>
5:16 pm - Saturday May 24, 4702

መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ፤ ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ። (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ)

መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ፤
ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ።
ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

  ለመግቢያነት፦የሐዲስ፡ዓለማየኹ።
(ባ፲፱፻፳፰፡ዓ.፡ም.፥ዐርበኝነት፡ሲወጡ፥ለሕዝብ፡ከበተኑት፡ቀስቃሽ፡ግጥም፡ውስጥ፡የተቀዳ።) አያያዝኩ፦
 
እናት፡ኢትዮጵያ፡
ውዲቱ፥ውዲቱ፥
በሦስቱ፡ቀለማት፡
የተሸለምሺቱ፥
ነጻነት፡የሚሽር፡
ቢመጣብሽ፡ብርቱ፥
ደማችን፡ይፈሳል፥
አይቀርም፡በከንቱ።
ላንቺ፡የማይረዳ፡
ሳለ፡በሕይወቱ፥
በረከትሽን፡ይንሣው፡
እስከ፡ዕለተ፡ሞቱ። 
            አመሰግናለሁ ክቡር ዶክተር ሎሬት የሐዲስ፡ዓለማየኹን።
003.JPG
     የታሪክ ትንቅንቁ በትግሬ ክፍለ ሃገር ተጧጥፏል፤መንግሥት(በሥመ ብልፅግና) እና “ምን አገባህ?” የሚል የሕውሃት(ዘረኝነትን የሚደግፍ)ቡድን ናቸው የሚገዳደሉት።”መፈፅም ዘዐቢይ፥ቀብር ዘጥልምያኮስ”የተባለውም ለእነዚሁ ሁለቱ ወገኖች የቀረበ ነው።በአንድ ወገን ይህን የትግሬ”ክፍለሓገር ሕዝብ” በዕምቢተኛነት አመፅ አግቶ፤በሕገመንግሥት ጭምብል በራሳቸው ሥልጣን በፈጠሩት ቡድን የሚመራ፣በትዕቢት እየተቆዘረ ለሌላው ደንታ በሌላቸው፣ሰዎችን በሚመስሉ እና የሰው ቆዳ በለበሱ ርኩሶች የሚዘወር ሰበበኛ ገዳይ አሸባሪ ፓርቲ ነው።
በሌላው በኩል በመንግሥት ሥልጣን ሳይወዱ-በግድ ትዕግሥት ለገዳዩ ያምበሸበሹት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ፣ በአንፃራዊነት የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ተወካይነታቸውን ባለመዘንጋት፣ለስድስት ሚሊዮኑ ሰዎች በደም ሳይፈርሙ፦ተንቀልቅሎ ገዳዩ ጦርነቱን በማስጀመሩ በትዕስት መሪ አማካኝነትም ፊሽካ እንዲነፉ ያስደረጉ የፖለቲካ ቀዶ-ጠጋኝ ዶክተር የተደረገ ፍልሚያ ነበር፤እነሆ ዓለም በአደባባይ እያየው እና ገዳዮቹን እየረገማቸው ለሕዝብ ክህደታቸውን ሲያጋልጥ፦ለሁለቱም በየግብራቸው”መፈፅም ዘዐቢይ ተብሎ”ለዶክተር ዐቢይ እንደተሰጠው፣የሕውሃት ቡድን ጉዳይ ደግሞ፣”ቀብር ዘጥልምያኮስ”በሚል ትግሉ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
