>

" የትህነግን እርሾ በመድፋት ነው ለውጥ የሚመጣው...!!!" (ክርስቲያን ታደለ )

” የትህነግን እርሾ በመድፋት ነው ለውጥ የሚመጣው…!!!”

ክርስቲያን ታደለ

“….ትህነግ ላይመለስ ቢቀበርም፣ የትህነግ ቫይረስ ተሻካሚዎች አሁንም ሞልተዋል። የእነሱን ውርስ የሚጠብቁና የሚያስጠብቁ ብዙ ናቸው” 
 
*…በዘር ፍጅት የቆመው ብልጽግና!
በክርስቲያን ታደለ  (የአብን ከፍተኛ አመራር
የፖለቲካ ክፍተት አለ። ክፍተቱም ሀገርን እንደ ሀገር በሚያይ እና ሀገርን እንደ ቅኝ ገዢ በሚቆጥር ቡድን መካከል የተፈጠረ ነው። እንደ ፖለቲከኛ እንኳን አንድ ቡድን ቀርቶ፣ ግለሰብም ሀገር የማፍረስ አቅም አለው ብለን እናስባለን።
መፍትሔው ግልፅ ነው። የትህነግን እርሾ በመድፋት ነው ለውጥ የሚመጣው። የትህነግ አስተሳሰብ ቤተ መንግስት ውስጥ ገዢ ሀሳብ ሆኖ እስከቀጠለ፣ ህገ መንግስቱም ባለበት ሆኖ እየገደለን ባለበት ሁኔታ የጋራ እውነት ይኖረናል ማለት ዘበት ነው።
ትህነግ ላይመለስ ቢቀበርም፣ የትህነግ ቫይረስ ተሻካሚዎች አሁንም ሞልተዋል። የእነሱን ውርስ የሚጠብቁና የሚያስጠብቁ ብዙ ናቸው።
አሁንም መፍትሔው በሌሎች ጉዳት የራስን ጥቅም ከማረጋገጥ መውጣት ነው። በአሸዋ ላይ ከቆመ የፖለቲካ ስሪት በመውጣት፣ እውነታውን መጋፈጥ ነው። እውነታው ደግሞ ሀገርን እንደ ሀገር ከመቁጠር ይጀምራል።
 
በዘር ፍጅት የቆመው ብልጽግና!
መተከልንም ሆነ ወለጋን የሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ነው። የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮችን የሚያስተዳድረውም ይኸው የብልጽግና ፓርቲ ነው። በኮማንድ ፖስት እና አጣሪ ግብረኃይል ስምም በቦታው ስምሪት የሰጠውም ብልጽግና ፓርቲ የራሱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ነው። አማራ/አገው ራሱን ከአጥቂዎች እንዳይከላከል የነፍስወከፍ መሣሪያ እንዳይታጠቅ፤ ከታጠቀም እንዲፈታ ያደረገው የብልጽግና ፓርቲ ነው። በተለይ በመተከል በአማራ/አገው ላይ እየተፈፀመ ባለው የዘር ፍጅት አመራሩ ጭምር እየተሳተፈ መሆኑን ብልጽግና ራሱ ያመነው ነው።
በሌላ አገላለጽ አማራውን/አገውን እየገደለና እያስገደለ ያለው ብልጽግና ፓርቲ ነው። አማራውን ወክላችሁ በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ እየተሳተፋችሁ  ያላችሁ ወንድሞችና እህቶች  ከአራጁ ጋር ትቀጥላላችሁ ወይስ አራጁን ታስወጣላችሁ?  በመደማመጥ፣ መከባበርና መተማመን ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃቀኛ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊስት ኃይሎች በገዥው ብልጽግናም ሆነ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ዘንድ ቢኖሩም በተለይ የአማራ ብልጽግናዎች ለአራጁ ቡድን በምታሳዩት ከልክ ያለፈ ትእግስት ነው ዝምታን የመረጡት።
እናንተ ያላከበራችሁትን አማራነት አራጁ ቡድን አያከብረውምና ደጋግማችሁ አስቡበት። የፍትኅ፣ እኩልነትና ዴሞክራሲ እከክ የሆነውን አራጅ ቡድን ከላያችሁ ላይ አራግፉት። አልያ ግን እናንተም ለወገኖቻችን መታረጃ ካራን በጓዳ አቀብላችሁ ከፊት ለፊት ከደሙ ንፁሕ ነኝ ለማለት በሙሾ እጃችሁን የምትታጠቡ ጲላጦሳውያን እንደሆናችሁ እንቆጥራለን።
ሕዝብን ይዘን የማናሸንፈው ትግል አይኖርም!
Filed in: Amharic