ከጦርነቱ ብኋላ ምን ሊሆን ይችላል?
ሸንቁጥ አየለ
ስልጣን አጋሩኝ ለማለት የሚፈራዉ ብአዴን
———————-
ስልጣን አጋሩኝ ለማለት የሚፈራዉ ብአዴን የአማራን ወጣት ካስፈጀ ብኋላ የኦህዴድ/ኦነግ ሀይል በኢትዮጵያ ላይ ሙሉ ለሙሉ ያነግሰዋል::አማራም መታረዱን መሳደዱን: በ አረመኔዎቹ ኦህዴድ/ኦነግ አንዴ በማጅሩ አንዴ በአንገቱ መታረዱን ይቀጥላል::ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን አማራን አርደዉ አይተዉተዉትም:: ደሙን እጃቸዉን ይታጠቡበታል ለጣኦት ይሰዉታል::
ስልጣን አጋሩኝ ለማለት የሚፈራዉ ብአዴን ፋኖ ወያኔን አባሮ ስልጣን እጁ ላይ ቢያስገባለት ስልጣኑን ሁሉ ወስዶ ለኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን አስረከበ::
አሜሪካ የገዱ ቲም የመጣ ጊዜ በዉጭ የሚኖሩ ጉጉ አማራዎች እነ ገዱን ጥያቄ ጠዬቁት ” ስልጣን ከኦህዴድ/ኦነግ ጋር ትጋራላችሁ?” ሲሉ::ኦህዴድ የሰዎች ስብስብ መስሏቸዉ::
ገዱ እየተሽኮረመመ “እኛ ስልጣኑ አያሳስበንም::ስልጣን አንፈልግም” ብሎ ቁጭ::
-ከዚያ ብ አዴን ሆይ ሄዶ ፋኖ ላይ ከኦህዴድ/ኦነግ : እንዲሁም ከብርሃኑ ነጋ ኢዜማ ጋር ሆኖ ፕሮፖጋናዳ ከፈተ::” ፋኖ የሚባል አያስፈልግም:: የታጠቀ አያስፈልግም:: ፋኖ አክራሪ ነዉ::መጥፋት አለበት” የሚል ፕሮፖጋንዳ በደንብ ተጧጧፈ::እንዳሉትም ፋኖን ማሰር:በጅምላ መግደል:ማሳደድ: መወንጀል እና ማሸማቀቅ ያዙ::
–አሁንም ከዚህ ዉጊያ ብኋላ የሚሆነዉ የሚከተለዉ ነዉ::
1. ብአዴን ስልጣን አጋሩኝ ብሎ የኦህዴድ/ኦነግ ጌቶቹን አይጠይቅም::ቢጠይቅም ስልጣን አያቀምሱትም::እንዲያዉም ስልጣን አጋሩን የሚል የብአዴን ባለስልጣን ከተገኘ እንደ አሳምነዉ ኦህዴዳዉያን የሆነ ሰበብ ፈጥረዉ ይገሉታል::ወይም እርስ በርስ ተገዳደሉ ብለዉ እራሳቸዉ ያጠፏቸዋል::ይሄም የሚሆነዉ ብ አዴኝ ውስጥ ያሉ ሰዎች የአማራ ህዝብ ሞት የማያሳስባቸዉ ኢትዮጵያን ለመምራት ወኔ ቢስ ስለሆኑ እና የሚራወጡትም ለጊዜአዊ ሆዳቸዉ ስለሆነ ተምምነዉ የሚሰሩት ሚስጢር ስለሌለ ነዉ
2. የክልሉን አብዛኛዉን ወጣት እና ፋኖን በዚህ ጦርነት ይማግዱታል::የቦንብ ማምከኛም ያደርጉታል::
3.ኦህዴድ/ኦነግ የራሱን ወታደር ማሰልጠኑን አጠናክሮ ይቀጥላል::ከሚያሰለጥነዉ ወታደርም አንድ አስረኛዉ እንኳን ወደ ጦርነቱ ግንባር አይገባም::
4.ከጦርነቱ ብኋላ የኦነግ/ኦህዴድ እብሪት ይበልጥ አብጦ እና ፈርጥሞ ይወጣል::የሽመልስ አብዲሳንም አማራን ፈጽሞ የማጥፋት እቅድ በስፋት ተግባራዊ ያደርጋሉ::
5. ዛሬ ይሄን ጦርነት ደግፈዉ የአማራን ወጣት በዚህ ጦርነት በማሰለፍ ሂደት ዉስጥ የተሳተፉ ተቃዋሚዎችም ጥያቋ መጠዬቅ ሲጀምሩ ተሰብስበዉ ልክ እንደ እንደ ሰላማዊዉ ታጋይ እስክንድር ነጋ ወደ እስር ቤት ይጣላሉ::
6.ጦርነቱ ሙሉ ለሚሉ በኦህዴድ/ኦነግ የበላይነት ባይደመደም እንኳን ወያኔ እና ኦህዴድ/ኦነግ በድኑን ብአዴንን ያገለለ የተናጠል ስምምነት ያደርጋሉ::ከላይ የተባሉት ነጥቦችም በዚህኛዉ ሁኔታ ይፈጸማሉ::
——————
እና መፍትሄዉ ምንድን ነዉ?
