የጠ/ሚ አብይ በመቀሌ መገኘት ትላንት ጅምሮ በመዘገብ ላይ ነው።መቀሌ ገብቶ ከወታደራዊ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረው ወጡ።ጥሩ ነው ግን የበለጠ ጥሩ የሚሆነው ራሳቸው አብይ ከመረጣቸው የትግራይ አሻንጉሊት አራት አመራሮች ጋር ብቻ 2ሺ ህዝብ በሚይዘው አዳራሽ ከመታየት ይልቅ ከህዝቡ ጋር ቢወያዩ ጥሩ ነበር።
ጠ/ሚ አብይ መለስ ቀለስ ።አገም ጠቀም ንግግር ይወዳሉ።እያሰቡ ከሚናገሩት ይልቅ ወጣትነታቸው እይገፋቸው የሚናገሩት ይበልጣል።ለምሥሌ የመጣሁት በ15ቀን ወያነን ያሸነፋችሁትን የመከላከያ አባላት ለማመስገን ነው አሉ።የወያኔን አከርካሪ ሰበርነው። በአጭር ግዜ አጠፋነው አሉ።ወያኔ 17 አመት የፈጀባትን እኛ በ15 ቀን ከጥቅም ውጭ አደረግነው አሉ። ጀግኖቹ ጀነራሎች እቅድ አውጭው ጅኔራል ብራሀኑ ጁላ እቅድ አስፈሚው ጀኔራል አበባው ጥይት ተኳሹ ጀኔራል አለምሽት….።እድሜ ለነሱ አሉ……..ቀጠል አደረጉና …….ግን ግን አትፎክሩ አሉ።ምክር መሆኑ ነው።” አትፎክሩ ወንድ ልጅ አይፎክርም አሉ” አይ አብቹ ……አብቹ ራስቸው ምን እያደርጉ እንደሆነ የገባቸው አይመስልም።
ፍከራ የዳምጠው አየለ ዘፍን ተከፍቶ ጎራዴና ጋሻ ተይዞ ወይ የሀጫሉ ሁብዴሳ ጦር ይዞ”ጄዲ ጋ” ሲል ብቻ መስሎ ከተሰማቸው ተሳስተዋል። ፉከራ ይኽው ነው።አንፎክርም በእርሳበርስ ጦርነት ስለሆነ ይባል እና ይፎከራል።
እኔ ይህን ድል አልናገርም ይባልና አርቲቶች ይዝፈኑበት ደርሲዋች ይፃፉበት አክተሮች ፊልም ይስሩበት ይላሉ ባደባባይ….አገም ጠቀም ….ሄድ መለስ
ይህ ማለት እንግዲህ የሳቸው አንዱ ድል ቢሆንም እሳቸው “ትሁት ” መባልን ስለሚፈልጉ ሌሎችቢሰሩት ግን ይወዳሉ ማለት ነው። ሄደት መለስ…….
በሰችዊሽን ሩም ሆነን የጁንታውን እያንዳንዱን እንቅሲቃሴ እያተከታተልን ነበር አሉ።የዛሬ አ10 ቀን። እኛ ደግሞ ጁንታ ተብዬዎች በማግስቱ በቃ ያሉበት ቦታ ስለሚታወቅ ሊያዙ ነው አልን።
አሁን ትላንትና ታዲያ “ሳዳም ሁሴን እንኳ ለመያዝ ለአሜሪካ መንግስት 30 ቀን ፈጅቶበታል አሉን”
እንደመሪ ለህዝብ የሚነገሩ እና የማይነገሩ አሉ።የማያስፈልጉ ነገሮችን ተናግሮ ያልሆኑትን ሆኖ መታየት የቦሊቪያው መሪ ኢቮ ሞራሌስ አይነት ስም ያሰጣል።ሞራሌስ ማለዳ ተነስተው ውሸት አስለመዱት ህዝባቸውን መጨረሻ የሚምናቸው ጠፋ።
ጠ/ሚ አብይ ብዙጊዜ በስሜት ነውጥ ውስጥ ሆነው ነው የሚወሩት።ህዝብን ሲያናግሩ የሚዘጋጁ አይመስልም።አማካሪም ያላቸው አይመስልም።
እንደመጣላቸው እስክስታ ወርደው ይገባሉ።
“ጁንታው አልተያዘም ……ያዙልኝ ብለው ተማፀኑ ትላንት”? እየተከታተልናቸው ነው አላልክም ወይ ያላቸው የለም? ማን ይኖራል ? እኛም የደፈርነው በወረቀት ነው።
ለማንኛውም”የሰችዌሽን ሩም ጭዋታ ሿሿ ነው እንደሚሉት ነው አዲስ አበቤዎች።ጁንታው መቼም ይሁን መቼ ይያዛል።ወይ ይገደላል። ወይ ራሱን ያጠፋል። ከዚህ የዘለል ምርጫ አይኖረውም። 360 ዲግሪ ተከቧል እና።
ስለዚ የሰችዊሽን ሩም ወሬ ባላስፈለገ።ድሮውን ባላስፈለገ።ድሮውን በአለም አቀፍ ደርጃ የተፈቀደ አይደለም።እንኳን ለሀርገ ውስጥ ጦርነት ለሁለት አገር ጦርናት እንኳ የተፈቀደ አይደለም።ለዚህ ነው መሪያችን አማካሪ የለውም የምንለው።
ሁሉንም አቃለሁ እና ከኔ በላይ ላሳር ስብእና ጥሩ አይደለም የምንለው።