>

ለ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር:- ( አሳዬ ደርቤ)

ለ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር:-

ከእንግዲህስ መቀሌ ላይ ስለሚሆነውም ሆነ ሆኖ ስላለፍ ተጠያቂው ትሕነግ እንጂ አንተን አይደለህምና…!!!
ከ አሳዬ ደርቤ

ለባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት አገሪቱ በዳግማዊ አጤ ምኒልክ ስትመራ የቆየች ይመስል የአማራ ሕዝብ ሦስት ዓመት ሙሉ በየጉራጉሩ ሲሳደድና ሲታረድ ነበር፡፡ በዚህም ማለቂያ የለሽ ግፍ ተንገሽግሾ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ፊቱን ማዞርም ሆነ ጣቱን መቀሰር የነበረበት የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ቢሆንም…. ከሁሉም በላቀ መልኩ አኩራፊ እና አማጺ ሆኖ የተገኘው ግን በእንክብካቤ የተያዘውና ‹‹ትሕነግ›› የተባለው ነፍሰ-በላ ቡድን ነበር፡፡
ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ‹‹በአብዮት›› ፈንታ ‹‹ሪፎርም›› የሚል ሐሳብ አምጥተህ በሽግግሩ ማግሥት ወደ ቃሊቲ ልትወረውራቸው የሚገባህን ማፊያዎች ቤተ-መንግሥቱ ውስጥ የእራት ድግስ አዘጋጅተህ ከዘረፉት ሃብት ጋር ወደ መቀሌ በክብር መሸኝትህ ያመጣው ጣጣ ነው፡፡
ስለሆነም ፍጻሜያቸውን ለማሳመር ስትሞክር አጀማመርህን አበላሽተህ እንደ አገርህ ስትሰቃይ ሦስት ዓመት ሙሉ አሳልፈኻል፡፡
ምንም እንኳን ለትግራይ ሕዝብም ሆነ ለህውሓት ባለውለታቸው እንጂ ጠላታቸው ባትሆንም ከሃዲው ቡድን ግን አንተን እንደ አሻንጉሊቱ፣ አገርህን እንደ እቃቃ ቤቱ በመቁጠር ፍዳህን ሲያበላህ ነበር፡፡
እንዲያም ሆኖ ታዲያ፡-
➛‹‹አገር ቀርቶ እድር መምራት አትችልም›› እስክንልህ ድረስ፤
➛‹‹ቤተ-መንግሥቱን ይሄን ያህል ካሰማመርክልን አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ፈልግልን›› እየተባለ እስኪቀለድብህ ድረስ፤
➛‹‹ከፌደራል መንግሥቱ በጀት እንጂ ሌላ ትዕዛዝ አንቀበል›› ያሉ ባንዳዎች በእነሱ የሥልጣን ዘመን ሊተገበር ይቅርና ሊታሰብ የማይችለውን ክልላዊ ምርጫ አድርገው አቅም አልባ መሆንህን እስኪገልጹ ድረስ፤
➛ጌታቸው ረዳ የሚባል ዐሣማ ሚዲያ ባገኘ ቁጥር ‹‹መሽረፈት እና ፋሽሽት›› እያለ የስካሩ ማብረጃ እስኪያደርግህ ድረስ፤
➛የዜጎች ነፍስ ከበጎች በታች እስቲሆን ድረስ፤
➛የትግራይ ሚዲያዎች ነግቶ በመሸ ቁጥር አንተን ከመዝለፍም አልፈው የሩዋንዳ እልቂት ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈጸም ዘንድ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ እስኪያደርጉ ድረስ፤
➛የፓርላማ አባላት እንባቸውን እያፈሰሱ ‹‹ሕግ ማስከበር አልቻልክም›› እስቲሉህ ድረስ፤
➛ከትሕነግ እና ከኦነግ ጥቃት ልትጠብቀን ባለመቻልህ የተነሳ እጅግ የምንጠላውን ሃያ ሰባት ዓመት መናፈቅ እስክንጀምር ድረስ፤
➛ደጋፊህ የነበረው ሕዝብ ሥምህን መስማትና ፊትህን ማየት እስኪያስጠላው ድረስ፤
➛ከዜጎችም አልፎ የሐገር ኩራት የሆነው መከላከያ ሠራዊት በካሃዲያን ጥይት እስኪደፈር ድረስ፤
➛እንደ አጠቃላይ በትሕነግና በኦነግ ላይ እርምጃ ባለመውሰድህ የተነሳ የኢትዮጵያውያን ሲቃ➖ የትሕነጋውያን ሳቅ፣ የአገራችን ውድቀትና ፍርሠት➖ የመቀሌ እድገትና ሕድሰት ሆኖ፣ ተከብራ የኖረች አገራችን ሦስት ዓመት ሙሉ የዜጎች መታረጃ ቄራ እስክትሆን ድረስ ብዙ ታግሰኻል፡፡ ለትግራይ ያለህን ክብር ኢትዮጵያን በመገበር ስትገልጽ ኖረኻል፡፡
እናም…
ከእንግዲህስ መቀሌ ላይ ለሚሆነውም ሆነ እስካሁን ድረስ በትግራይ ክልል ለሆነው ትሕነግን እንጂ አንተን ተወቃሽ ለማድረግ የሚያስብ የኢትዮጵያና የትግራይ ሕዝብ ጠላት የሆነው እራሱ ህውሓት ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም…
ይህ የባንዳዎች እና የካሃድዎች ጥርቅም በንጹሃን ሕይወት ላይ የደገሰውን እልቂት አክሽፈህ ዘመቻውን በድል ታጠናቅቅ ዘንድ እመኝልኻለሁ፡፡
Filed in: Amharic