—————-
ብአዴን ልብ ካበጀ መፍትሄዉ እራሱን በፍጥነት ከኦህዴድ/ኦነግ ማፋታት::የራሱን ሰራዊት እራሱ ማደራጀት::ከኦህዴድ/ኦነግ እዝ ስር በፍጹም አለመግባት::መዋጋት ካለበትም በራሱ ቀመር እና በራሱ ስትራቴጂ ብቻ መዋጋት::ብአዴንነራሲን ከኦህዴን/ኦነግ ካፋታና የራሱን ሰራዊት ማደራጀት : መምራት: ማሰልጠን እና ማዋጋት ከቻለ በአስተማማኝነት ከጦርነቱ ብኋላ የአማራ ህዝብን ህይወት የሚታደግ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት በርግጠኝነት የሚያስጠብቅ ሀይል ሆኖ ይወጣል::
ሆኖም ብአዴን ይሄን አያደርግም::ብ አዴን እራሱን በኦህዴድ/ኦነግ ባርነት ቀንበር ዉስጠ አስገብቶ የሚቀጥል ሙት ሀይል ስለሆነ ከጦርነቱ ብኋላ የሚሆነዉ ከ;አይ ከ1-6 የተጠቀሰዉ ነዉ::
ሌላ ሶስተኛ አማራጭስ አለ?
———————-
ሌላ ሶስተኛ አማራጭ ነበረ::ነገሩ ነበረ ነዉ::ግን የአማራ ህዝብ ተቃዋሚ የሚላቸዉ ሀይሎች ሶስተኛዉን አማራጭ አክሽፈዉታል::አሁን አማራዉ እዉነት መስሎት ሙሉ ለሙሉ ልቡን ከኦህደድ/ኦነግ ሀይል ጋር እንዲያሰልፍ ተቃዋሚዎች ሳይቀሩ ሶስተኛዉ አማራጭን ደፍሮ ሊተገብረዉ የሚሞክር አይኖርም:: ስለዚህ እሱን አማራጭ እዚህ መተንተኑ ዋጋ የለዉም::
———————-
የእግዜር ጣት ነገር
——————-
ፖለቲካ ዉስጥ የእግዚአብሄርን ነገር አስገብቼ ስተነትን አለማያ ዩኒቨርስቲ ሳለን ሲ-ባሌ የምንለዉ ጓደኛችን የሚተርበኝ ትረባ ነዉ ትዝ የሚለኝ:: ነገሩ እንዲህ ነዉ:: እዶርም ዉስጥ እኔ ጫት ከማይቅሙት ልጆች አንዱ ነበርኩ::ጫት እንኳን ልቅመዉ ገና ሲሸተኝ ያስጠላኛል::ያቅለሸልሸኛል::ጫት የሚቅሙ ልጆች አንዱ የሚገርመኝ ባህሪያቸዉ እሚመቻቸዉ አልጋ ላይ ሰብሰብ ብለዉ የደራ ወሬ እያሞቁ አለምን በሙሉ በቁጥጥራቸዉ ስር ያደርጉታል::
ስለዚህ አልጋዬ ላይ ሰፍረዉ ጫት እንዳይቅሙበት ማድረግ ነበረብኝ:: እናም አልጋዬን በደንብ አድርጌ አነጥፍና ትልቁን ሰማኒያ አንዱን መጽሃፍ ቅዱስ አልጋዬ መሃል ለመሃል አስቀምጠዋለሁ::ከዚያም ለያንዳንዱ ልጅ እኔ አልጋ ላይ ጫት መቃም እንደማይችልም ጮክ ብዬ እናገራለሁ::እናም ማንም እዚያች አልጋላይ ጫት አይቅምባትም::ከእኔ ንግግር በላይ ግን የሚገታቸዉ መጽሃፍ ቅዱሱ አልጋዉ ላይ መቀመጡ እንደሆነም አዉቃለሁ::እናም ሲ-ባሌ የሚባለዉ ተራቢ ሁል ቀን እየሳቀ ተረቡን ያወርድብኛል:: ከተረቡ ሁሉ ግን የሚገርመኝ አልጋዉ ላይ የተቀመጠዉን መጽሃፍ ቅዱስ እያዬ “የሸንቁጥ አለጋ የራሱ እግዜር አለዉ” የሚለዉ ነገር ነዉ::
