>

"ሕወሓት ላይ የሚደረገው ጦርነት የወንድማማች ጦርነት ሳይሆን ፍትሐዊ የሆነ ጦርነት/Just War  ነው!!!" (አቻምየለህ ታምሩ)

ሕወሓት ላይ የሚደረገው ጦርነት የወንድማማች ጦርነት ሳይሆን ፍትሐዊ የሆነ ጦርነት/Just War  ነው!!!”

 
አቻምየለህ ታምሩ

 

ሕወሓት የሚባለው ለወንጀል የተቋቋመ ድርጅት  የኢትዮጵያ ካንሰር ነው። ማንም ያድርገው ይህን የኢትዮጵያ ካንሰር ለማስወገድ የሚደረግ ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነው።  እኔ ሕወሓት የተባለውን የኢትዮጵያ ነቀርሳ ለማስወገድ የሚያደረገውን ተጋድሎ የወንድማማቾች ጦርነት አድርጌ የምወስድ ነሆለል አይደለሁም። ሕወሓት ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለውን፤ በተለይም ደግሞ የአማራ ተወላጅነት ያለውን ሁሉ ሳይበድለው ጠላት በማድረግ  ለማጥፋት  የተቋቋሙ የወንጀል ድርጅት ነው። አንድን ሰው ወንድም የሚያደርገው ተግባሩ ነው። በሕወሓትና በሙሶሎኒው ፋሽስት ፓርቲ ሰዎች መካከል ከቆዳ ቀለም በስተቀር ምንም አይነት ልዩነት የለም። በመሆኑም አቅምና ጉልበቱን ሁሉ ሳይቆጥብ ለክፉ ተግባር ያዋለው፤ በእምነትና በቅን መንፈስ ተገፋፍቶ ያለፋቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙለት፤ በትምህርት ተወልደው መልካም የሚሰሩና ለወገናቸው የሚያስቡ ሰዎችን በማጥፋት ክብረወሰን የተቀዳጀው፤ ድሀ ዘራፊ፣ ገፋፊና ለወንጀል የተቋቋመው ሕወሓት የሚባለውን የኢትዮጵያ ነቀርሳ ከነአስተሳሰብ ሰንኮፉ እንዲነቀል የሚደረግ ጦርነት የወንድማማቾች ጦርነት ሳይሆን ፍትሐዊ የሆነ ጦርነት ወይም ፈረንጆች Just War የሚሉት አይነት ጦርነት ነው።
Filed in: Amharic