>

አርበኛ እና ባንዳ ...!!!

አርበኛ እና ባንዳ …!!!

በመምህር  ዘመድኩን በቀለ

አርበኛ ማለት ገና ከመጀመሪያው ሲፈጠር ጀምሮ ቀድሞውኑ ዘወትር አሸናፊ እንዲሆን፣ ጀግና የጀግና ልጅ እንዲሆን፣ ለትውልድ እንደጧፍ እያበራ እሱ እንዲቀልጥ ተደርጎ የተፈጠረ ፍጥረት ማለት ነው። አርበኛ ከሩቅ በጠረኑ ያስታውቃል። በድምጹም ይለያል። መልኩ ግርማ ሞገሱ ያስደነግጣል። እንደ ባንዳ ቀትረ ቀላል፣ ሥጋ ቅብ፣ መንፈሰ ኮስማና፣ ሽምቅቅ ያለ፣ ጥላቢስ አይደለም። አርበኛ በቃ አርበኛ ነው። አከተመ።
ባንዳ ማለት የሃገር ሸክም፣ የሃገር ዕዳ ማለት ነው። ባንዳ ከሃዲም ነው፣ ቅጥረኛም ነው። የእናት ጡት ነካሽም ነው። ባንዳ ማለት የጠላት መንገድ መሪ፣ ለጠላት እንቁላል ቀቃይ፣ ስንቅም አቅራቢ ነው። ባንዳ ማለት ራስ ወዳድ እኔ ከሞትኮ ሰርዶ አይብቀል ባይ ሴት ልጁን፣ እናትና ሚስቱን እህቱን ሃገሩንም ጭምር ዓይኑን ሳያሽ ለጠላት በሽያጭም በኪራይም አቅራቢ ፍጥረት ነው። ባንዳ ማለት ረጃጅም ምላስ፣ ትንንሽ ጭንቅላት፣ ሰፋፊ ሆድ ያለው ፍጥረት ነው። ውሸታም  !!
•••
ታዲያ ሁለቱም ልጆችም ዘርም አላቸው። የአርበኛ እና የባንዳ ልጆች። ዘር አላቸው። በደም የሚተላለፍ፣ የሚዋረስ፣ ከትውልድ ትውልድ የሚንከባለል ማንነት አላቸው። በህክምናም በአዋቂም የማይፈወስ ማንነት አላቸው። ባንዳ ባንዳ ነው። ልጁም፣ የልጅ ልጁም ያው እንደ አያት ቅድመ አያቱ ባንዳ ነው። ጳጳስ ያስረሽናል፣ ካህን ሼኪ ያሳርዳል፣ ወገኖቹን በጅምላ ይፈጃል። ባንዳ እጅግ ሲበዛ ክፉ፣ ጨካኝ፣ አረመኔም ጭምር ነው።
•••
ባንዳ ለስብሰባ ይጠራሃል። ወንድሜ እህቴ እያለ ሲጋብዝህ ያመሻል። አንተ ደክሞህ ስትተኛ በተኛህበት ይረሽንሃል፣ ያርድሃል። ምክንያቱም ባንዳ ነዋ፣ ከሃዲ የከሃዲ ልጅ ነዋ። ባንዳ ቀሚ ነው፣ ገፋፊ፣ ራቁትህን የሚያስቀር፣ ባንዳ ወንበዴ ነው። እልም ያለ ማፍያ። ባንዳ ዘማዊ ነው፣ ርኩስ ነው። ቀሚስ ያየበት፣ ሱሪ ቀበቶ ባየችበት የሚልከሰከስ ፍጥረት ነው። ባንዳ አያርስም፣ አይዘራም፣ አይኮተኩትም፣ አይወቃም፣ ወደ ጎተራም አያስገባም። የተጋገረ እንጀራ፣ የደረሰ፣ ያለቀለት ቀምቶ የሚበላ ገፋፊ ነው። በዚህ ግብሩ ባንዳ ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ክፍለ ከተማ፣ ዞንና ክልል፣ ሃገር ሲመራ አስቡት። ባንዳ ሃገር ሲመራ። ባንዳን አምነን ሃገርን ያህል ውድ ነገር ምራ አስተዳድር ብለን የሰጠነው ዕለት እኮ ነው ነገር ዓለሙ ያበቃው።
•••
ባንዳ አሁንም አለ። ባንዳነቱን እያወጀ እየተንጎማለለ። ለጠላት ሃገር፣ ለጠላት ጦር ሲሰልል የኖረ። ባንዳ የባንዳ ልጅ አለ። አለ ባንዳ ካናት ከቁንጮው ላይ የተገሸረ። የባንዳ መድኃኒቱ አርበኛ ብቻ ነው። አርበኛው ሰምተሃል። ያንንም ይሄንንም በቀጠሮ፣ በተራ አነጋግረው። ይኸው ነው።
• የአርበኛ ልጆች ደህና ዋሉልኝ  !!
ቀደም ሲል ተጽፎ የነበረ
Filed in: Amharic