       መቼም የኢትዮጵያን ነፃነት እና አንድነት ለማስጠበቅ ያለፉት ትውልዶቻችን የበለጠውን መስዋዕትነት ባይከፍሉ ኖሮ ኢትዮጵያችን በነፃነት ተጠብቃ እስከዛሬም አትኖርም ነበር።በተፃራሪው ደግሞ አንድነቷ እንዳይኖር በባዕዳን በጥቅማ-ጥቅም ተገዝተውም ሆነ ተታለው ሕዝቦቿን እያለያዩ ሊበታትኑን ሌትተቀን በመሰሪ ተንኮሎች የጠላት መሳለቂያ እያጋደሉን ያደረጉን ውርደታሞች በታሪክ ተመዝግበዋል።ይሁንና የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነውና፣ጡቷን መንከስ ብቻ አይደለም ራሷን ኢትዮጵያን ለመሸጥ ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ያልመዘዙባት ሠይፍ አልነበረምና፤ቢያንስ ለሃምሳ ዓመታት አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው በራሳችን ዜጎች ሰበብና ምክንያትን እያስታከኩ በደም ያጨማለቁን የሰዎች ሥም ዝርዝር ታሪክ አላት። 
     የጀግኖችም ሆነ የከሃዲዎች በነፍስወከፍ የተፃፉም ቢሆን በንፁህ ሕሊናቸው ፀንተው ከተሰዉት ሐይማኖታዊ አባት አቡነ ጵጥሮስን በግምባር ቀደምትነት እናስታውሳቸዋለን፤በዘመናችን ደግሞ ከእነ ንፁህ ሕሊናቸው ይህቺን ዓለም የተሰናበቱ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ነብሳቸውን እግዚአብሔር በመንግሥተ-ሰማያት ያሳርፋትና ፍፁም ዝም ሳይሉ፣ጠመንጃ ሳያነሱ፤በእሳት ልሳናቸውና በመራር ቃላታቸው እየለበለቡ ዕድሜ ልካቸውን መንግሥታትን እንደተዋጉ ሁላችንም እናውቃቸዋለን።በእርሳቸውም የትግልት ስልት ምክንያት በዘመነ-ቴክኖሎጂ ሐቁን በሕዝብ መገናኛ ሚሳይል እያስወነጨፉ የሚደበድቡ ጠንካራ ዜጎች ተፈጥረውም ሰምተናል።የሚያሳዝነው ደግሞ”ሰውን በመግደል የፈለግነውን ማስፈፀም እንችላለን”ብለው የሚያምኑና የሚተገብሩ፤ራሳቸው እንዳይሞቱ ግን፣ከለቅሶ ጀምሮ የማያደርጉት ነገር እንደሌለ ማየታችን ነው።        
      የእኛው ትውልድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው የምንላቸው ለእነዚያ የፋሺሽት-ሕውሃት ሰው በላዎች ዛሬም በድብቅ ጠበቃዎች ሆነው ያስረግጡናል።”ከትግሬዎቹ መካከል-“ሕውሃት ነን” የሚሉት በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወቅት”ናዚዎች”በመሆናቸው ሲኩራሩ እንደነበሩት ገዳዮች ነገ በሕዝብ የሚሳደዱቱ ናቸው።፣በዚህ ብቻም አላበቁም “እኛ ከሞትን ሰርዶ አይብቀል”ብለው ሊያጠፉን ሲውተረተሩ፣ወገባቸውን በሕዝብ አመፅ ተቀጥቅጠው ሽባ እንደሆኑ አንገታቸው ተቆርጦ፣እየወደቁ እየተንፏቀቁ መቀሌ በእንቅጥቅጥ ከሸመቁ ድፍን ሁለት ዓመታት ካለፋቸው ሰነባበተ።              “ያ!”የመከራ ወቅት ግን በይቅርታ እና በፍቅር ሥም ሠላምን በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመፍጠር በሚል “በአደባባይ” ስምምነታቸው ቢነገርም የኢትዮጵያ ግምባር ቀደሙ ጠላት “ዘረኝነትን የዘራው፣ሕውሃት”ያለ እኛ  ኢትዮጵያ የለችም” ብለው ዛሬም ይገድሉናል፣በትክክል እየገደሉን እና እያጋደሉን ይገኛሉ፤ለኢትዮጵያ ችግር ሰበቦቹም ሆኑ ምክንያቶቹ አሁንም ርዝራዦቹን የደበቀው “ሕውሃት”የተባለ የሽብርተኛ ቡድን ብቻ ነው፣ሌላው አገላለፅ ከዝባዝንኬ ይቆጠራል። 
