>
5:13 pm - Thursday April 18, 4222

ጠቅላይ ሚንስትር አብይን በማገዙ ላይ ብናተኩር .... (አሰፋ ታረቀኝ)

ጠቅላይ ሚንስትር አብይን በማገዙ ላይ ብናተኩር….

 

አሰፋ ታረቀኝ


“ ለጉድ የጎለተኝ” የጎረበታችን የእማማ ዘምዘም አባባል ነበር፡፡ እሳቸው በህይወት እያሉ እህት ወንድሞቻቸው ብቻ ሳይሆኑ፣ ልጆቻቸውንም በሞት ስለተለዩ የሚጠቀሙበት አባባል ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ‘ኦሮሚያ’ የምትባል ሀገር ለመመሥረት አልሞ የተነሳው ኦነግ፤ ያንን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሰውልጅ ታሪክ ውስጥ ለጨካኝነቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ድርጅት አጅቦ አድስ አበባ የገባበት ዘመን 30 አመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ይቀሩታል፡፡ “ፍቅር እስከመቃብር’ እንዲሉ ኦነግ ህዋህትን አጅቦ አዲስ አበባ በማስገባት ብቻ ሳይወሰን ወደመቃብርም አብሯት ወርዷል፡፡ ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደነገሩን፤የኦነግ ‘ወታደሮች’  ባንዲራችን ያሉትን ምልክት ተሸክመው ከህዋህት ገዳይ ቡድን ጋር ሆነው የኢትዮጵያን መለዮ ለባሽ ባለፉት የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ያልተመዘገበ የጭካኔ አይነት ፈጽመውበታል፡፡ ምስክርነቱን የሰጡት ደግሞ በጭንቅ ቀን ጥሪ ከተደረገላቸው ኦሮሚኛ ተናጋሪ ጀኔራሎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ የ ‘ነፍጠኛ ተረት ነው’ ለማለት አያመችም ለማለት ነው፡፡

የጦር ሐይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄኔራል ብርኅኑ  ጁላ፤ ሰሞኑን አዲስ አበባ ላይ በተደረገ ስብሰባ ታላቋ ኢትዮጵያ፣ ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ፣ ይህችን ታላቅ ሀገር፣ እያሉ ሲያሽሞነሙኗትና የሰራዊቱን ስብጥርነት ከአዲስ አበባ ኗሪ ጋር ሲያመሳስሉት፣ በጎሳ ፖለቲካ ላይ የሞት ፍርድ እንደታወጀበት ቆጠርኩት፡፡ ለጉድ የጎለታቸውም ኦነጎች፣ ‘በኢትዮጵያ መቃብር ላይ’ የምትመሰረተውን ‘ኦሮሚያ’ ሳያዩ መጠጊያቸውና አሰልጣኛቸው ሕዋህት እስክወዲያኛው ላይመለስ አሸለበ፡፡ አጨራረሳቸውን እንደአጀማመራቸው ያሳምርላቸውና፣ ከኦሮሞ ብሄረሰብ የወጡት የኢትዮጵያ ጄኔራሎች፣ ኢትዮጵያ አትፈርስም አሉ፡፡ አዎ የሩቁም የቅርቡም ከኦሮሞ ብሄረሰብ የወጡ ጀግኞች ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር በደም ባጥንታቸው ኢትዮጵያን ሲያስከብሩ እንጅ ሲክዷት አልተመዘገበም፡፡ ሰሞኑንም የሆነው ይኽው ነው፡፡

የዛሬ 125 ከውጭ የመጣን ወራሪ ለመመከት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ በጋራ ወድቆ በሠራው ታሪክ ነጻነቱን ለትውልድ አስተላልፎ አለፈ፡፡ ያሁኑም ትውልድ በጋራ ተሰውቶ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለምሥራቅ አፍሪካ ሥጋት የነበረ ጸረ የሰው ልጅ የሆነን ድርጅት፣ ብትትኑን አውጥቶታል፡፡ ለጉድ የጎለተው ኦነግ ቁጭ ብሎ እያየ ክአርባ አመት በላይ የለፋበት ኢትዮጵያን የመበተን አላማ እነሆ ወደ መቃብር ወረደ! ዕቅድህ ሞቶ አንተ በህይወት ልትኖር ትችላለህ፡፡ የፖለቲካ ሞት ይሏል ይህ ነው፡፡ ችግሩ የኦነግ ሰወችና አሞጋሾቻቸው ኦሮምኛውን እንጅ ኦሮሞን አያውቁትም፡፡ ኢትዮጵያን ለመፈታተን ትነስቶ የተሳካለት የለም፡፡ “እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም” አይደል የሚል ምጽህፉ፡፡ የፍጥረቱ አካል ነችና ኢትዮጵያንም ይሚጠብቅ አይተኛም፡፡ አድስ በማቆጥቆጥ ላይ ያለውም የ “አማራ” አክራሪ ቆም ብሎ ቢያስብበት ይሻለዋል፤ የኦነግ ርዝራዦች ጋር አተካራ መግጠሙን ገታ አድርጎ ጠቅላይ ሚንስትር አብይን በማገዙላይ ቢያተኩር የሚመኛትን ኢትዮጵያ በቅርቡ ያያታል፡፡

 

 

Filed in: Amharic