>

የመተከል እልቂት ትክክለኛ ምክንያት የኦሮሙማ ተስፋፊነት ፕሮጀክት ነው.. .!!! (የአማራ ብልፅግና አመራር እና የክልሉ ካቢኔ አባል ሲ/ር ብዙአየሁ ቢያዝን)

የመተከል እልቂት ትክክለኛ ምክንያት የኦሮሙማ ተስፋፊነት ፕሮጀክት ነው.. .!!!

የአማራ ብልፅግና አመራር እና የክልሉ ካቢኔ አባል ሲ/ር ብዙአየሁ ቢያዝን


ከያሶ ወረዳ ወደ ድባጤና ቡለን የሚደረግ መስፋፋት አለ!! በካማሽ ዞን የምትገኘው ያሶ (Yaso) ወረዳ ከፊል ግዛቷ በኦሮሚያ ስር የተጠቃለለ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ በመነሳት ብቻ የወረዳዎቹን አከላለል እናጢናቸው። መተከል ውስጥ አባይን ተሻግሮ ያሉት ድባጤ፣ ቡለን እና ወምበራ ወረዳዎች ከቤንሻንጉል ጉሙዝያሶ ወረዳ እንጅ ከኦሮሚያ ጋር ድንበር አልነበራቸውም። የያሶ ወረዳ ክፍል ከተጠቀለለ በኋላ ግን የኦሮሚያ ድንበር አባይ ድረስ ሆኗል። 

በወቅቱ ሁኔታውን የፃፈው Getahun kassahun እንዲህ ብሎ ነበር።

“The Oromia Region has annexed parts of the Benshagnul-Gumuz (BG) areas adjacent to the Abay River by stealth and are now administered by so called Oromia region. In the process, they forcefully displaced Gumuz residents from their places. For example, I have confirmed about 730+ Gumuz people were forced to flee to the low-laying areas of Womberma Woreda of Gojjam (metekel) across Abay River. ” 

በያሶ የሚኖሩጉሙዞች በኃይል ከተፈናቀሉ በኋላ በወረዳዋ ሰፊ ቁጥጥር እየተካሄደ መሆኑን አካባቢው ላይ ያሉ ሰዎች ሲገልፁ ይታያሉ። በተጨማሪም ኦነግ መተከል ላይ ፅ/ቤት በመክፈቱ በርካታ ታጣቂዎቹ ሰርገው ወደ መተከል በመግባት በወንበራ፣ ቡለን እናጉባ ወረዳዎች በዋናነት የአማራ፣ አገውና ሺናሻ ነዋሪዎች ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ጥቃት በመፈፀም መተከልን የመውረር ስራው ቀጥሏል። በመተከል ከሚደርሰው ጥቃት ጀርባ ኢ_መደበኛው የኦሮሚያ ታጣቂ ከሌሎች ኃይሎችና አኩራፊዎች ጋር በመተባበር የሚፈፀም ነው። በገንዘብ ተገዝተው ቀዮችን ግደሉ የሚባሉ እና ለጥቃት የሚሰለፉ ታጣቂዎዎችም አሉ።

“መተከል የኛ ነው” የሚለውንየኦነግ ትርክት ለማሳካት አላማ ያደረገ ፣ የታሰበበትና የታቀደ ኦፕሬሽን ነው የሚመስለው። በተጠቀለሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አካባቢዎችየኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ነው። አሁን በሌሎች የመተከል ወረዳዎች ጭምር የነበረውን ጥቃት ወደ ያሶ አጎራባች የአባይ ዳርቻ ወረዳዎች ሙሉ ትኩረት ሰጥቶ በንፁሐን ላይ ጥቃት በመክፈት የድባጤና ቡለን ወረዳዎችን የመቆጣጠር ሴራው መቀጠሉን እየነገሩን ነው።

ከዚህ ቀደሙ እርምጃ በተለየ የሽናሻና ሌሎች ብሔረሰቦች ጭምር እየተገደሉ አካባቢውን እንዲለቁ እየተደረገ መሆኑ የጥቅለላ አጀንዳው የሞት ሽረት ተደርጎ መወሰዱን የሚያሳይ ይመስላል። ምናልባት ከሰሜን ዘመቻ መልስ ይዘመታል በሚል ቀድሞ የመቆጣጠር ሩጫም ይመስላል።

አሳዛኙ ነገር በዝቅተኛ ገንዘብ ተገዝተው ቀይ መግደልን አላማ ያደረጉ ቀስት ወርዋሪዎች እንዳሉት ሁሉ የወረዳ አመራሮችም የዚሁ አላማ ተሰላፊ ሆነው ህዝብ እያስጨፈጨፉ መገኘታቸው ነው።

በቀጣይ ልክ ከሱማሊ አዋሳኝ አካባቢዎች ጋር ሲደረግ እንደኖረው አይነት በሕዝበ ውሳኔ (Referendum) ድንበሮች ይለዩ የሚል “ሰላማዊ መፍትሔ” ብሎ ነገ ኦነግ ሽኔ አያፍርም ብቻ ሳይሆን የሀሳቡ ተጋሪ አያጣምና ሊያቀርብ ይችላል የሚል ግምት አለኝ!

የዚህን መነሻና መዳረሻ ይዘህ እና ኢትዮጵያን እያሰብህ፣ በጉዳዩ ላይ ምንም የማያውቁ የንፁህ ኢትዮጵያውያን የሞትና የእልቂት ምክንያት መርምረው። ችግሩ ከላይ ከገለፅሁት እንደሚመነጭ ወይም ሌላ የሚሳበበት ሀይል የሚሰራው ተንኮል ነው /አይደለም( አይ፣አወ ) ብለህ ብዕርህን አንሳ፣ በዚህም በንፁሐን ሞት የሚሰቃየው ህዝባችን የኢትዮጵያውያንና የአለም ጆሮ እንዲያገኝ አድርግ!!

  ክብር ለእውነተኛና ለሀቀኛ ጀግኖቻችን!!!

  ሲስተር ብዙአየሁ ቢያዝን Bizuayehu Biazen 

የአማራ ክልል ገቢወች ቢሮ ኃላፊ።

Filed in: Amharic