 ስለዚህም ዶክተር አቢይ አህመድ ማሰሪያ የትግላችንን ልጥ ካለበት ፈልጎና መርጦ ካመጣ በኋላ በሚገባው የዓለም አቀፍ ሕግ ተጠፍሮ እንዲታሰርና በታሪክ ማሕደር ውስጥ እንደነዚያ ፋሺሽቶ ናዚዎች ማስደረግ ይጠበቅበታልና”መፈፅም*ዘዐቢይ መሆኑንና የከሃዲዎች መጨረሻ ደግሞ ቀብር ዘጥልምያኮስ በአንፃሩ መፈፀሙን ማረጋገጥ ይኖርበታል።
   ስለዚህም ነው ቅማሏን እና ትኋኗን አግኙ፤ያለበለዚያ ለሠይጣን ደንግጦ ሬሳ መቁጠሩ መፍትሄ እንደማያመጣ ደጋግሜ የገለፅኩት።ወገን እንግባባ ዛሬም አትሞኙ፤ችግሩን ለማጥፋት ቅማሏን አግኙ።ትሗኗ ላይ አሁን ካልወሰድን እርምጃ፤ተስቦው አይቀርም ለመዳን ግን እንጃ::ለዚህ ነው እንደገናም በየጥጋጥጉ፤ጊዜ ያብከንነው የሌለ አትፈልጉ::
    እባካችሁ ወገኔ ዛሬም አትሞኙ፤ቅድሚያ ይቺን ፋሺሽት ትኋኗን አግኙ።ጥርሷን ከተከለች ቅማል እንኳን ባቅሟ ፤ጥብጣብ ታስፈታለች አሳብጧት ደሟ።ሺህ ቦታ መቶ ጥግ በየጉራንጉሩ፤ማከክ መሞዠቁ አካል መቆፈሩ፤ለሰይጣን ደንግጦ ሬሳ መቁጠሩ፤ መፍትሔ ባይሆንም እንደው ለጅምሩ፤ገዳይ እንዳይቀድመን:-ከልብ ግን አምርሩ።ለሕዝብ በመቆማችሁ ባንዳ የጠላችሁ፤ የኢትዮጵያ ሕላዌ ያንገበገባችሁ።ለአገር የምትጓጉ፤ትርጁማን ፈልጉ!!!እናም ለነፃነት እንዲቆም በዝና፤ዛሬውኑ አምጡለት የመቅደምን ዜና።ለነፃነት ፃፉ በሙያችሁ ሁሉ፤ለፍትህ ለፍፉ ያሻችሁን በሉ።ሁሉም ሆኖ ግና ቃል ግቡልንና፤ አምጡልን በዝና የደም-ዋጋ ዜና!!!…….መንግሥት ተጠልለው ለጥቅም የማሉ፤የሕዝብን ያቀለሉ ጋዜጠኞች አሉ።ሕዝብን የሚወጉ፤ከሕዝብ የመሸጉ።ፋሺሽቱ-ወያኔ በኦሮሞ ሥም ታገል፤እኛን እንዳጋደልክ ሩጥ ወደገደል።ዛሬም ዋሻ ሆነውበሕዝብ እያላገጡ፤በድብቅ ትዕዛዝ አሉ የሚሰጡ።ከሸበጥ ተነስተው አየር ላይ የወጡ፤በወንጀል በዝርፊያ አብጠው የቀበጡ፤በግፍ በጭካኔ ሕዝብን የረገጡ፤ዛር ሳይሞትባቸው ሳይገለበጡ፤ከላይ ተከስክሰውምድር ላይ ሳይፈርጡ፤ እንደወንጀላቸው በሞት ሳይቀጡ፤እናት ሆድ አይገቧት የትም አያመልጡ፤አይማሩም ፍፁም እንዲህ እንዳላገጡ። ቀረ’ኮ ይሉኝታ ቀረ’ኮ መ-ደበቅ፤በጉጅሌ ጉያ ሕዝብ ላይ መሳለቅ።በይሉኝታ ዝምታ ምንም የማይባል፤አይነደረቅ ሌባ:-ቃጭል ይዞ ይገባል።ዘንዶው ቢቀረንምጇሗር እባቡም ተይዟል፤የኢትዮጵያ ትግል!!!በጨካኞች ጦዟል።በሰላም መታገልብለን ይሻለናል፤ እናውቃለን ያሉት፣ዛሬም ያጋድሉናል።ዘንዶውም አይቀርምከያለበት አገር፤በእንፉቅቅ ይመጣል፣ከዋሻቸው ሳይቀር። እየተለቀመ አደራ እባቡንፍፁም እንዳትገድሉት፤ከሙሴ ተማሩ እንዲደርቅ ስቀሉት።እናም ተቀጥቅጦደሙ እየፈሰሰ፤ይነቃል በቅፅበትአፈሩን ከላሰ።አንገቱም ቢቁረጥ እየሞቶ ይኖራል፤በጥርሱ ሰው ገድሎመሞት ይጀምራል።ግና እስከዚያው ድረስጇሗር ያው እባብ ነው፤ሞቷል ብለን ሲገድል አይተን የማናምነው።ወገን እንግባባ ዛሬም አትሞኙ፤ችግሩን ለማጥፋት ቅማሏን(ትኋኗን)አግኙ።
Filed in: Amharic