>

የመታረጃ መለያ ኮድ...!!! (ዮሀንስ መኮንን)

የመታረጃ መለያ ኮድ…!!!

ዮሀንስ መኮንን

ፋሺስቱ ናዚ አይሁዳውያንን ሲጨፈጭፍ #J_stamp  የተባለ ምልክት አስቀድሞ በየመታወቂያቸው ላይ አትሞ ነበር::
ሩዋንዳ ውስጥ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከመካሄዱ አስቀድሞ በነዋሪዎቹ መታወቂያ ላይ #ሁቱ እና #ቱትሲ የሚል የዘር መለያ ታትሞባቸው ነበር::
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባደረገው ማጣራት ማረጋገጡን ዛሬ ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት አንዳስታወቀው በማይካድራ ከተማ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙት የከተማዋ ፖሊሶች ሚሊሻዎች እና “ሳምሪ” የተባለው የትግራይ ወጣቶች ኢመደበኛ ቡድን ናቸው! (የህወሓቱ “ሳምሪ” እንደ ሩዋንዳው “ኢንተርሃምዌ ሚሊሻ” መሆኑ ነው)
ከጥቅምት 30 ከቀኑ 9 ሰዓት እስከ ቀጣዩ ቀን ጠዋት ድረስ በቀጠለው ጭፍጨፋ፣ የ“ሳምሪ” (ኢንተርሃምዌ) ቡድን አባላት ነዋሪዎችን #አማራ እና #ወልቃይቴ ብለው በመታወቂያቸው ለይተዋል፤ ከዚያም በሚሊሻ እና በፖሊስ እየታገዙ:-
– በጩቤ በመውጋት
– በፋስ መጥረቢያ በመፍለጥ
– በገመድ በማነቅ
– በገጀራ በመቆራረጥ
– በዱላ በመቀጥቀጥ እና
– በእሳት በማቃጠል በትንሹ 600 ሰዎችን በፍጹም አረመኔያዊነት ጨፍጭፈዋል::
ህወሓቶች የኢትዮጵያውያን መታወቂያ ላይ የብሔር ማንነታችንን የጻፉት ለዚህ ክፉ ቀን እያዘጋጁን ነበር:: ፈጣሪ ቀደማቸው እንጂ እነርሱማ ሀገራችንን በደም አበላ ሊያጥቧት ተዘጋጅተው ነበር::
አሳዛኙ እውነት ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያውያን በህወሓት የታደላቸውን የመታረጃ መለያቸውን #መታወቂያ ብለው በብብታቸው ታቅፈው መዞራቸው ነው!  “የብሔር ፌደራሊዝም” የተባለው የፖለቲካ አደረጃጀትም ህወሓት ለወደደችው ለአንገቱ የወርቅ ሀብል ለጠላችው ካራ ለመሸለም ያዘጋጀችው መሆኑን በተግባር እያየነው ነው!
ህወሓትን መደገፍ ይህንን ሁሉ ግፍ እንዳላዩ ሆነው ማለፍ አልያም ተባባሪ መሆን ነው:: ይህ ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ይሆናል እንጂ ሁሉም የህሊናም የሕግም ተጠያቂ ከመሆን አያመልጥም::
Filed in: Amharic