>
5:13 pm - Monday April 20, 0342

የራያ አላማጣ ሕዝብ “ማንነት” (አቻምየለህ ታምሩ)

የራያ አላማጣ ሕዝብ “ማንነት”

አቻምየለህ ታምሩ

በየሄደበት ሰማዩንም ምድሩንም የኔ ነው ከማለት አፍታ እንኳ ቦዝኖ የማያውቀው ናዚያዊው ኦሮሙማ የአማራ ልጆች መስዕዋት የከፈሉበትን የትግል ፍሬ  እንደልማዱ  ለመሰብሰብ ከሰሞኑ አላማጣ ላይ ከች ብሏል። ኦሮሙማ ውስጥ ሐፍረት የሚባል ተፈጥሮ በተፈጥሮ ለሰው ልጅ የለገሰችው ስሜት ስለሌለ በፍጥምጥም ራሱን የአላማጣ አቅኝና “ራስ”  አድርጎ በዋናው ልሳኑ በኦ.ቢ.ኤን. ዝባዝንከውን ሸክፎ ብቅ ብሏል። የኦሮሙማ ድፍረት የሚመነጨው ሰውን  ሁሉ እንደ ቄሮ የተባለውን ሁሉ ያለ ስስት ሳይመረምር የሚቀበል ደንቆሮ  ነው ብሎ ከመናቅ ነው። በመሆኑም እዚያ ቤት ማስረጃና ዱካ ሰማዩንም ምድሩንም የኦሮሞ ለማድረግ ስለማያግዝ ዋጋ የላቸውም። ከሰሞኑ አላማጣ ላይም የከሰተው ይህንን ተፈጥሮውን ነው።
ለመሆኑ የራያ አላማጣ ሕዝብ “ማንነት” ምንድን ነው?  ይህን ጥያቄ  ለመመለስ አካባቢው በኦሮሞ ከመወረሩ በፊት ማን ይኖርበት እንደነበር ታሪክ እስከመምዘዝ ድረስ አያስኬድም። የፋሽስት ወያኔና የናዚ ኦነግ ሃይማኖት የሆነውን “የራስን እድል በራስ መወሰን” የሚሉትን  ቅራቅንቦ መፈተሹ ብቻ ይበቃል።
«የራስን እድል በራስ መወሰን» በሚለው የብሔርተኞች «መርኅ»  መሰረት “የማንነት” ዋናው አምድ የማንነቱ ባለቤት ራሱን ነኝ ብሎ የሚገልጽበት መለያ ነው። ይህንን መነሻ ወስደን የአላማጣን ወረዳ ሕዝብ ማንነት ስንመረምር ሕወሓት የአላማጣ ወረዳን ወደ ትግራይ ክልል ባካተተበት ወቅት የአላማጣ ወረዳ ከነበረው አጠቃላይ ሕዝብ ውስጥ 18 ሺህ 663ቱ ወይም 65%  አማራ ሲሆን 7ሺህ 886ቱ ወይም 25% ደግሞ  የራያ ትግርኛ [ራይኛ] የሚናገር ነበር። ከዚህ በተጨማሪ በወረዳው ምስራቃዊ የገጠር ክፍል 2886 የሚሆን ወይም 9% ያህሉ ኦሮሞ ነኝ የሚል ሕዝብ ይኖርበ ነበር። ይህ የሕዝብ ቁጥር በ1976 ዓ.ም. በደርግ  የተካሄደው የሕዝብና የቤት ቆጠራ ውጤት ሲሆን ወያኔም ይህን የሕዝብና የቤት ቆጠራ ውስጤ በ1984 ዓ.ም. ታኅሣሥ ወር ላይ የሚቀቅለውን ቀቅሎ ድጋሜ በማሳተም ከትግራይ ውጭ ያሉ ክልሎችን እንደመሰለው ለማካለል ተጠቅሞበታል።
ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነውና ብሒሉ  በኦነጋውያን ዘንድ የተፈተነ ፌዴራሊስት እየተባለ የሚሞካሸው ፋሽስት ወያኔ ማንነት ላይ የተመሠረተበትን «የራስን እድል በራስ መወሰን» መርሁን ባፍ ጢሙ ደፍቶ 18 ሺህ 663 ወይም 65% አማራና 7ሺህ 886 ወይም 25%  የራያ ትግርኛ[ራይኛ] ተናጋሪ ይኖርበት የነበረው የአላማጣ ወረዳ የትግራይ ክልል አካል አደረገው።  በነሱ መርኅ መሰረት ግን 65% አማራ ይኖርበት የነበረው የአላማጣ ወረዳ መካተት የነበረበት  አማራ ክልል ወደሚባለው  እንጂ ወደ ትግራይ ክልል አልነበረም። ይህንን ሲያደርግ የኖረው ፋሽስት ወያኔ ነው እንግዲህ የራስን እድል በራስ መወሰን፣ ፌዴራሊዝምን፣ ወዘተ ለኢትዮጵያ አስተዋወቅሁ እያለ ሌት ተቀን ሲያደነቁረን የኖረው።
የተፈተነ ፌዴራሊስ ነው እየተባለ በኦነጋውያን የሚሞካሸው ፋሽስት ወያኔ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ከሾማቸው ጀኔራልና አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጁኔይዲ ሳዶ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ሙክታር ከድር፣ ወዘተ ከሚባሉት ምስለኔዎች ይልቅ አሐዳዊ ነው እየተባለ በሚወገዘው በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የነበሩት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪው ኦሮሞ ራስ መስፍን ስለሺ፣ የአርሲው ባላባት ግራዝማች ኦገቶ ጉቱና እና ደርግ በግፍ የረሸነው ልጃቸው ፊታውራሪ በቀለ ኦገቶ፤ የወለጋዎቹ ልጅ ካሳ ወልደ ማርያም፣ ጀኔራል ቀልቤሳ ቤካ ወዘተ. . . እጅግ ከፍተኛ የሆነ የመግዛት ሥልጣንና «የራስን እድል በራስ የመወሰን» መብት ነበራቸው።
ወደ ዋናው ጉዳይ ስንመለስ ሰልቃጩ ኦሮሙማ የአማራ ልጆች መስዕዋት የከፈሉበትን የትግል ፍሬ ለመሰብሰብ አላማጣ ተከስቶ ኦሮሞ ሊያደርገው የሚሻው ራያ አላማጣ 9% የማይሞላ ኦሮምኛ ተናጋሪና ከ65% በላይ አማራ የሆነ ሕዝብ  የሚኖርበትን ምድር ነው። ዲሞክራሲያዊ ነው እየተባለ የሚደሰኮርለት ገዳ ወልዶኛል የሚለው ኦሮሞማ የዲሞክራሲ ሽታ ቢኖረው ኖሮ 9% የሚሆን ዳህጣንን (minority) ተጠግቶ 65% የሚሆነውን አብዛኛ (majority) ለመሰልቀጥ ባላሰበ ነበር።
ከላይ የተያያዘው መዝገብ ጥንብ አንሳው ኦሮሙማ ሊወረው የሚያንዣብብበት ራያ አላማጣን የሕዝብ ስብጥር የሚያሳይ የስታቲስቲክስ ማስረጃ ነው።  እነ ሰማዩም ምድሩም የኛ ውሸት ማምረታቸውን ወደፊትም ይቀጥላል! እኛ እንዲህ እየተከታተልን ውሸታቸውን ራቁቱን ማስቀረቱን እንቀጥላለን!
Filed in: Amharic