የእግዜርን ነገር ፖለቲካ ዉስጥ አምጥቼ ስተነትን የምትናደዱብኝ ሰዎች ለተረብ እንዲመቻችሁ ከላይ ያለዉን ታሪክ አቀበልኳችሁ::
እናም ወደ እግዜር ጣት ነገር ስመለስ ኢትዮጵያ እግዜር አላት::እግዚአብሄርም የኢትዮጵያ ክፉዎችን ጠርጎ እርስ በርሳቸዉ አባልቶ የሚያጠፋበት ቀን አሁን ነዉ ብዬ አምናለሁ::ማንም ሀይል ኖሮት ሳይሆን በእግዚአብሄር ፈቃድዲትዮጵያን የሚታደግ መልካም ሀይልም ይነሳል:: ከኢትዮጵያም የጎሳ ፖለቲካን ያጠፋል::የተበታተነዉን የኢትዮጵያን ህዝብም ከረከሰዉ የነገድ እና የብሄር ፖለቲካም ይታደገዋል::
በኢትዮጵያ ምድርም ተሳዳጅ እና አሳዳጅ:መጤ እና ነዋሪ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰዉ እንዲኖር ይሆናል::ይሄ የሚሆነዉ በእግዜር ጣት ነዉ:: ይሄ እምነት ነዉና ከዚህ በላይ ትንታኔ አያስፈልገዉም::ግን የምተነትነዉ መንፈሳዊ መረጃ ስለሌለኝ ሳይሆን ካመንክ ይሄ ብቻ በቂ ስለሆነ ነዉ::ካላመንክ ደግሞ አንድ መጽሀፍ ትንታኔም አያሳምንህም::
ለማንኛዉም ልክ ሲ-ባሌ ስተቸኝ እንደነበረዉ “የሸንቁጥ ኢትዮጵያ የራሷ እግዜር አላት” ብላችሁ መሳለቅም መብታችሁ ነዉ::ኢትዮጵያን ግን የሚታደጋት አምላክ እንዳለ ምንም የማይዛነፍ እምነት አለኝ::
አሜን እንደምነቴ ያድርገዉ::እንደ እኔ የምታምኑ ኢትዮጵያዉያንም አብራችሁኝ አሜን በሉ::
ኢትዮጵያዊ ልጄ ነዉ ያለዉ የእግዚአብሄር ቃል ዘላለማዊ እንደሆነም እመኑበት::የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ ብሎ ለማመን ግን ጀግንነት ይጠይቃል አይደል?
ለማስታወስ ያህል እግዚአብሄር ኢትዮጵያዊ ልጄ ነዉ ሲል ክርስቲያን እስላም ኢ አማኝ ወይም አይሁድ አላለም እና ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ ይሄን እንድታዉቀው ይሁን::ለነገሩ አልሰማሁም ልትል አትችልም::ልብህን ካላከበድህ በቀር::