>

ጴንጤነትና ኦሮሙማ (መስፍን አረጋ)     

ጴንጤነትና ኦሮሙማ

መስፍን አረጋ     


“The numerous tribes who inhabit the Ethiopian state are being forcibly kept from European colonialism by Abyssinian rulers whose aim is to act as champions of all black people so as to attack and destroy Western culture”

የጦቢያን አያሌ ብሔረሰቦች የነጭ ባርያ የመሆን ምርጫ የነፈጓቸው፣ ዓላማቸው በነጭ የባህል (እና የሐይማኖት) ወረራ መቃብር ላይ የመላው ጥቁር ሕዝብን ልዕልና መገንባት የሆነው የሐበሻ መሪወች ናቸው፡፡ Roman Prochazka (Abyssinia: The Powder Barrel, Vienna, 1935)

“The Europeans give us bibles only so that, when we close our eyes to pray, they can take our land.” 

“አውሮጳውያን መዱስ የሚሰጡን፣ ለመጸለይ ዓይናችንን ስንጨፍን መሬታችንን ለመንጠቅ ነው፡፡”  ጆሞ ኬንያታ (Jomo Kenyata) 


ታላቁ አፍሪቃዊ አርበኛ ጆሞ ኬንያታ ሊያስገነዝቡን እንደሞከሩት፣ ሚሲዮኖች የክርስትና ሐዋርያወች ሳይሆኑ፣ የቅኝ ገዥወች ፊታውራሪወች ነበሩ፡፡  የአውሮጳ ጅቦች አፍሪቃ የገቡት፣ ሚሲዮን ውሾቻቸው በቀደዱላቸው በር ነበር፡፡  ያገራችን ጴንጤወችስ?

ያገራችን ጴንጤወች በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚጫወቱት ሚና፣ ሚሲዮኖች ባፍሪቃዊነት ላይ ከተጫወቱ ሚና ጋር አንድ አይነት ነው፡፡  የሚሲዮን ሚና በሐይማኖት ሽፋን አፍሪቃዊነት ማጥፋት እንደሆነ ሁሉ፣  የጴንጤም ሚና በሐይማኖት ሽፋን ጦቢያዊነትን ማጥፋት ነው፡፡  ሚሲዮንነት ያፍሪቃዊነት ፀሮች ሐይማኖታዊ መሣርያ እንደነበረ ሁሉ፣ ጴንጤነትም የኢትዮጵያዊነት ፀሮች ሐይማኖታዊ መሣርያ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ እየሱስ (Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus) በሚል ስያሜ ጴንጤነትን በጦቢያ ላይ በ1950ወቹ የዘሩት ጉዲና ቱምሳን የመሳሰሉ ቀንደኛ ኦነጋውያን ነበሩ፡፡ ለጴንጤነት ምሥረታ ከፍተኛውን እገዛ ያደረጉት ደግሞ የሉተራን (Lutheran) እና ፕሬስቢቴርያን (Presbyterian) ሚሲዮኖች ነበሩ፡፡  እነዚህ ሚሲዮኖች ወደ ጦቢያ የተላኩት ደግሞ የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ጦቢያን በጎጥ የማፈራረስ ዓላማ ለመተግበር ነበር፡፡  

ነጮቹ ሚሲዮኖች ጦቢያን ለማፈራረስ የሚፈልጉት፣ የቅኝ ገዥወች ዋና እንቅፋት በመሆኗ ነው፡፡  ኦነጋውያን ጴንጤወች ደግሞ ጦቢያን ለማፈራረስ የሚፈልጉት በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አጼጌ (empire) ለመገንባት ነው፡፡  ስለዚህም ነጮች ሚሲዮኖችና ኦነጋውያን ጴንጤወች ግባቸው (goal) እየቅል ቢሆንም፣ ትልማቸው (strategy) ግን አምሳል ነው፡፡   ሁለቱም ግቦቻቸውን ሊመቱ የሚችሉት ጦቢያን በማፈራረስ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ሁለቱም የሮማን ፕሮቻዝካ ደቀመዝሙሮች ናቸው፡፡ 

