የአውሮፓ ምክር ቤት (European Parliament)
D W
* …. “ሁሉንም ግድያዎች፣ ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀምን ፣ ያለ ፍርድ እስራትን እና በግዳጅ መሰወርን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የተሟላ፣ ነፃ፣ ውጤታማ እና ገለልተኛ የሆነ ምርመራ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እንዲያደርግ” ተጠየቀ…
“የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና በህወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል” የጀመሩት ውጊያ እንዳሳዘነው የገለጸው ምክር ቤቱ ሁለቱም ወገኖች በአፋጣኝ ተኩስ እንዲያቆሙ፤ ዘላቂ ሰላማዊ መፍትሔ ለማበጀት ፖለቲካዊ ልዩነቶቻቸውን በአገሪቱ ሕገ-መንግሥት መሠረት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ፤ የተኩስ አቁም ቁጥጥር የሚደረግበትን ስልት እንዲቀይሱ እና በአካታች ውይይት ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር እንዲሰሩ ምጠይቋል።
የአውሮፓ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ረዘም ያለ የውሳኔ ሐሳብ ያሳለፈው ትናንት ሐሙስ ሕዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው። በዚሁ የውሳኔ ሐሳብ “ሁሉንም ግድያዎች፣ ከመጠን በላይ ኃይል መጠቀምን ፣ ያለ ፍርድ እስራትን እና በግዳጅ መሰወርን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ የተሟላ፣ ነፃ፣ ውጤታማ እና ገለልተኛ የሆነ ምርመራ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እንዲያደርግ” የጠየቀው የአውሮፓ ምክር ቤት ለዚህም የትግራይ ባለስልጣናት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።
ምክር ቤቱ “በማይ ካድራው ጭፍጨፋ የሚመለከታቸው አካላት ግልጽ ምርመራ ሲያደርጉ በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች በቅርበት እንዲሰሩ እና የወንጀሉ ፈፃሚዎች ያለ መዘግየት ተጠያቂ ሆነው ለሕግ እንዲቀርቡ” ጠይቋል።
ሙሉውን ለማንበብ ↓