>

"ሕወሓት እና ኦነግ ሽኔ ለምንድነው በሽብርተኝነት የማይፈርረጁት? ምንድነው የቀረው? ሽብርተኝነት ከዚህ በላይ ምንድነው?" (ያሬድ ሀይለማርያም)

“ሕወሓት እና ኦነግ ሽኔ ለምንድነው በሽብርተኝነት የማይፈርረጁት? ምንድነው የቀረው? ሽብርተኝነት ከዚህ በላይ ምንድነው?”

ያሬድ ሀይለማርያም

የሽብርተኛው ሕወሓት የፋይናንስ ድርጅቶችን በህግ ለመጠየቅ መንግሥት  ምን ያህል ቁርጠኛ ነው? 
2ኛ/ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ፤ በተለይም UN በማይካድራ እና በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የተፈጸሙትን በሰው ዘር ላይ የተነጣጠሩ እና የጦር ወንጀሎች የራሱን ባለሙያዎች ልኮ እንዲያረጋግጥ መጋበዝ፣
3ኛ/ የህውሃት ባለሥልጣናት፣ የጦር አበጋዞቻቸው እና የኦነግ ሽኔ አመራሮች (ሁሉም የሚታወቁ ከሆነ) በአለም አቀፍ ተፈላጊ ወንጀለኞች ዝርዝር ውስጥ እንዲገቡ እና አለም እነዚህን ሰዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ትብብር እንዲያደርግ መጠየቅ፣
4ኛ/ እነዚህ በስም እና በፎቶ ተለይተው የሚፈለጉ የከፍተኛ ወንጀል ተጠርጣሪች ድርጊታቸው የአለም አቀፉን ሕግ ጭምር የጣሰ እና በአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ጭምር የሚያስከስስም ስለሆነ ወደ የትኛውም አገር አምልጠው ቢሰደዱ ወይም ከጦርነቱ በፊት ቀድመው የተሰደዱም ካሉ አገራት አሳልፈው ለኢትዮጵያ መንግስት እንዲሰጡዋቸው መጠየቅ እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኖች ድርጅትም በስደተኝነት ተቀብሎ እንዳይመዘግባቸው ማሳሰብ፣
5ኛ/ በጦርነቱ የደረሱ ጉዳትች ዝርዝር መግለጫ እና የተገኙ ውጤቶች፤ በተለይም እስከ አሁን ምን ያህል ሰውና እነማን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ይገለጻል ብለን እንጠብቃለን።
ቸር ያሰማን!
Filed in: Amharic