ጦቢያን ማፈራረስ የሚቻለው ደግሞ ጦቢያ የተገመደችባቸውን ገመዶች በመጣጠስ ነው፡፡  ከነዚህ ገመዶች ደግሞ አንዱና ዋናው የጦቢያ ርቱምነት (ርቱዕ ዕምነት፣ orthodox) ተዋሕዶ ነው፡፡  የሐይማኖትን ገመድ መበጣጠስ የሚቻለው ደግሞ በሐይማኖት ነው፣ እሾህን በሾህ እንዲሉ፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ጴንጤነትን የመሠረቱት ለክርስትና አስተምህሮ ግድ ኑሯቸው ሳይሆን፣ ጦቢያን ለማፈራረስ የሚያስችላቸው ፍቱን መሣርያ ሆኖ ስላገኙ ብቻና ብቻ ነው፡፡  በሌላ አባባል ለኦነጋውያን ጴንጤወች፣ ጴንጤነት የግብ መምቻ እንጅ ግብ አይደለም፡፡ 

ለኦነጋዊ ጴንጤወች ጴንጤነት የግብ መምቻ ሳይሆን በራሱ ግብ ቢሆን ኖሮ፣ ክርስትያናዊቷን ተዋሕዶን ከማጥቃታቸው በፊት በዋቄፈታ ላይ በዘመቱ ነበር፡፡  ዋቄፈታን እያንቆለጳጰሱ ተዋሕዶን ባላንኳሰሱ ነበር፡፡  መስቀል መሳለምን እያወገዙ፣ ኦዳን በቅቤ ባላወዙ ነበር፡፡  ኢሬቻን እያደነቁ፣ በመስቀል በዓል ባልተሳለቁ ነበር፡፡  ካቶሊክን ሳይነቅፉ፣ ተዋሕዶን ባልዘለፉ ነበር፡፡  እስልምናን እየፈሩ፣ ተዋሕዶን ባልደፈሩ ነበር፡፡   

ኦነጋዊ ጴንጤወች፣ ጴንጤነትን ላጀንዳቸው ማስፈጸሚያነት የሚጠቀሙ የክርስትና ቁማርተኞች እንጅ፣ ክርስቲያኖች አይደሉም፡፡  ዓላማቸው ተሳክቶላቸው በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አፄጌ ቢመሠርቱ፣ በመጀመርያ የሚያደርጉት የቀሩትን ሁሉንም ሐይማኖቶች (ክርስትና፣ እስልምና፣ ባሃይፍና ወዘተ.) በሕግ ከልክለው፣ ዋቄፈታን ነጥለው ብቸኛ መንግሥታዊ ሐይማኖት ማድረግ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡

 እንቆቅልሹ ደግሞ አብዛኞቹ ጴንጤወች፣ የኦነጋዊ ጴንጤወችን እኩይ ዓላማ ባለመረዳት ጴንጤነትን በሐይማኖትነቱ ብቻ ተመልክተው የጰነጠጡ አገር ወዳድ ጴንጤወች መሆናቸው ነው፡፡  በሌላ አባባል አብዛኞቹ ጴንጤወች በኦነጋዊ ጴንጤወች የተደለሉ (convince) ወይም የተታለሉ (confuse) አገር ወዳድ ጴንጤወች ናቸው፡፡  እነዚህ አገር ወዳድ ጴንጤወች በሐይማኖት ሽፋን ዓይናቸው ስለተሸፈነ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች እየሱስ፣ በየሱስ የሚሉት ጦቢያዊነት እስኪደመሰስ ድረስ እንደሆነ አልተገለጠላቸውም፡፡  

እጅጉን የሚያሳዝነው ደግሞ በስብከትና በዝማሬ ክሂሎታቸው ጴንጤነትን እንደ ሰደድ እሳት በማስፋፋት፣ የሚወዷትን አገራቸውን የኢትዮጵያን ሞት የሚያፋጥኑት እነዚህ አገር ወዳድ ጴንጤወች መሆናቸው ነው፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን፣ ኢትዮጵያዊነት የተገመደበት ሌላኛው ገመድ ለሆነው ለአማርኛ ቋንቋ ካላቸው የመረረ ጥላቻ የተነሳ ቋንቋውን በቅጡ የማይቸሉ፣ ቢችሉም የማይችሉ ለመምሰል የሚጣጣሩ ከንቱወች ስለሆኑ፣ በስበከትም ሆነ በመዝሙር የማጰንጠጥ ችሎታቸው ከመ አልቦ ነው፡፡  

