>

አሻድሌና ማዕከላዊው መንግስት በጋራ የሚያ ፈሱት የአማራ/አገው  ደም ማብቂያው መች ይሆን?!? (መስከረም አበራ)

አሻድሌና ማዕከላዊው መንግስት በጋራ የሚያ ፈሱት የአማራ/አገው  ደም ማብቂያው መች ይሆን?!?

መስከረም አበራ

ከትናንት ወዲያ አመሻሽ ላይ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወ/ስላሴ “ቢሰቀጥጥም እውነት ነውና እይው” ብሎ በቤኒሻንጉል መፈጠርን የሚያስጠላ ስራ የተሰራበትን ፎቶዎች ላከልኝ።
ፎቶው ሃገር ሰላም ብለው በመኪና በሚጓጓዙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተደረገ ለወሬ በማይመች ሁኔታ ክቡር የሰውልጅ ገላቸውን በስለት መቆራረጥ፣ደማቸውን እንደ ጎርፍ የማፍሰስ አረመኔያዊነት ነው።በበኩሌ ፎቶውን በሙሉ አይኔ ለማየት ተቸግሬያለሁ።እኔ የሆነውን በአይኖቸ ለማየት ያልቻልኩ እስከመጨረሻዋ እስትንፋሳቸው በስለት የተጨፈጨፉት  ምስኪኖች በዛች ቅፅበት ምን  እንደሆኑ ማሰብ አልፈልግም። (በነገራችን ላይ ፎቶዎቹን የማየት ብርታት አለኝ  ለሚል ሁሉ በውስጥ መስመር ለማጋራት ዝግጁ ነኝ)
ይህ ማለቂያ ያጣው በቤኒሻንጉል የሚደረገው የአማሮች ሞት የሚያቆመው የአማራ ህዝብ በጋራ ወገቡን ጠበቅ አድርጎ በሚያደርገው ኮስታራ ትግል እንደሆነ አምናለሁ። ታዲያ ትግሉ እንዴት ይጀምር ሲባል ለእኔ የሚታየኝ መንግስትን አንድ ቀላል ጥያቄ በመጠየቅ ነው።
 ይህም ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን በመጣሉ ላይ ብቻ እንዲበረታ አበክሮ የሚያሳስበው መንግስት ህወሓትን ለማጥፋት የሚደረገው ዘመቻ በተፋፋመበት ሰዓት ሹም ሽር አድርጓል። ይህ ሹም ሽር የቤኒሻንጉል ክልልን የአማራ/አገው የለቅሶ ድንኳን ያደረገውን የክልሉ ፕሬዚደንት አሻድሌን አላካተተም። ለምን???????!!!!!!!!
 በቤኒሻንጉል አሁን እየሆነ ያለው ጥፋት አሻድሌን ከስልጣን ለማንሳት የሚያንስ ሆኖ ነው ወይስ ድርጊቱ በመንግስትም ስለማይጠላ ነው?
 ሃገሩ ኢትዮጵያ ባይሆንና አሻድሌና ማዕከላዊው መንግስት ገና የሚያስገዱሉት በርካታ አማራ/አገው እንዳለ ባይማማሉ ኖሮ አሻድሌ ራሱ በፈቃዱ ነበር ስልጣን መልቀቅ ያለበት።
 ስለዚህ የአማራ ህዝብ በቤኒሻንጉል በኩል በሚያደርገው ትግል ቅድሚያውን መውሰድ ያለበት የህዝብ ደም የሚያፈሰውን አስተዳደር የሚመራው  አሻድሌ ለምን በማዕከላዊ መንግስቱ ተወደደ?የሰሞኑ ሹም ሽርስ እንዴት ዘለለው?በክልሉ የሚፈሰውን አረመኔያዊነት ማስቆም አለመቻል ከሹመት ለማስነሳት  ያልበቃው ደሙ የአማራ/አገው ደም ስለሆነ ነው???????በሚሉት ጥያቄዎች ዙሪያ መሆን አለበት!
Filed in: Amharic