>

"እርፍ ተጨብጦ ወደኋላ አይታረስም ..." (መስቀሉ አየለ)

“እርፍ ተጨብጦ ወደኋላ አይታረስም …”

መስቀሉ አየለ

ወያኔ አንድ ብሎ እግሩን ወደ መሃል አገር ማስገባት ሲጀምር የመጀመሪያ ስራው ያደረገው የእዚህችን አገር ግማደ መስቀል ተሸክሞ እዚህ የደረሰውን አማራን በሁሉም በኩል እንዴት ማዳክም እንደሚችል ሮድ ማፑን ከእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ተቀብሎ እንደ ወረደ በመተግበር እንደነበር ብዙ ግዜ ጽፈንበታል። ይኽም ሲባል አንዱ መንገድ አማራው በዋናነት የሰፈረባቸውን ይዞታዎች በሁሉም አቅጣጫ በመከርከም እንዲት የፌስታል ጭምብል ማሳከል ሲሆን ከወሎ እራያን እና ከጎንደር ወልቃይት(ሁመራን) ወደ ትግሬ እንደከለለው ሁሉ ከፊል ሸዋን ወደ ኦሮሞ እንዲሁም ከጎጃም መተከልን ወስዶ ቤንሻንጉል የሚባል ያልነበረ ክልል መፍጠሩ ይታወቃል። ወልቃይትና እራያ ግዜውን ጠብቆ መልስ ሲያገኝ የመተከልና የሸዋው መሬት ጉዳይ ግን ቀጣዩ የፍጥጫ ግንባር እንደሚሆን አይካድም።
የኦነግን ልብና ኩላሊት አስገጥመው መሃል አዲስ አበባ ላይ ጉብ ያሉት የወቅቱ ምንደኞች መተከልን በተመለከተ ማልቃቀስ የጀመሩበት ጉዳይ ግልጽ ነው። መቸም እንደ ዮናታን እረጋሳ ከመሳሰሉ ካድሬዎች እስከ ብርሃኑ ጁላ ድረስ ያሉት ባለ ሁለት በኩል ጃኬቶች ምን ያህል እየተናበቡ መሆኑን ሁኔታዎች እንደሚያሳብቁ ለማንም የተሰወረ አይደለም። በተለይ ዮናታን ተስፋዬ እረጋሳ የጠቅላይ ሚስትሩ የፌስቡክ ፔጅ አድሚን መሆኑን ጠንቅቀን ለምናውቀው ሁሉ አንዳንድ ግዜ ይህ ግምኛ ሰው እየወጣ የሚዘረግፋቸውን እስትራቴጅካል የሚመስሉ ሴራዎች የእራሱ የአክቲቪስቱ የግል አቋም ብቻ አድርገን ለመውሰድ ቢቸግረን የሚገርም አይሆንም። ተወደደም ተጠላም በመተከል ጉዳይ እርማችሁን ብታወጡ ይበጃችኋል።አራት ነጥብ!
Filed in: Amharic