ስለዚህም ጴንጤነት የተመሠረተው በኦነጋዊ ጴንጤወች ቢሆንም፣ የቆመው ግን በኦነጋዊ ጴንጤወች በተደለሉ ወይም በተታለሉ አገር ወዳድ ጴንጤወች ነው ማለት ነው፡፡  በሌላ አባባል ጦቢያን የማፈራረሻ ስልት ለሆነው ለጴንጤነት መስፋፋት ወሳኙን ሚና የሚጫወቱት፣ ጦቢያ ፈራርሳ ከማየት ይልቅ ሞታቸውን የሚመኙ አገር ወዳድ ጴንጤወች ናቸው ማለት ነው፡፡  

ስለዚህም አገር ወዳድ ጴንጤወች የኦነጋዊ ጴንጤወችን እኩይ ዓላማ ተረድተው፣ የዓላማው አስፈጻሚ ላለመሆን ከወሰኑ፣ ኦነጋዊ ጴንጤነት ባጭር ጊዜ ውስጥ ያከትማል ማለት ነው፡፡  ጴንጤነትን በሐይማኖትነቱ ብቻ የሚመለከቱት አገር ወዳድ ጴንጤወች፣ ወደ ሐይማኖታቸው ሲያንጋጥጡ፣ ሐይማኖታቸው የቆመበትን አገራቸውን እንዳያጡ አበክረው ሊያስቡበት ይገባል፡፡   

ሐይማኖታዊ ነጻነትን (religious freedom) ጨምሮ ሁሉም ነጻነቶች፣ የሀገር የነጻነት ዛፍ የሚያፈራቸው ፍሬወች ናቸው፡፡  ለምሳሌ ያህል ቢሊ ግራሃምን (Billy Graham) የመሳሰሉ ምዕራባውያን ወንጌላውያን (evangelicals) ሰበካቸውን በጨረሱ ቁጥር be with our soldiers in harms way እያሉ አምላካቸውን ከወታደሮቻቸው ጎን እንዲቆም የሚማጸኑት፣ የሐይማኖት ነጻነት የሚቆመው ባገር ነጻነት ላይ መሆኑን  ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡   

ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን አገር የግዜር ነው እያሉ ለጦቢያዊነት ዘብ መቆምን (ወታደር መሆንን) ኀጢያት ያደርጉታል፡፡  ይህን የሚያደርጉት ደግሞ በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አፄጌ ለመገንባት ያቀዱትን እቅድ የሚያከሽፍ፣ ለጦቢያ ቀናዒ የሆነ ትውልድ እንዳይፈጠር ነው፡፡  አገር የግዜር ነው በሚሉበት አፋቸው ደግሞ ኦሮሚያ ኬኛ ይሉበታል፡፡  እልፍ አእላፍ የተዋሕዶ አርበኞች በደም ባጥንታቸው ባቆሟት አገር ላይ፣  የተዋሕዶ መዕምኖችን ባዕድ ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡   በማን ላይ ቁመሽ ማንም ታሚያለሽ እንዲሉ፡፡  

ጴንጤነት ማለት ሰሙ ክርስትና ወርቁ ኦሮሙማ የሆነ የሐይማኖት ቁማርተኞች ቅኔ ነው፡፡  አገር ወዳድ ጴንጤወች ግን፣ በኦነጋዊ ጴንጤወች በመደለል (convince) እና በመታለል (confuse) እንዲያዩ የተደረጉት የጴንጤነትን ኦሮሙማዊ ገጽታ ሳይሆን፣ የጴንጤነትን ክርስቲያናዊ ገጽታ ብቻ ነው፡፡  የጴንጤነት ቅኔ፣ ሰሙ እንጅ ወርቁ አልተገለጠላቸውም፡፡  ስለዚህም (ላገር ወዳድ ጴንጤወች) በጴንጤነትና በተዋሕዶ መካከል ያለው መሠረታዊ ችግር ያሰተምህሮ (doctrine) ልዩነት ይመስላቸዋል፡፡    

ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን ለዋቄፈታ እንጅ ለክርስትና ዴንታ ስለሌቸው፣ ፀባቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንጅ ከተዋሕዶ አስተምህሮ ጋር አይደለም፡፡  ተዋሕዶነት ከጦቢያዊነት ጋር ባይቆራኝ ኖሮ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች የካቶሊክን አስተምህሮ የሚያከብሩትን ያህል፣ ተመሳሳዩን የተዋሕዶን አስተምህሮ ባከበሩ ነበር፡፡  ችግሩ ግን ካቶሊክ የጣልያን፣ ተዋሕዶ የጦቢያ መሆኑ ነው፡፡  

ስለዚህም ኦነጋዊ ጴንጤወች ባልተገራ አንደበታቸው ተዋሕዶን የሚዘልፏት፣ ባስተምህሮዋ ምክኒያት ሳይሆን ተዋሕዶን በማዋረድ ጦቢያዊነትን ለማሽመድመድ በነደፉት ኦሮሙማዊ ትልም (strategy) መሠረት ነው፡፡  ስለዚህም አገር ወዳድ ጴንጤወች፣ ተዋሕዶን የዘለፉ መስለው ኢትዮጵያን የሚዘልፉትን ኦነጋዊ ጴንጤወች አቁሙ ሊሏቸው ይገባል፡፡  አቁሙ ከተባሉ ደግሞ ሳይወዱ በግዳቸው ያቆማሉ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች የሚቀናጡት ባገር ወዳድ ጴንጤወች ጫንቃ ላይ ነውና፡፡  

ሐይማኖት ማለት ምክኒያታዊነትን የማያስተናግድ ዶግማ ስለሆነ፣ ማናቸውም ሐይማኖት በሐይማኖትነቱ ትክክለኛ ሐይማኖት ነው፡፡  ስለዚህም፣ ሐይማኖቶች ሲባሉ በመዕምናን ብዛት እንጅ ባስተምህሮ አይበላለጡም፣ አይተናነሱም፡፡  የሚጥመውን አስተምህሮ የሚያውቀው ደግሞ መዕምኑ ነው፡፡  

ስለዚህም የተዋሕዶን አስተምህሮ አለመቀበል መብት ቢሆንም፣ አስተምህሮውን መዘለፍ ግን መብት አይደለም፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን ድፍን ኢትዮጵያን ኦሮምያ የማድረግ ዓላማቸውን ማሳካት የሚቸሉት ተዋሕዶን በማራከስ ብቻና ብቻ ስለሆነ፣ ኻይ እስካልተባሉ ድረስ አፋቸው ለከት አይኖረውም፣ ከፀረ ተዋሕዶ ድርጊታቸውም አይቆጠቡም፡፡ 

ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩን፣ ብኻዩን… ወደ ጎን ትተው፣ ተዋሕዶውን ብቻ እግረ በግር እየተከታተሉ “እየሱስን ተቀብለሃል?” እያሉ መነዝነዝን ምን ይሉታል?  ተዋሕዶወች ብቻ እንዲጰነጥጡ የተፈለገበት ምክኒያት ምንድን ነው?  የተዋሕዶ ዐብያተ ክርስቲያኖች በቄሮ መንጋ ሲጋዩ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች ደስታቸውን መደበቅ እስከሚያቅታቸው ድረስ ፊታቸው እንደ ፈንድሻ የሚፈካው ለምንድን ነው?  በመንግሥታዊ ቢሮስፍና (bureaucracy) ውስጥ የተሰገሰጉ ኦነጋዊ ጴንጤወች፣ የሌሎች ሐይማኖታዊ በዓሎችን አከባበር እያመቻቹ፣ የተዋሕዶ ባዕሎች ግን እንዳይከበሩ አያሌ ቢሮስፍናዊ (bureaucratic) መሰናክሎችን የሚቸክሉት ለምንድን ነው?  

አገር ወዳድ ጴንጤወች ሆይ፣ ዓይናችሁን ክፈቱ እንጅ፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች በየሱስ ስም የከነቧችሁን ክናብ (ዓይነ ርግብ፣ veil) ገልጣችሁ፣ ግማሹን ውነት (half truth) ሳይሆን ሙሉውን ውነት የምታዩት፣ የጴንጤነት ቅኔ ሰሙ ብቻ ሳይሆን ውርቁም የሚገለጥላችሁ መቸ ነው?  ጦቢያ ከሞተች በኋላ?  በዳግም ምጽኣት?

