>

ወልቃይት ጠገዴ. ራያና ትግራይ ምን ላይ አሉ ? (ግርማ ካሳ)

ወልቃይት ጠገዴ. ራያና ትግራይ ምን ላይ አሉ ?

ግርማ ካሳ

ሕወሃቶች ከመቀሌ ወደ ሃገረ ሰላም ተንቤን በመሰባሰብ መሽገው በመጨረሻ ዉጊያ ሃገረ ሰላም ሊሆን ይችላል…!!!
 
እዚህ የምታዩት የትግራይ ክልል ተብሎ ይታወቅ የነበረው ነው። ሕወሃቶች የሰሜን ላይ ጥቃት ከፈጸሙና ሕወሃትን የማሰገድ እንቅሳሴ ከተጀመረ ሁለት ሳምንት ገና አልሞላውም።፡ወደ 11 ቀን አካባቢ ነው።
በአረንጋዴ ያሉ አካባቢዎች ከሕወሃት ነጻ የወጡ ናቸው። ከሕወሃት ነጻ የወጡ ስል በየመንደሩ እየተገና መከላከያ አካባቢዎች ከሕወሃቶች አጽድቷል ማለት አይደለም። ሸሽተው በየጫካውና በየጉራንዱሩ፣ እንዲሁም የሲቪል ለብሰው በየቤቱ የተደበቁ ይኖራሉ። አንዳንድ ደግሞ እከተኖች ራቅ ብለው ተከበው ያሉ እንደ ዲቪዥን ያሉ ጥቂት ቦታዎች አሉ። ሆኖም ግን ለብቻቸው ተበታትነው ያሉ እንደመሆናቸው ብዙዎች እጅ እየሰጡ፣ ብዙዎች እየሸሹ ራሳቸውን ለማዳን ነው እህየተጨነቁ ያሉት።
በብርቱካማ ቀለም ያለው ደግሞ በሽሬና ወደ ጎንደር በሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ወደ ትግራይ የተጠቃለለው ጠለምትን ጨምሮ ያለ አካባቢ ነው። ይህ አካባቢ ተራራማ እንደመሆኑ ፣ ሽሬ ዙሪያዋንም መከላከያ በመቆጣጠሩ ከመቀሌም ሆነ ከሃገረ ሰልማ ዋሻ ተለይተዋል። ሽሬ ለዚህ ነበር በጣም ቁል የሆነችው። ዝሬን በመያዝ እንዳለ ይሄን አካባቢ መነጠል ተችሏል። ሙሉ ለሙሉ ባይባልም ይሄ አካባቢ በተወሰነ መልኩ ነጻ ወጥቷል ማለት ይችላል። ስለተከበበ።
ሶስተኛው በቀይ ያለው ገና በሕወሃት ስር ያሉ አካባቢዎች ናቸው። በቅርቡ ጊዜ
እነ ኮረም ፣ ማይጨው ያሉም በመከላከያ ስር ይሆናሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው። መቀሌም በቀናት ውስጥ እጅ ሳትሰጥ አይቀርም።፡ ሕወሃቶች ከመቀሌ ወደ ሃገረ ሰላም ተንቤን በመሰባሰብ መሽገው በመጨረሻ ዉጊያ ሃገረ ሰላም ሊሆን ይችላል።
ልሳሳት እችላለሁ፣ በኔ እይታ ግን መቀሌ ከተያዘች ወያኔዎች ሃገረ ሰላም ቢመሽጉም ትግራይ ነጻ ወጣች ብለን ማወጅ እንችላለን።
ከዚያ በኋላ ደግሞ ሌላው ትልቁ ጥርነት ይጀመራል።፡ጥይትና መድፍ እየተተኮሰ የሚደረግ ጥርነት ሳይሆን ሕዝብን ለማቀራረብ፣ በወጊያው ምክንያት የተፈጠረው ቁስል እንዲድን ለማድረግ አሁን ያለው አይነት ችግር ሌላ ጊዜ ተመልሶ እንዳይመጣ ለማድረግ የሚደረገ ከአስተሳሰብ፣ ከአመለካከት ግር የሚደረግ ጦርነት። ይሄ ጦርነት በጣም ከባዱና ብዙ ጊዜ የሚወስድ ጦርነት ነው።
Filed in: Amharic