>
5:26 pm - Tuesday September 17, 7411

"ላለፉት 27 አመታት የተተገበረው ፌዴራሊዝም የውሸት ከመሆኑም በላይ የአንድ ቡድን የበላይነት የነገሰበት ነበር!"

“ላለፉት 27 አመታት የተተገበረው ፌዴራሊዝም የውሸት ከመሆኑም በላይ የአንድ ቡድን የበላይነት የነገሰበት ነበር!”
 የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ኸርማን ኮኸን
የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ኸርማን ኮኸን ኢትዮጵያ ለገባችበት ችግር  ዘራፊው ህወሓት እና የእሱ ወዳጆች  በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ላይ ራሳቸው  የበላይ በማድረጋቸው  እና  በአገሪቱም  “ሀሰተኛ” የፌዴራል  ስርዓት  በመመስረታቸው  ነው  ብለዋል።
 በ 1991 በጎሳዎች ላይ የተመሠረተ የክልሎች ስርዓት በኢትዮጵያ   የተቋቋመ  ቢሆንም   ስርዓቱ  የውሸት  በመሆኑ   ከትግራይ  ውጪ  ያሉ  ክልሎች   አንዳቸውም   ቢሆኑ  በአገሪቱ ላይ  የመወሰን  መብት አልነበራቸውም ያሉት ኸርማን ኮኸን፤  ሂደቱ የአንድ ፓርቲ  የበላይነትን ያነገሰበት  ከበርካታ ዓመታት  በፊት  በአፍሪካ ተሞክሮ  የወደቀ   አካሄድን የተከተለ ነው ብለዋል።
ጥቂት የህወሓት  አባላት የአገሪቱን ኢኮኖሚ  ብቻቸውን  በበላይነት በመቆጣጠራቸው ምክንያት  ጥቅማ ጥቅሞችን ለእነርሱና እነርሱን ለሚመስሏቸው  ብቻ  ሲያደርጉ መኖራቸውን የጠቀሱት ኸርማን ኮኸን ፤ በዚህም    ምክንያት  ሌሎች የህብረተሰብ  ክፍሎች  ጫና ተፈጥሮባቸዋል፤ የመሰረተ ልማትም   ፍትሃዊነት በጎደለው መልኩ  ለራሳቸው አድርገውታል፤ ይህ አይነት አካሄድ  በሌሎች ላይ ቁጭትና ጫና  ፈጥሮባቸዋል ብለዋል አምባሳደሩ።
ይሄንን አይነት በደለን ፖለቲካዊና  ኢኮኖሚያዊ  ኢፍትሃዊነትን ተቃውመው  ሰልፍ በሚወጡ  ባልታጠቁ ሰልፈኞች  ላይ  የህወሃት  ኃይል  የሚወስዳቸው  እርምጃዎችም  ያልተመጣጠነ  እንደነበር  ኸርማን ኮኸን  አብራርተዋል።
ይህን ሁሉ የሰብጻዊ መብት  ጥሰት  ይፈጽም ለነበረ  አካል  አሜሪካ ለምንድን ነበር  የምትደግፈው ተብለው የተጠየቁት አምባሳደሩ፤ “ ስትራቴጂካዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት ስንል ይህን ታግሰናል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
Sours:- EPA
Filed in: Amharic