ሐይማኖት የሚቆም ነውና ባገር ላይ

በሐይማኖት ሽፋን ሲመጣ አገር ገዳይ

ባንድነት ግጠመው በምነት ሳትለያይ፡፡

ድኅረ ኪታብ (Post-script)

ጴንጤወች ጴንጤ መባልን ስለሚቃወሙ፣ ራሳቸውን የሚጠሩት ፕሮቴስታንት (protestant) ብለው ነው፡፡  ጴንጤወች ፕሮቴስታንትፓስተርቸርችባይብል የመሳሰሉትን ባዕድ ቃሎች መጠቀም መብታቸው ነው፡፡  ነገር ግን አንድን ያማረኛ ተናጋሪ ራሱ እስካልፈቀደ ድረስ ያማረኛ ባልሆነ ቃል ጥራኝ ብለው ማስገደድ አይችሉም፡፡  

ተዋሕዶወች ራሳቸውን ኦርቶዶክስ የሚሉት ምርጫቸው ስለሆነ ነው (ምንም እንኳን ኦርቶዶክስ ከሚለው ባዕዳዊ ቃል ይልቅ ርቱምነት የሚለው አገራዊ ቃል የሚሻል ቢሆንም)፡፡  ማናቸውም ሐይማኖት ያማረኛ ስም እስከሌለው ድረስ፣ ያማረኛ ተናጋሪወች ያማረኛ ስም ሊያወጡለት ሙሉ መብት አላቸው (ስሙ አንቋሻሽ ወይም አራካሽ እስካልሆነ ድረስ)፡፡  ለምሳሌ ያህል የነብዩ ሙሐመድ እምነት ተከታዮች፣ አማረኛ ተናጋሪወችን እንደ አረበኛው ሙስሊም እንጅ፣ እንደ አማረኛው እስላም አትበሉን ብለው ማስገደድ አይችሉም (እስላም የሚለው ቃል ያሉበትን ችግሮች ዘርዝረው እስካላብራሩ ድረስ)፡፡   

የፕሮቴስታንት ያማረኛ ትርጉም ዓማፂ ስለሆነ፣ የእምነቱን ተከታዮች ዓማፂያን ብሎ መጥራት ያማረኛ ተናገሪወች ሙሉ መብት ነው፡፡  ፕሮቴስታንቶች ባማረኛ ሲጠሩ ዓማፂያን ወይም ጴንጤ እንዳይባሉ ከፈለጉ ደግሞ ራሳቸውን በራሳቸው ባማረኛ ይሰይሙ፡፡  ይህን እንዲያደርጉ ግን ኦነጋዊ ጴንጤወች እንደማይፈቅዱላቸው እሙን ነው፣ ሐይማኖቱ ጦቢያዊነትን ተላብሶ ጦቢያዊነትን እንዳያራምድ ይፈራሉና፡፡ 

በመጨረሻም ለተዋሕዶ ማሳሰቢያ፡፡  የሽንፈት መንስዔው የራስ ድክመት እንጅ የጠላት ጥንካሬ አይደለም፡፡  ጴንጤነት ደግሞ መንፈሳዊ ስካር ስለሆነ፣ ጥንካሬው የብቅል ነው፡፡  ስለዚህም ምንም እንኳን የኦነጋዊ ጴንጤነት ዓላማ ተዋሕዶን መግደል ቢሆንም፣  ተዋሕዶ ልትሞት የምትችለው ግን በጴንጤነት ጥንካሬ ሳይሆን በራሷ ድክመት ነው፡፡  በመሆኑም ተዋሕዶ ሐይማኖት እሷ ራሷ ሙታ ጦቢያን ይዛ እንዳትሞት፣ ራሷን አብጠርጥራ መርምራ፣ በሽታወቿን በደንብ አውቃ፣ ፍቱን መድሐኒቶችን አጥብቃ መሻትና መራራ ቢሆኑም እንኳን ባፋጣኝ መውሰድ አለባት፡፡

 

መስፍን አረጋ      

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic