>

ስለተፈቱት ደስ ብሎን ስለታሰሩት እንጮሀለን...!!! (መኳንንት ፋንታሁን)

ስለተፈቱት ደስ ብሎን ስለታሰሩት እንጮሀለን…!!!

መኳንንት ፋንታሁን

✍️በሃገራችን ለሰላማዊ የትግል ዘዴ ምሳሌና ፈርቀዳጅ ጥራ ብባል የመጀመሪያየም የመጨረሻየም እስክንድር ነጋ ነው።ሌላው ሲደላው በእጁ ሲቸገር በሹካው የሚጫዎት ነው።
በአውሬያዊ ፖለቲካ መካከል የብሕትውና ፖለቲካ የሚያራምድ የክፍለ ዘመናችን የፖለቲካዊ ቅድስና አሻራ ነው እስክንድር።
በብልጣብልጦች መካከል በበግነት የሚጓዝ የሸላቾቹን ነውር መልሶ የሚሸልት ምሳሌያዊ በግ እስክንድር ነጋ።
ተስፋ ከልቡ የማይጠፋ የተስፈኞች ቀዳሚ መሪ።
ለሸርና ለተንኮል ያልተፈጠረ የበከተውንና የቆሸሸውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምሳሌ ሆኖ ለማከም የሚታትር የዘመን ክስተት እስክንድር ነጋ።
በአካለ ስጋ ታስሮ በመንፈሰሰ ነፃ የሆነ ምስጢራዊ ሰው አሳሪዎቹን በአካል ነፃ ሆነው እያየ ግን የመንፈስ እስረኛ አድርጎ የሚያቃዥ ተአምራዊ ሰው እስክንድር።
#
ይኸ ሰው የኢትዮጵያ political justice ማንጠሪያ ነው። ታላቁን ንጹሁንና የዋሁን እስክንድር አስሮ ሽህ ወሬ ቢደረደር ሽህ መፍትሔ ቢደሰኮር አሉቧልታ መሆኑ ለብዙዎቻችን ክሱት ነው።
የሚሻለው የተሻሉ ጭንቅላቶችን ፈትቶ በተሻለ ሃሳብ የተሻለ ሃገር መገንባት ነው።
ከዚህ ውጭ የግል እስረኛ አስቀምጦ ተቋም ግንባታ ላይ እንሰራለን 10 አምዶችን አቁመናል የሚል ጅኒጃንካ የእምቧይ ካብ ከመካብ ምጥጥን ነው።
ሁሉም የዘራውን ያጭዳል።
ኃላፊነት እንደሚሰማው የሃገር ዜጋ በድጋሚ እጠይቃለሁ እስክንድር ነጋና በግፍ የታሰሩ ንጹሃን እጆች ይፈቱ።
Filed in: Amharic