>
5:13 pm - Tuesday April 20, 6556

‘’ታምራዊ የውጊያ ስልት አላቸው‘’ (ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ)

‘’ታምራዊ የውጊያ ስልት አላቸው‘’

ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ


የህወሐት አፈ – ቀላጤዎች ለሶስት አስር አመታት ሚዲያውን ተቆጣጥረው ስለ ወታደራዊ ብቃት ሲያላዝኑብን ነበር፡፡ ዳሩ ግን በጦር ሜዳ ውሎ የሚያውቋቸው አንጋፋ የጦር – ሜዳ አርበኞች የህወሐት የጦርነት አቅም በትክክል ያውቁታል፤ ባዶ ጩኸት እንደሆነ፡፡ ጦርነትን በተንኮል እና በሸፍጥ እንጅ በጀግንነት እንዳላሸነፉ ብዙ ተብሏል፡፡አንጋፋው ጀነራል ካሳዬ ጨመዳ በቅርቡ የተናገሩትን እንደማሳያ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህወሐቶች

       ‘’ ድሮም አቅምና እውቀት ሳይሆን ባዶ ትምክህት ነው የነበራቸው፤በትምክህት የደነደነ ማንነት ነው ያላቸው፡፡ የደርግ መንግስት ሊሸነፍ የቻለበት ምክንያትም በደርግ ስህትት እና በውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት እንጅ ወታደራዊ ብቃት ያልነበራቸው ቡድኖች ነበሩ’’

በተመሳሳይ ሁኔታ አሁን የሚካሄደውን ውጊያ የሚመሩት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል መሰለ መሰረት የሚከተለውን ብለዋል፡ 

      ‘’ ከእኛ ውጭ መዋጋት የሚችል የለም ሲሉ የነበሩ የህወሐት ጀነራሎች አብረን ሰርተናል እንተዋወቃለን፤ የውጊያ መሀንዲሶች እኛ ነን ሲሉ ነበር፡፡ ከእነርሱ በላይ መስራት እንደምንችል አረጋግጠናል ‘’

እውነታው ይህ ሁኖ እያለ ለወሬ እና ለሚዲያ ፍጆታ ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው፤

ጦርነት መስራት እንችላለን የሚሉ አባባሎች በባዶ ማንነታቸው እውነትን የያዙ አስመስሎታል፡፡  የጦር ሜዳ ውሎን፣ ጀግንነትን በማነብነብ ሳይሆን በገቢር ወይም በድርጊት ማሳየት የማይችሉ  ባዶ ማንነትን በወሬ እና በተንኮል መገንባት የሚፈልጉ ኃይሎች ነበሩ፡፡ የህወሐት የጥፋት ኃይሎች ማየትም፣ ማሰብም ተስኗቸው እንጅ የአማራን የተጋድሎ ብቃት ከድርሳናት መረዳት ይችሉ ነበር፡፡ በቅርቡ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚኒሻው መከላከያ ሰራዊቱን ከጥፋት ኃይሎች የታደገበት ተጋድሎ ለታሪኩ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚኒሻው ከመከላከያው ጎን ሁኖ ያሳየው ጀግንነትም ታሪካዊ ማንነቱን ያስመሰከረ ነው፡፡ ይህንን ጀግንነቱን ከመሰከሩለት የጦር ሜዳ አርበኞች መካከል አንድ የደቡብ ኢትዬጲያ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባል ስለ አማራ ልዩ ኃይል እንዲህ ነበር ያለው፡

ሌት ከቀን ያገለገልናቸው(አንበጣ በማባረር፣ ሰብል በመሰብሰብ፣ ገበሬዎችን በማገዝ) የትግራይ ልዩ ኃይሎች  ሌሊት በተኛንበት  ሲወጉን ምንም ያላደረግንለት የአማራ ልዩ ኃይል  ከእገታ ታደገን፡፡ 

የአማራ ልዩ ኃይል ክላሽኮፍ ይዘው እንደ ስናይፐር ይተኩሳሉ፤ በፍጥነት ያጠቃሉ፣ ታምራዊ  የሆነ የውጊያ ስልት አላቸው፡፡ ሶስት ቀናት ይወስዳል የተባለውን ወጊያ በሰባት ስዓታት ይጨርሱታል፡፡ ኢላማ ሲመቱ ልዩ ናቸው፤ እጅግ ፈጣን ተዋጊ ናቸው፡፡ ሀያ ሶስት  ዓመታት በመከላከያ ሰራዊት ቆይቻለሁ፣ እንደነዚህ የሚመስሉ ተዋጊዎች አይቸ አላውቅም፡፡  የወጊያ ቀጠናቸው ከግራና ከቀኝ ቢሆንም የተሰጣቸውን የወጊያ ቀጠና አጥቅተው መሀል ላይ ይገኛሉ፡፡  

ከኤርትራዊያን ጋር በባድመ፣ አሁን ደግሞ ከትግራውያን ጋር እተዋጋሁ ነው፡፡ ሁለቱም በደፈጣና በቆረጣ ውጊያ ድንቅ ናቸው፤ በፊት ለፊት ውጊያ ግን ያን ያህል አይደሉም፡፡ የአማራ ልዩ ኃይል ግን በሁሉም የውጊያ አይነቶች ተወዳዳሪ የላቸውም፡፡ 

