>

በሰሜን ጦርነት ድባብ ሥር ኦርቶዶክሳዊያንን ማፅዳት በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ቀጥሏል!!! (ፋንታሁን ዋቆ)

በሰሜን ጦርነት ድባብ ሥር ኦርቶዶክሳዊያንን ማፅዳት በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ቀጥሏል!!!

ፋንታሁን ዋቆ
አንዘናጋ!

 
#ኦርቶዶክስ የሆናችሁ እባካችሁ የገዳይ አስገዳዮቻችንን ማንነት አትሸፋፍኑ!!!! 
 
ባለጥላውን ትቶ ጥላውን መደብደብ ለውጥ አያመጣም
ከልብ ከፈቀደ  የኦርቶዶክሳዊያንን ሞት መከላከልና ማስቆም የሚችለው፤ ወይንም እያሳበበ የሚያስቀጥለው ባለ ታንኩና ባለባንኩ መንግሥት ብቻ ነው።
ኦሮማያ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ለሚፈፀም ወንጀል ተጠያቂው ራሱ የየክልልሎቹ መንግሥትና እነርሱን ለማረቅ ዳተኛ የሆነው ፌደራልጰመንግሥት ነው።
ኦነግ መንግሥት አይደለምና ከበደኖ የዛሬ 30 ዓመት የጀመረውን ቀጥሏል። ማስቆም*የመንግሥት ኃላፊነት ነው።
ትሕነግ ዘረኝነትና አራጅነት ተፈጥሮዋ ነውና እርሱኑ አጋንታዊ አሠሯሯን  የሙጥኝ ብላ አዲስ ጦርነት ውስጥ ናት። በሀገሩ ሁሉ ተላላኪ እንዳላት ማንም ያውቃል።  መከላከል ግን የመንግሥት ድርሻ ነው።
መከላከል ያልተቻለው መንግሥት በሚመራበት የተውሶስሑት  የፖለቲካ ርእዮት ምክኒያት ራሱ በኦርቶዶክስ መኖር ደስተኛ አይደለም።
የችግሩ መፍትሔ የሀገር ሥልጣን በጨበጠ ትከሻ ላይ ነው ያለው።
የ1960ዎቹ የኮሚንስት አጋንንት የፈጠረው የምሁራን እይታ፣ ሒትለርን የወለደው የሉተር መንፈስ የፈጠራቸው ፖለቲከኞች፣ አይሲስና አልሻባብ ከእንቅልፍ ያነቁት የኦቶማን ቱርክ መልዕክተኛ የአህመድ ግራኝ ጂሐድ ናፋቂዎችን የፈጠረው አዲሱ ኢስላም በአንድነት  የሶስትዮሽ ጊዜአዊ ስልታዊ ትብብር ፈጥረው በኦርቶዶክስ መጥፋት ተስማምተዋል።
ይህንን ትብብር አጋር ያደረገው ዘመንኛ ፖለቲካ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ለብልፅግናና ለዲምክራሳዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት ነው ብሎ አምኗል (ታላቅ ድንቁርና)።
ስለዚህ በኦነግ፣ በትሕነግ፣ በሌላ ዘረኛ ፓርቲ እያሳበበ ኦርቶዶክስን ከየአካባቢው የማጽዳት ሂደቱን መንግሥት ራሱ ይፈልገዋል።
የማፅዳት ሂደቱ እንዳይቋረጥ የብሔር ፖለቲካ፣ ቋንቋ፣ ነፍጠኛ፣ ጭቆና፣ የበላይነትና የበታችነት፣ ታሪክ፣ መብት፣ ነፃነት ወዘተ የሚባሉ የኮሚኒስቶቹ የተውሶ ድንግዝግዝ ፅንሰ ሀሳብ የደነቆሩ ልሂቃን ዜማ አሁንም ከአየር አልወረደም። ከሕገ መንግሥቱም አልተፋቀም።
ስለዚህ በማንም ስም ይፈፀም በማን፣ አሁን በየቦታው ለሚሰቃየውና ለሚገደለው ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ  ተጠያቂው ከፌደራል እስከ ቀበሌ የተዘረጋው ለመታረምጨፈቃደኛ ያልሆኒው የመንግሥት ሥርዓት ነው።
ኦርቶዶክሳዊያን ዋናውን ተጠያቂ ትተን በማስፈፀሚያ ላይ ስናላዝን በጉራ ፈርዳ፣ ሻሸመኔ፤ በቡርጂ፣ በወለጋ፣ በአዲስ አበባ፣ በጉምዝ መታረዳችንን ሳይከላከሉ የቀሩ የክልልና የከተማ መስተዳደር ባለሥጣናት ዛሬም በሥልጣን መቀጠላቸው ምን ይነግረናል? ሥልጣን የያዙት ሊጠብቁን ወይስ በመግለጫ ኃዘን ሊደርሱን?
እንደኔ ኦርቶዶክሳዊያንን የሚያሳርደን የመንግሥት ፈቃደኝነት ነው!!! መፍትሔውም ከመንግሥት ጋር ብቻ የተያያዘ  ነው።
ሌሎች ልማቶችና ለማሸነፍ የምንደክምላቸው ጦርነቶች ሁሉ  የኦርቶዶክሳዊያንን ሕልውና በሁለተኛ ደረጃ ላይ እያስቀመጡ ተቸግረናል።
በቃ!!! 
ማስመሰል ይብቃና መንግሥት የጥፋት ዒላማ የተደረጉ ኦርቶዶክሳዊያንን በልዩ ሁኔታ በማስታጠቅ ራሳቸውን እንዲጠብቁ፤ በሚኖሩበት አካባቢ ሁሉ የመንግሥት መዋቅር አካል እንዲሆኑ፤ ፐረ ኦርቶዶክስ የክልል መንግሥታት መዋቅር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ይደረግ።
Filed in: Amharic