አሃዳዊ፣ ደፍተራ፣ ጠንቋሊ እያልክ የምትቀጠቅጥበት ዘመን ላይ አይደለህም ያለኸው። አሁን ዐማራ እንዲህና እንዲያ ነው ብለህ ፀጉርህን የምትነጭበት ዘመን ላይ አይደለህም። 45 ዓመት ሙሉ ያላጠፋኸውን ዐማራ ዛሬ ወደ መቃብር እየወረድክ ብትጮህበት፣ ብትጭርበት፣ ዐማራዬ፣ ጀግናዬ ብትለው  መስሚያው ጥጥ ነው። እገሌ ነው ዐማራ፣ ጎጃም ኦሮሞ ነው፣ ሸዋ እንደዚያ ነው ብትል ማን ይሰማሃል። https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2765378630396604&id=100007734818814 ። ወዳጄ አይንህ እያየ የዐማራው ፀሐይ ስትወጣ የአንተ የካድሬው ጀምበር ደግሞ ለመጥለቅ አዘቅዝቃለች። የሚያዋጣው ላለፈው ንስሐ መግባት ነው። አሁን ኡስስስ ዝም በል። ሰምተሃል !!
•••
ህወሓት የምትባለው መርዝ፣ የሃገር ነቀርሳ በሞራሉ፣ በእምነቱ፣ በባህሉ፣ በማንነቱ፣ በስብዕናው ላይ በፈፀመችው አሰቃቂ ፋሽስታዊ በደል የተነሣ ህወሓት የተባለችን ጨካኝ አረመኔ ፍጡር የሚበቀልበት ቀን ሲጠባበቅ የነበረው የዐማራ ነገድ ዛሬ ይሄን የማርያም መንገድ ሲያገኝ ግልብጥ ብሎ በእልህ ቤቱን ደጃፉን ጣጥሎ ነቅሎ በህወሓት ላይ መዝመቱም፣ ሆኖ ብሎም በህወሓት ላይግልብጥ ብሎ መውጣቱም የሚጠበቅና ተፈጥሮአዊም ሕጋዊም ነው። ነገር ግን ዐማራው የትኞቹም ክልሎች ሳይረዱት፣ ብቻውን፣ ያውም ገበሬው፣ አምራቹ ክፍል ብቻውን፣ እደግመዋለሁ ብቻውን ልጁንም፣ ቤተሰቡንም ሳያስቀር ወንድ የሆኑትን በሙሉ አስከትሎ ወደ ጦርነቱ መትመሙን አልወደድኩለትም። ነገሩን በጥንቃቄ እዩት። ተናግሬአለሁ በጥንቃቄ እዩት። መከላከያ ሠራዊቱን የሚያግዝ ጥቂት የዐማራ ልዩ ኃይል ለወራዳዋ የህወሓት ሰራዊት ከበቂ በላይ ነው። ህወሓት የሞራል ልዕልና ስለሌላት የቄራ ልጆች እንኳ ድንጋይ ይዘው ቢሄዱ የምትሸነፍ ደካማ ናት። የንፁሐን ደም፣ ያረደችው፣ ስታፈስ የኖረችው የኢትዮጵያውያን ደም ራሱ አዙሮ በአፍጢሟ ይደፋታል። እናም ዐማሮቹ ብትሰሙኝም ባትሰሙኝም ምክሬ ግን ይኸው ነው። ሰፈር ጠባቂ ሳታስቀሩ፣ ለቀጣይ ጦርነት የሚዘጋጅ ኃይል ሳታስቀሩ መትመማችሁን አልወደድኩትም። ለህወሓት መከላከያ ሠራዊቱ ራሱ ብቻውን በቂዋ ነው ባይ ነኝ።
•••
አሁን ያለው ተዋጊው የዐማራ ሠራዊት ተተኪ እንኳን እንዳያሰለጥን የተደረገ መሆኑን ከግምት ውስጥ ብታስገቡ መልካም ነው። በሌላ በኩል ዐማራው በጠላት እንደተከበበም መዘንጋት የለበትም። ቤትህን ብርግድ አድርገህ በእልህ ወደፊት መንጐዱ ብቻውን  አዋጭም አይደለም። ከኋላህ ግማሽ ሚልዮን ለወጊያ የተዘጋጀ፣ የሰለጠነና ሙሉ መሣሪያ የታጠቀ የአክራሪ ፕሮቴስታንትና የአክራሪ እስላም ስብስብ የሆነ የዐቢይ ሽመልስን የአባ ገዳ ጦር አስቀምጠህ በእልህ ጉልበትህን ባትጨርስ ብዬም እመክርሃለሁ። ኦጎኖቼ ኃይል ቆጥቡ። ተናግሬአለሁ።
