ጦርነቱ ተከፍቶአል፤ የእኛ ድርሻ ምንድነዉ?
ሃራ አብዲ- ካለፈዉ የቀጠለ
…«ከዚህ ዉጥንቅጡ ከወጣ የዉርደት እሽክርክሪት እንዴት ነዉ የምንወጣዉ» ብለን ነበር የተለያየነዉ።
ለዛሬ አንዳንድ ነጥቦችን አንስተን እንድንወያይ ይረዳ ዘንድ ብቅ ብያለሁ።
ይህ ጽሁፍ ወያኔ በይፋ ጦርነት አዉጃብን ሳለ እንደአዘቦቱ ቀን ሁላ መንግስትን መቃወምና በነገር መተክተኩ መብዛቱን ተከትሎ «ሃይ» ለማለት የተቃጣ ነዉ።
በረኪና የበላዉን ኩታ በአራቱም ማእዘናት ስንጓተት ፤ ኩታዉ ተቦጫጭቆ ጎታቾቹ አይወድቁ መዉደቃችን ላይቀር ነዉ። (ofcourse Nothing will happen to those contributing to the proxy war from abroad). ማንን ?መቼ?ለምን? እንቃወም የሚሉት ጥያቄዎች መመለስ ያለባቸዉ የሚያስከትሉት በጎም ሆነ መጥፎ ዉጤት ከግምት ገብቶ መሆን አለበት።
መጀመርታ ስለ ትግራይ ፖለቲከኞች እንነጋገር፤
የወያኔ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ የወያኔ ከፍተኛ ተቃዋሚዎች የነበሩ፤ ወያኔ ወንጀለኛ ድርጅት ነዉ ሲሉ የተደመጡ፣ አንዳንዶቹም ወያኔ በጥጋብ ዘመንዋ በካልቾ ጠልዛ በቡጢ ፐዉዛ ዘብጥያ ያወረደቻቸዉና ከስልጣንም ያባረረቻቸዉ የትግራይ ተወላጆች ልቅምቅም ብለዉ ከወያኔ ጋራ ወግነዋል። ይህን ባናደርግ ባንድ ገበታ የተባጠቅነዉ አምባሻና ድቁስ ይነቀን ብለዉ ጎራቸዉን ለይተዋል። ከዘመድ ጋር የበሉት በሶ መሆኑ ነዉ።ወያኔ በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ምን አይነት ክህደት እንደፈጸመችበት እያወቁ እነርሱ ወገናዊነታቸዉን ለጦር ወንጀለኛዉ የሚያሳዩ ከሆነ፤እኛ ኢትዮጵያዉያን መቼ ነዉ ይህ ምስጢር የሚገለጽልን?
በዚህ አያበቃም፤
የቀድሞ የዉስጥ አፓርታይድ አራማጆች፤ የአሁኑ የጦር ወንጀለኞችና ሰራዊታቸዉ፤ የነፍሰ-ገዳዩ ኦነግ አመራርና የሽብር ሽምቅ ተዋጊዎቹ፤ሰላማዊ ነኝ የሚለዉና የቀበሮ ለምድ ለብሶ ከበጎቹ መሃል የተደባለቀዉ የመሀል ሀገሩ ኦነግ፤ እንዲሁም በብልጽግናና በመንግስት መዋቅር ዉስጥ ተሰግስገዉ ከዉስጥ classified information የማቀበል እና ከለላ የመስጠት ስራ የሚሰሩ ጥቂት የማይባሉ የኦሮሞ ተወላጅ ባለስልጣናት በአንድነት ወግነዉ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት፤የአማራ ልዩ ሀይልና ፖሊስን ጨፍጭፈዋል። እንዲሁም ባዶ እጃቸዉን የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎችን ያለአንዳች ልዩነት በጅምላ ገድለዋል።
አብላጫዉ የኦሮምያ ልዩ ሃይልም እድሉን ቢያገኝ የሚጠላዉ አይደለም።
ዋናዉ ነጥቤ፤ጦርነት በመሳሪያ የሞት ሽረት ትግል የመሆኑን ያህል የፖለቲካና የአስተሳሰብ ፍጭትም ነዉና የሰራዊታችንን ሞራል በመገንባት እንዴት ይህን ጦርነት በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ እናድርግ ነዉ ። ጦርነቱ በድል ሲጠናቀቅ፤ በመንግስት የአመራር ስህተትም ሆነ በማንኛዉም ብልሽት ሀገራችን እዚህ ዉድቀት ላይ መድረስዋን አስመልክቶ ለመወያየት ፣ለመወቃቀስና ሃላፊነቱ የሚመለከታቸዉን መንግስትንም ሆነ ማንኛዉንም አካል ተጠያቂ ለማድረግ የማንችልበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
Let us not die on every hill!
የጠቅላይ ሚኒስትር አመራር እስከዛሬ ወያኔን…
(I hear you all…) እኔም የምለዉ አለኝ። እስኪ ጦርነቱ ያብቃ።
ለአሁኑ፤ የቱንም ያህል ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራር ጋር ባይስማሙ የዚህን ጦርነት ምንነት በሚገባ ተረድተዉ ጦርነቱ ህጋዊ ጦርነት ነዉ ፤ኢትዮጵያ በድል ማጠናቀቅ አለባት ብለዉ ድምጻቸዉን ጎላ አድርገዉ ለሚናገሩ፤ለሚጽፉና ማንኛዉንም የሃሳብና ሌላም አይነት ድጋፍ በማድረግ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ከፍ ያለ ክብር መስጠት እፈልጋለሁ።
የዛሬዉን ጽሁፍ ከመቓጨቴ በፊት ዉስጤን ጎንተል ያደረገኝን ሃሳብ ወርወር ላድርግና ትንሽ ይቅለለኝ።
የሰሜን እዝ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ አረም አራሚና ሰብል ወቂ እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት ለጊዜዉ ሳይገባኝ የማልፈዉ ቢሆንም፤ ነገሩ እንደከነከነኝ መደበቅ አልሻም።
የተፈጥሮ አደጋ ማለትም፤ እንደ እሳት ቃጠሎ፤የጎርፍ አደጋና የምድር መናወጥ ሲከሰት፤እንዲሁም ፤ እንዳሁኑ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል (በታሪክ አንበጣ ለትግራይ ምድር እንግዳ ባይሆንም) አስፈላጊም ሲሆን መልሶ ለማቁዋቁዋም የሰራዊቱ ከአካባቢዉ ህብረተሰብ ጋር መንቀሳቀስ የሚጠበቅ ነዉ። ሃተኡ መሌ (ይሁንና) « ከሃያ አመት በላይ በትግራይ የኖረ….ከህዝቡ ጋር አረም ሲያርምና ሰብል ሲወቃ የኖረ ጀግናዉ ሰራዊታችን ክህደት ተፈጽሞበታል…» እየተባለ የሚታተተዉ ወግ ምቾት አልሰጠኝም። የወያኔ ክህደት እንዳለ ሆኖ ከኦሮምያ ድረስ በተጫነ አፈር የተመረተዉን ተረፈ-ምርት ከሆነ ኤፈርት ከፍሎ ሊያሳርምና ሊያስወቃ ይገባዉ ነበር።
ምቾት ማጣቴን ዋጥ አድርጌ ወያኔን እስከነወዲያኛዉ ከላይዋ ላይ አሽቀንጥራ ለመጣልሀገሬ የመልስ ምት የምትሰጥበትን ጦርነት
መደገፍ ግን ምርጫዬ ነዉ።
ይቀጥላል