>

"የጁንታው አመራሮች ያሉበትን  ለጠቆመ ግለሰብ 10 ሚሊዮን ብር ይሰጣል...!" (የመከላከያ ሚኒስቴር)

“የጁንታው አመራሮች ያሉበትን  ለጠቆመ ግለሰብ 10 ሚሊዮን ብር ይሰጣል…!”

የመከላከያ ሚኒስቴር

ተፈላጊ የህወሃት ጁንታ አመራሮች  ያሉበትን ለጠቆመ ግለሰብ 10 ሚሊዮን ብር እንደሚሰጥ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በመከላከያ ሚኒስቴር የህብረት መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ ጉዳዩን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ በመግለጫቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት የጁንታው አመራሮችን በፍጥነት ለህግ ለማቅረብ የሚያስችለውን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት።
አሁን ላይ የጁንታው አመራሮች በእግር በመሸሽ በተለያዩ ጫካዎችና ዋሻዎች እራሳቸውን ደብቀው እንደሚገኙና ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
ከዚህ አንጻር የጁንታውን አመራሮች ያሉበትን ለሚጠቁም ግለሰብ 10 ሚሊዮን ብር ይሰጣል ብለዋል።
ENA
Filed in: Amharic