•••
የዐማራ ገበሬ ከጦርነቱ በሰላም ባይገባ እኮ ጦሱ ከቤት ለቀረችው ሚስትና ልጆቹ፣ አባትና እናቱ ነው የሚተርፈው። ዘማቹ ካሳም ደሞዝም፣ ጡረታም እንደሌለውም ይታወቅ። እናም ገበሬው የዐማራ ተዋጊ ኃይል ድንበሬ የሚለውንና ህወሓት በኃይል የቀማችውን ግዛቱን የአባቶቹን ርስት ካስመለሰ በኋላ ወደ ትግራይ ግዛት እሱ ባይሻገርም ፈቃዴ ነው። ይሄን ማድረግ የሃገር መከላከያ ሠራዊቱ ሥራ ቢሆንም እመርጣለሁ። ነገር ግን ከኋላ ያለው የዐቢይ ሰበካና ዐማራው በህወሓት የደረሰበትን በደል እያሰበ ምክሬን በቀላሉ ይሰማኛልም ብዬም አይደለም። ቢሆንም ግን ለታሪክ ይቀመጥ።
•••
ትናንትና ደሴ ላይ የዐማራ ልዩ ኃይልን በማሰልጠናቸው ብቻ ተቆጥቶ፣ ሰድቦ፣ አዋርዶ፣ አንጓጦ ያም ሳይበቃው አክሱም ላይ ከደብረ ጽዮን ጋር መክሮ ሲያበቃ በከሃዲያን ቅጥረኞች በኩል እነ ዶር አምባቸውን፣ ጄነራል አሳምነው ጽጌንና ሌሎችንም የዐማራ ልጆች አስወግዶ የሰባበረህ፣ ፖለቲካም የሠራብህ ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የዐማራ ልዩ ኃይልንና እያሳደደ ሲቀጥፈው የኖረውን ፋኖ በሙሉ ምንትስዬ፣ ቅብጥርስዬ የእኔ ጀግና ስላለህ ብዙም ባትሸወድ መልካም ነው። ፀረ ዐማራው የኢዜማ ቡድን ጀግና እያለ ስለጻፈልህ ብዙም አትሸወድ። ጦርነቱ መቀሌ ላይ ብቻ አያልቅም። ይሕን ዕወቅ። ዐውቀህም ተዘጋጅ።
•••
አስተውል ከአሁኑ ዛሬ ሱዳን በድንበሯ አካባቢ የሚገኙ የዐማራ ባለሃብቶችን የእርሻ ካምፖችን አቃጥላለች የሚል መረጃ እየወጣ ነው። የኦሮሞ 10ሺ ሠራዊትም ባሕርዳር ይገባል እየተባለም ነው። ነገ ሱዳን በሰላም አስከባሪ ስም ዘው ብላ ብትገባ የዐቢይ ሽመልስ የአባ ገዳ መከላከያ ሠራዊት አያድንህም። አይረዳህምም። እናም ኃይልህን በጥበብ ተጠቀም። አታባክን።
•••
ከግማሽ ሚልዮን በላይ በሚገባ የሰለጠነው የኦሮሞ አባ ገዳ ሠራዊት አሁን በየትኛውም የኦሮሚያ ግዛት ዐማሮችን መግደል አቁሞ ቀጣዩን የዐማራና የትግሬ ጦር ፍስፍስ እየተጠባበቀ ነው። የሚገርመው ነገር የኦሮሞ ጦር አሁን ድምጹ አይሰማም። የሚገደል የሚታረድ ዐማራም በየክልሉ የለም። ዐማራውን በወለጋ በሻሸመኔ አርዶ አሳርዶ ስሜቱን ካጦዘው በኋላ ይሄው ዛሬ በደንፉ ህወሓትን እንዲቀጣለት እየማገደውም ነው የሚሉም አሉ። በጎንደር በኩል የተንቀሳቀሰው የደቡብ ዕዝ መሆኑን ስታይ ደግሞ መሃል ሃገር የሆነ ድግስ እንዳለ ይሰማኛል። እናም ዐማራ ሁሉም ተኳሽ ሁሉም ቀዳሽ ባይሆን እመርጣለሁ። ቀዳሾችም ተኳሾችም በልክ በመጠኑ ቢሆኑ እመርጣለሁ። ራብ የሚባል ነገር አለና መሬቱም ጦም እንዳያድር ማለቴ ነው። ወታደር እየቀለብክ ጎተራህን ካሳሳህ በኋላ በኋላ እዬዬ ብትል ሰሚ እንደሌለህ እወቅ።