ጀብድ ለመስራት ካላቸው እምነት የተነሳ የጠላት ጦር ይበረታባቸዋል በተባሉ የውጊያ ቦታዎች ላይ ምሽጎችን ለመደርመስ ይሽቀዳደማሉ፡፡ ታምራዊ የውጊያ ስልት አላቸው፡፡ በፍጥነት ያጠቃሉ፤ ፈጣን ተዋጊ ናቸው፡፡  በውጊያው ላይም ከእነርሱ ወገን የሚጎድል ብዙም የለም፡፡ 

ታምራዊ የውጊያ ስልት አላቸው፡፡  ፈጣን ተዋጊ ናቸው፡፡ ወታደራዊ ስልጠና ብቻ እንዲህ ብቁ አያደርግም፤ አንዳች በትውልድ የሚተላለፍ ድፍረትና ብልኃት ቢኖር እንጅ ‘’

በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሜን ዕዝ የ5ኛ ክፍለ -ጦር አዛዥ ብርጋዴል ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ  ስለ አማራ ልዩ ኃይል  እንዲህ ነበር ያሉት፡

‘’ ነውረኛው የህወሃት  ኃይል በሌሊት ሲረሽኑን፣ በዳንሻ ላይ በህወሃት  ኃይል በተከበብንበት ጊዜ የአማራ ልዩ ኃይል ነው የታደገን፡፡  የአማራ ልዩ ኃይል ጀግንነት ለመስራት  ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡  የስነ ልቦና ጥንካሬ እንጅ የመሳሪያ ብዛት እና ጥራት ለስኬት አያበቃም ‘’

አዳነች አመንቴ የ22ኛ ክፍለ ጦር አባል  በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲህ  ነበር ያለችው፡ 

‘’ ጥቃት ከተፈፀመብን በኃላ የአማራ ልዩ ኃይል ነው ነፃ ያወጣን፡፡ የአማራ ልዩ ኃይል ከኃላ ገብቶ የጠላትን ጦር ደመሰሰልን ‘’

ይህ የጀግንነት ተምሳሌት የሆነ ድል የህወሐት ቢሆን ኑሮ ለዘመናት ሲያፏጩብን ይኖሩ ነበር፡፡ እንኳን እንዲህ አይነት ድል አስመዝግበው በባዶው ጩኸት ይወዳሉ፡፡ በዘር መድሎ ያበዱ ጎጠኞች አማራን አንገቱን ሊያስደፉት ቢጥሩም አማራ ግን ጀግንነቱ የማንነቱ ምሰሶ ነው፡፡ የአማራ ልዩ ኃይል ለሀገር  እና ለህዝብ መድህን መሆን የቻለ ኃይል ነው፤ ይሄ ደግሞ የተገነባበት የስነ-ልቦና ውቅር ውጤት ነው፡፡ ክብርና ምስጋና ለአማራ ልዩ ኃይል፣ ለአማራ ሚኒሻ እና ለመከላከያ ሰራዊታችን፡፡

አማራነት እንዲህ ነው፡፡ አማራነት ጀግንነት ነው፤ አማራነት ሆደ – ሰፊነት ነው፤ አማራነት አቃፊነት ነው፤ አማራነት ታጋሽነት ነው፡፡ በአማራ ክልል የኦሮሞ እና ሌሎች ኢትዩጲያውያን ዜጎቻችን መብታቸው ተክብሮ፣ ሳይሸማቀቁ፣ ንብረት አፍርተው ይኖራሉ፡፡ አማራ ስልጡን ህዝብ ነው፡፡ ሰርቶ መለወጥን፤ አብሮ መኖርን ያውቅበታል፡፡ ይህን ያልተረዱ በሌብነት እንጀራን በልተው ያደጉ ፅንፈኞች በኦሮሚያ፣ በቤንሻጉል – ጉምዘ፣ በደቡብ፣ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በአማራ ተወላጆች ላይ ላደረሱት  እና ለሚደርሱት ጥቃት የአማራ ህዝብ በዝምታ የሚታገሰው ግጭትን ወይም ጦርነትን ፈርቶ ሳይሆን ከሌሎች ወንድም ከሆኑ ኢትዩጲያውያን ጋር አብሮ ለመኖር እና ኢትዩጲያዊ አንድነቱን ለመጠበቅ ብሎ ነው፡፡  

ከዚህ በኃላ ግን የአማራን ህዝብ እወክለዋለሁ የሚለው አመራር የአማራን ህዝብ እንባ እና ግድያ ሊያስቆም ይገባል፡፡ ከትናንት ዛሬ ይሻላል ብለን ስርዓቱን ስንጠብቅ አማራነት የነገር ማሞቂያ ሁኖ የክፋት ኃይል እና የዘረኞች ተንኮል ማስተናገጃ የሚገለጥበት ህዝብ እየሆነ መጥቷል፡፡ ዛሬም በበቤንሻጉል – ጉምዘ ዜጎች የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ይሄ ግን በቃ ሊባል ይገባል፡፡ የአማራ ብልፅግና የሚጠበቅበትን ሚና ሊወጣ ግድ ይለዋል ያለበለዚያ የአማራን ልዩ ኃይል ልብ እና ጀግንነት ለተላበሱ አመራሮች ቦታውን መልቀቅ ይገባል፡፡

Filed in: Amharic