“መተከል ሁለተኛው ማይካድራ ነው!!!
አምሀራ ኢንፎርመር
* መተከል እና አሳዛኝ ውሎዋ!!
* ሰባት ቤተሰብ ከአንድ ቤት ታርደው ተጥለዋል
*”… ጉምዞቹ አፈሩን እያነሱ እየው ይህን አፈር አሽትተው የጉምዝ መሬት እኮ ነው!” ይሉናል
መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ በዛሬው ቀን የሳስማንደን ቀበሌ ህዝብ ሃብቱን ንብረቱን ቤቱን ያፈራውን አዘመራ ጥሎ መውጣቱ ታውቋል። ወጣቶች አሮጊቶችንና አቅመ ደካሞችን በመሸከምና በማገዝ ከሞት ቀጠናው እንዲወጡ አድርገዋል።
ከመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ሳስ ማደልና ፋርዘይት ቀበሌዎች አማራው ሙሉ ለሙሉ መፈናቀሉን መዘገባችን ይታወሳል።
ከቦታው በደረሰን መረጃ መሰረት የተፈናቀሉ አማራዎች እስከአሁን ድረስ በ13 ተሽከርካሪዎች መንታውሃ ደርሰዋል። ተሽከርካሪ ያላገኙት ደግሞ አሁንም ከፋርዘይት ወደ ድባጢ በእግራቸው ከድባጢ ደግሞ ወደ መንታውሃ በመኪና እየመጡ እንደሆነ አረጋግጠናል።