•••
ቤኒሻንጉል የሚገኘው የጎጃም አገው ዐማራ በጉምዝ ቀስተኞችና በዐቢይ ሽመልስ የኦነግ ሸኔ ጦር መሞቱም አልቀረለትም። የጎጃም ሰው ሬሳ መቁጠር እንጂ ምላሽ ለመስጠትም አልደፈረም። እና ይሄ በቤኒሻንጉል በኩል ሰፍ ብሎ የሚጠብቀው የአባ ጋዳይ ሠራዊት ነገር ዓለሙን ረስቶ ብር በመቁጠር ስለ ቢዝነስ፣ ስለ ንግድ ብቻ በማንሰላሰል ላይ የተቸከለውን የጎጃም ዐማራ ይምረዋል ብዬም አልጠብቅም። በላይ ዘለቀ ቂልጡ ኬኛ፣ ጎጃም ኬኛ ሲል የከረመው ቄሮ አይንህ እያየ እንዳያናፍጥህ በተጠንቀቅ ደጃፍህን ብታጠባብቅ መልካም ነው ባይ ነኝ።
•••
የዐቢይ አባ ገዳይ ኦነግ ሸኔ የዐባይ ሸለቆን ተከትሎ ጎጃምና ሰሜን ሸዋ ከከተመ ቆየ። አሁን እንዲያውም ይሄ የሰሜነኞቹ የሴማውያን ጦርነት ሁለቱንም ሰሜነኞች በደንብ እንክትክት እሲኪያደርጋቸው ነው የሚጠብቀው እየተባለ ነው። ኦህዴድና አሽከሩ ብአዴን ዐማራውን ከአሁኑ ነፍጥ አውርድ እያሉትም ነው አሉ። ይሄ ማለት ሸዋ ለዐራጁ በርህን ከፍተህ ጠብቅ ማለትም ነው። እናም ዐማራ ብትጠነቀቅ፣ እንደ እባብ ብልህ፣ እንደ ርግብ የዋሕ ብትሆን መልካም ነው ባይ ነኝ። ግድየለም እንደማመጥ። በውስጥም ላይ አተኩሩ።
•••
ከጦርነቱ መልስ ወልቃይትን ልቀቅ ላለመባልህ ምን ዋስትና አለህ? ጠገዴን ራያንስ ልቀቅ ላለመባልህ ምን ዋስትና አለህ? እናም ከአሁኑ ፈር እያስያዝከው ሳትሄድ በባዶ ሜዳ አመድ አፋሽ እንዳትሆን ከስሜት ወደ ስሌት ብትመለስ መልካም ነው ባይ ነኝ። ብአዴን እንደሁ ዛሬ ባለ ሾርት ሚሞሪዉን ሁላ ኮርኩሮ እየነዳ ካሸነፍክ በኋላ ወደ ኋላ ዙሩ እንደማይላችሁ ማረጋገጫ የላችሁም። እናም በጥበብ ብትመላለሱ መልካም ነው። ለሃገር መከላከያ ሠራዊቱ ከደም ልገሳ እስከ ቀለብ ብትሠፍሩለት አይቆጭም። ነገር ግን በጥበብ አድርጉት። የትአለ መከላከያው? እስከ አሁን የዐማራን ግዛቶች እያስለቀቀ ያለው ፋኖና ልዩ ኃይሉ ነው። ስንቅ፣ ጉልበት፣ ኃይል በጎንደር ፋኖ ላይ ብቻ ነው የወደቀው። ራያም እንዲሁ። እናም ዙሪያ ገባችሁንም አማትሩ።
•••
ከልጅነቱ ጀምሮ የአያትህን ጡት የቆረጠው ዐማራ ነው ብሎ የሚያስተምረው አባ ገዳይ ሽመልስ ቁማሩን አሁንም በደንብ ላለመጫወቱ ምን ማረጋገጫ አለን። ቦለጢቃ ማለት ቁማር ነው ነበር ያለው አይደል? ዓባይን ተሻግሮ ግማሹን ኮንፊዩዝድ፣ ገሚሱን ኮንቪንዝስ አድርጎ እንደነበር የነገረን ሽሜ አሁን ደግሞ ከተከዜ ማዶ ምን ዓይነት ቁማር አስቦ ይሆን? የሰሜን ዕዝስ ከምር ተማርኳል? አልገብቶኝም።
