>
5:26 pm - Saturday September 15, 9240

የኦሮሚያ አመራር ስውር እጅ (አምሀራ ኢንፎርመር)

የኦሮሚያ አመራር ስውር እጅ

-አምሀራ ኢንፎርመር

 

በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለው ዘር ማጥፋት በኦሮሚያ መንግስት ወኪሎች እና ድጋፍ የሚፈፀም ስለመሆኑ የሚነግረን ማረጋገጫ አለ ወይ?
1)  በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለው ግድያ ጭካኔ የሽብር ማሳያ ነው። በመንግስት ከሚደገፍ የዘር ማጥፋት ሽብር ፅንሰ ሀሳቡ ጋር የሚሔደው minorities (ጌዲዮ: ጋሞ: ወዘተ) እና አማራን  target ያደርጋል። ማንነት የመረጠ Genocidal ነው። ጅምላ ግድያ : አፍኖ ገንዘብ መጠየቅ (ሰሜን ጎንደር) : እገታ (የተማሪዎች) ወዘተ የሚነግሩን ነገር አለ።
 
2) ቡድኖቹን shelter በማድረግ በኩል 5ሺህ የሸኔ ሠራዊት በኦሮሚያ አለ። ተበትኗል ይባላል ግን ቤጉን  ÷ ደቡብን ÷ ሱማሌን ÷ አማራ ክልሎችን እያጠቁ ዝም ተብለዋል።
በወለጋ ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ስልጠና ሲወስዱ ሲያስመርቁ ይታወቃል። በኦነግ ልሳን ONN Tv ሲገለፅና ሲታይ ነበር። 
 
3) የታጣቂ ቡድኑ ጥቃት የሚፈፀመው በODP ፈቃድና ትዕዛዝ መሆኑን ጀነራል ከማል ገልቹ በ2011 በLTV መስክሯል። ያንን በመቃወሜ ተባረርኩ ነው ያለው። ለጥምረታቸው መፍረስ ምክንያቱ ታጣቂ የሚመራው ኦነግ እንዴት ይዋሃዳል በሚለውና ታጣቂ ኃይል ስላለኝ 40% ድርሻ ልያዝ በማለቱ እንደሆነ በግልፅ ነግሮናል።
 
▪ ባንኮች የሚዘረፉት በODP ደብዳቤ እንደሆነ መስክሯል።
 22 የባንክ ቅርንጫፎች ተዘርፈው ምንም አልተባለም።  ፊንጫ ስኳር ለሁለት አመት እነሱን ሲቀልብ እንደነበር ሰሞኑን ሰምተናል። 
 ▪ትጥቅና ሎጂስቲክስ ከመንግስት ሠራዊት ሳይቀር ለታጣቂው እንደሚቀርብ ተገልጿል። ከህወሓትም ድጋፍ እንደሚቀርብ ተነግሯል። በይፋ ፎቶ ግራፍ እያነሱ ይለጥፋሉ። 
 
4)  በታጣቂው ላይ የሚደረጉ operations የሚድበሰበሱ ናቸው። ሽምግልና የሚባለው የታጣቂውን የስነምግባር ችግር ከማረም ያለፈ አልመስል እያለ ነው።
 ▪ የምዕራብ ዕዝ መቀመጫ የተለወጠው ለምን ነበር? አመት ሙሉ ወለጋ የከረመው ምዕራብ ዕዝ ምን አደረገ?
 
5) የኦሮሚያ አክቲቪስትና የፖለቲካ ኃይል በዚህ ታጣቂ ዙሪያ የሚያወግዘው ነገር የለም። እንዲያውም መንግስት እርምጃ ልውሰድ ሲል ይጮሃሉ። ለምን? አንዳንዶች : ኦሮሞም እየተገደለ የማንናገረው ለህይወታችን ሰግተን ነው ብለዋል።
 
6) አማራ እና ኦርቶዶክስን የመሰሉ ተቋሞች ኦሮሚያን እንዲለቁ  አሊያም  ተለውጠውና “ኦሮሞ ነን” ብለው እንዲኖሩ ለማድረግ  የሚሠራው ግድያ  እና አስተሳሰቡ የstate sponsored terrorism ፍላጎት ግልፅ ማሳያ ነው።
▪በአቶ ሽመልስ አብዲሳ ይፋ የሆነው ያ ሁሉ እቅድ ምን ይነግረናል? 
▪ በሻሸመኔ ጉዳይ ተከሳሹ ከንቲባ ለአቶ ሽመልስ ደጋግሜ ስደውል እና ከተማውን እናድነው ስለው ” አርፈህ ተኛ” አለኝ ማለቱ ምን ይነግረናል?
▪ታጣቂው ወለጋ ከሆነ  : ሰላሌ ድረስ ታጥቀው መጥተው መንገድ ዘግተው የሚገድሉት እንዴት እና በየት አልፈው ነው? 
▪ከወለጋ በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ አልፈው አጣዬና ከሚሴ ደርሰው ሰው የሚገድሉት እና የሚዋጉት ያለመዋቅር ድጋፍ ነው ወይ?
 
7)  ታጣቂው በሰሜን ሸዋና አጣዬ ኦነግ ወረራ በፈፀመበት ወቅት የኦሮሚያ ምስራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ “የአማራ ድንበሩ ቡልጋ ነው” ብሏል የሚለው መረጃ ምን ይነግረናል።
 
▪ የታገቱ ተማሪዎች ዳና መጥፋት እና የሕግ ሒደት እየተካሔደ ነው መባሉ ምን ይነግረናል? 
 
8) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘በአሜሪካ በዚህ አመት የሞተው በኢትዮጵያ በአምስት አመታት ከሞተው ስለሚበልጥ አታራግቡት’ ማለቱ ምን ማለት ነው?
▪ “እኔ እንደሆነ አንድም ሰው አፈናቅዬ አላውቅም” ሲለን ለምን ነበር?
▪ በኦሮሚያ ከ30 ዙር በላይ
Filed in: Amharic