ትህነግ ከ 10 ሺህ በላይ የራያ ተወላጅ እስረኞችን ከራያ አላማጣ ይዞ እንደተሰወረ መንግስት አስታውቋል!!!!
ፋና ብሮድካስቲንግ
* በዋናነት ደግሞ ጉዳዩ የሚመለከተውና Ethiopia State of Emergency Fact Check በሚለው የመንግስት ኦፊሻል የፌስቡክ ገፅ መልዕክቱን የሚያስተላልፈው ኮማንድ ፖስት በእንግሊዝኛ ካቀረበው ሪፖርት ላይ ዋናው ጭብጥ በአማርኛ እንዲህ ይነበባል::
<< የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የራያ አላማጣ ከተማን ከትህነግ ጁንታ ነፃ አውጥቷታል:: በራያ አላማጣ ሽንፈት የደረሰበት የትህነግ የጥፋት ቡድን ከተማዋን ሲለቅ 10 ሺህ የሚሆኑ የራያ ተወላጅ እስረኞችን ወዳልታወቀ ስፍራ ይዟቸው ሸሽቷል:: >> ይላል ሪፖርቱ::
————–
በእርግጥ ቁጥሩ ከዚህ ይበልጣል:: በመቀሌ በኩይሃ በተንቤን እና ሌሎች ስውር የትግራይ እስር ቤቶች ከአመት እና ከሁለት አመት በላይ አፍኖ እያሰቃያቸው ያሉ የራያ ሽማግሌዎች እና ወጣቶችን ቤት ይቁጠራቸው!!! በዚህም ሳቢያ አያሌ ቤቶች ተዘግተዋል : ልጆች ያለ አባት ቀርተዋል: እናቶች አንብተዋል… :: በህዝባችን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ እና ሰቆቃ መግለጽ ከባድ ነው::
አሁን ደግሞ 10ሺህ የራያ ተወላጆችን ይዞ ተሰወረ::
እንግዲህ ምን እንላለን??? ምን ያደርጋቸው ይሆን?? ህዝብን አፍኖ የፖለቲካ ቁማር ሊጫወት?? ሰውን አፍኖ እንደ ቁስ መደራደሪያ ሊያደርግ?? ወይስ ከዚህም በላይ ሌላ ዘላለማዊ ጥፋት ሊፈፅም?? በፍፁም አይደረግም!!! ይህንን ከፈፀመ ግን የትግራይ ብሄረሰብ ተወላጆች የወደፊት እጣ ፈንታ ድድር ጨለማ እንዲሆን ወስኗል ማለት ነው!!!! ራያ ላይ ብቻ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ማሰብ ከወዲሁ ይዘገንናል!!! ይቅርባቸው እላለሁ!!!!
በአንፃሩ መንግስት አሁንም ከዚህ በላይ ይፍጠን!!!! በርግጥ መንግስት ይህንና ያንን ያድርግ ብለን መምከር ባንችልም ዜጎቹን ከእርድ ለመታደግ ግን የቻለውን ሁሉ መስዋዕትነት ይክፈል!!! በጣም ይፍጠን!!!
ውድ ወገናችን የሆነው የአማራ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻም ከመከላከያ ጎን በመቆም የእስከዛሬ ገድሉን ይቀጥል!!! በዚህ ሪፖርት ያልተካተተው politically correct ለመሆን እንጅ ዋጋን ለማሳጣት አለመሆኑን ልብ ማለት ያሻል!!!
በዚህ ሁሉ መከራ እና ስቃይ ውስጥ ፀንቶ የሚገኘው የራያ ህዝብ ደግሞ አሁንም በሙሉ ልብ ከመንግስት ጎን ይቁም!!!! እየተወሰደ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃም እስከፍጻሜው ድረስ በቁርጠኝነት ያግዝ!!! በመረጃና በሎጅስቲክስ ያግዝ!!!! መታጠቅ ካለበትም ይታጠቅ!!!!
መላው የኢትዮጵያ ህዝብም አሁንም ድምፅ ይሁነን!!!! የቀረ ህዝብ አለ! ከ10 ሺህ በላይ ዜጎችም መጨረሻቸው አልታወቀምና… ሚዲያዎች: ታዋቂ ግለሰቦች: ምሁራን : አክቲቪስቶች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ አሰሙ!!! ፈጣሪ የራያን ህዝብ እና የታፈኑትን ወገኖች ከክፉ ነገር ከልሎ የሁላችንንም ልብ ከዳግም ሃዘን ይጠብቅ!!!! ይነጋል!!!