•••
በተረፈ መጪው ጊዜ ለሁላችንም ከባድ ነው። የርስ በርስ ጦርነቱ ከደጃችን ነው። ጦርነቱን ተከትሎ የሚመጣው ማኅበራዊ ምስቅልቅልም ሌላኛው ጣጣ ነው። በሽታ ወረርሽኝም ከጦርነት መልስ አጃቢዎቻችን ናቸው። አንበጣው እህሉን ሰብሉን ጨርሶታል። አሁን የግሪሳ ወፍ ተተክቷል። ንስሐ መግባት አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው። አሁንም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አልቻልንም። እሱ ነገር ላይ አንስነፍ እንበርታ።
•••
በመስከረም 5 ቀን ዘንድሮ ከወር በፊት በተዘጋው የዩቲዩቤ የነገርኳችሁ የበረኸኞች የትንቢት ቃል አንዳችም ሳይቀር ሙሉ በሙሉ እየተፈጸመ እንደሆነ ግልጽ ነው። ስሙን መጥቀስ ያልፈለኩት የአንድ ብሔር አባላት ምነው ከዚያ ብሔር ባልተወለድኩ የሚሉበት ዘመንም ይመጣል የተባለው ዋዜማ ላይ መሆናችንንም እዩ። ተመልከቱም። አሁን በየሰፈራችሁ ከሥራም፣ ከደሞዝም እየተቀነሱ ያሉ ወገኖችንም አስቡ። ዐማራን በማንነቱ፣ ትግሬን ደግሞ ከጦርነቱ ጋር አስታከው ኦሮሞዎቹ በጥበብ እያስወገዷችሁ፣ እያጸዷችሁ እንደሆነም እያያችሁ ነው። ተዉ ተዉ ብንል አልሰማ ያለው የህወሓት ካድሬ ሁላ ለእሱ የመጣው ጦስ ለንፁሐኑም እየተረፈ ነው። ብዙ የሚራብ የሚጎዳ ዜጋ ገና ወደፊት አለ። ይኖራልም። ህዳርና ታህሳስ ደግሞ ከዚህ የባሰ ይከፋል። ራብ ብዙ ሰው ይቀጣል። እህልና የእህል ዋጋ ከወዲሁ እየናረ ነው። አስጨናቂ ነገር በዝቷል። የርስ በእርስ ጦርነቱ ሲበዛ በሰላም አስከባሪ ሰበብ የሩቁም፣ የቅርቡም ሃገራት እንግባ ማለታቸው አይቀርም። እንግዲህ መዘጋጀት ለዚያን ጊዜ ነው። እናም ኃይል አታባክኑ።
•••
ቅዳሴ ማስቀደስ መቀደስ እንዳማረን ከቀረ ሰነባበተ። ተዘዋውሮ መነገድ፣ ትምህርት ብሎ ተዘዋውሮ መማር፣ ተዘዋውሮ መሥራትንም አትስቧት። በቶሎ የሚሆን አይመስልም። ብሩ ቢኖርህስ ምርቱ ከሌለ ምን ታደርግበታለህ? ጨውና የማይነቅዝ እህል ሸሽጉ፣ ወደ መትረፊያ ገዳማትም ላኩ የተባለውንም አትርሱ። እናም ባለ ማዕተብ የምታባንን ከሆነ ባን አልያም እንደ ፍጥርጥርህ።
•••
