>

የደብረፂዮን ልመና፣ የጌታቸው ተቃርኖ! (አርአያ ተስፋ ማርያም)

የደብረፂዮን ልመና፣ የጌታቸው ተቃርኖ!

አርአያ ተስፋ ማርያም

የትግራይ ክልል ፕ/ት የሆኑት ደብረፂዮን ለመንግስት የድርድር ተማፅኖ ጥያቄ ማቅረባቸው ታውቋል። ባለፈው ሰኞ ምሽት በትግራይ ለሃያ አመት በኖረው መከላከያ ሰራዊት ላይ አስነዋሪ ዘመቻ በማድረግ ጥቃት የሰነዘሩት መቀሌ የመሸጉት የስብሃት ቡድን ጥገኛ የሆኑት ሁለተኛው ቡድን አስፈፃሚ ደብረፂዮን በተማፅኗቸው እንዳሉት “ፖለቲካዊ ችግሮች በወታደራዊ አማራጮች እንደማይፈቱ ፅኑ እምነት አለኝ” ካሉ በኃላ አያይዘውም “ጦርነቱ ቆሞ ድርድር እንዲደረግ እማፀናለሁ” ማለታቸውን ሮይተርስን ጠቅሶ BBC ዘግቧል። በነ ስብሃት የሚታዘዘው የደብረፂዮን ቡድን ይህን ቢልም ባለፈው ሳምንት “እናሳያቸዋለን፣ እንደመስሳለን” እያለ ሲፎክርና ሲሸልል እንደነበር ይታወሳል። ጌታቸው ረዳ የተባለ የነ ስብሃት ሎሌ በበኩሉ የደብረፂዮንን ተማፅኖ ልመና የሚፃረር መግለጫ ተብዬ ሲዘላብድ እየታየ ነው። በሁለቱ ቡድን ያለውን ልዩነት ግልፅ አድርጎ የሚያሳይ ነው! ደብረፂዮን የትግራይ ተወላጁን በማነሳሳት፣ ከነ ስብሃት ትእዛዝ ተቀብለው በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከፈፀሙ በኃላ ቅርቃር ውስጥ እንደገቡ ሲያውቁ አሁን የሚያቀርቡት ልመናና ድርድር ተቀባይነት የለውም! ሲረገጥ የኖረው የትግራይ ህዝብ ከእነሱ ነፃ የሚወጣበት ጊዜ አሁን ነው! አምስት አካባቢዎች በመከላከያ ቁጥጥር ስር ሲውሉ በአንፃሩ “ለነ ስብሃት አንሞትም” ብለው እጅ የሰጡ በርካታ ሚሊሻዋች በቅርብ ቀናት በሚዲያ እንደሚቀርቡ ከቅርብ ታማኝ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። ኦፕሬሽኑ በቅርብ እልባት ያገኛል! አራት ነጥብ!!
Filed in: Amharic