የቀረችው ቤተ እመነቷ ናት። ቤተ ክህነቱንም ለማፈራረስ ይኸው የቤተ ክህነቶቹ ወጣት የብልጽግና ሰዎች በሰፊው ወጥረው ይዘዋል። የፓትርያርኩ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፕሮቶኮልና የግል ጠባቂዎችም በትግሬነታቸው ተለይተው ታስረዋል ተብሏል። አሁን ባለጊዜን ምክር አያቆመውም። ቀጣዩ ደግሞ ፓትርያርኩን ከራሩላቸው ወደ ገዳም ከጨከኑባቸው ደግሞ አንቀውም ቢሆን መርዘውም ይገድሏቸዋል የሚል ስጋት ነው ያለኝ። የእነ ዶክተር ዘሪሁን ሙላት ከመሬት ድንገት ተነሥተው የዐቢይ ደጋፊ መሆንና በእልህ፣ በስሜትና በቀል የተሞላበት ጦማርም የሚያሳያው ነገር ቢኖርም የሆነ የታቀደ ነገር መኖሩን ነው። ጠረኑ ደስ አይልም። ወንድሜ ዘሪሁን ሙላትን የሚመክረው ሰው ማጣቱም በብዙ ይቆጨኛል። አዎ ዘሪሁን ሙላት በዘመነ ህወሓት በግል፣ ሌላው ደግሞ እንደ ሃገር ተበድልናል። ነገር ግን ቂመኛ መሆን ከአንተ አይጠበቅም። እናም ወላፈኑ ማንንም ስለማይምር እንደወንድምነቴ የምመክርህ ነገር ቢኖር የብዕር ሰይፍህን ከፓትርያርኩ ላይ አንሳና ቢቻልህ ልትቀበር አንድ ጀንበር የቀራት ህወሓት ላይ ወጥር። ፎክርም። ከህወሓት ሰዎች ከትግሬዎችም ብዙ የአንተ ወዳጆች እንደነበሩም አትዘንጋ በሉልኝ። በአንተ ብዕር የተነሣ ቅዱስ ፓትርያርኩ አንዳች ነገር ቢደርስባቸው፣ አይደለም ተገድለው፣ በተፈጥሮ ሞት ቢሞቱ እንኳ ከዚህ አጀንዳ ጋር ስማችሁ ለተያያዘው አካላት መልካም ዘመን የሚገጥማችሁ አይመስለኝም። እናም ተረጋጉ።
•••
የውጪው ሲኖዶስ አባላት ከድሮ ጀምሮ እቅዳቸው የታወቀ ነው። ወያኔን ከጣሉ በኋላ የወያኔ ነው የሚሉትን ማስወገድ የቆየ ዕቅዳቸው እንደነበረም ይታወቃል። እነሱን ተጠግተው በምንፍቅና ቤተ ክርስቲያኒቱን የወጉትንም ታስታውሳላችሁ። ትግሬን በዐማራ መተካቱ ላይ ባትጣደፉም መልካም ነው። ደግሞም ቋመጣችሁበት እንጂ አሁን ዘመኑ የኦሮሞ ስለሆነ የኦሮሞ ፓትርያርክ ያስፈልገናል የሚሉት አካላት በሙሉ አቡነ ማትያስን አስወግደው አቡነ መርቆሬዎስን ለደቂቃ እንደማያቆዩአቸውም ማወቅ ቢኖርባችሁ መልካም ነው። ተረኛው ቤተ ክርስቲያኒቱን ካላፈራረሰ በቀር እንደማይተኛም እንረዳ። እንወቅም። የምትፈሩት ሙስና የአስተሳሰብና የአስተዳደር ለውጥ ካልመጣ በቀር የሰማይ መልአክ መጥቶ አሁን ያለውን የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቢመራው እንኳ የሚለውጥ የለም። እንኳን አሁን ፈረንኳ ማግኘት ውድ እየሆነ በመጣበት ጊዜ ይቅርና፣ ምእመናን እጃቸው ባጠረበት ጊዜ ይቅርና ድሮም ገንዘብ መጫወቻ በነበረበት ጊዜም ቢሆን ጻድቅ የበቃ እንኳ መጥቶ ቤተ ክርስቲያኑን ቢመራው አይስተካከልም ነበር። እናም የቤተ ክህነቱ ብልጥግናዎች አረፍ፣ ቀዝቀዝም በሉ።
•••
እናም ኦጎኖቼ … ያው እንደተለመደው በተለመደው ሰዓት፣ በተለመደው መልኩ፣ ሰንዳ ሰንዳ፣ ሰብሰብ፣ ሰብሰብ ብላችሁ ከቤተሰብ ከጓደኞቻችሁም ጋር ሆናችሁ
Filed in: Amharic