>

የጠቅላይሚኒስተር አብይ በትህነግ ምክር ቤት መንገዋለል (ታጠቅ መ ዙርጋ)

የጠቅላይሚኒስተር አብይ በትህነግ ምክር ቤት መንገዋለል

 

ታጠቅ መ ዙርጋ


 

ከፖለቲካ ሥልጣን  መገለጫ  ምልክቶች (elements of power symbols) አንዱ የህወሃቶች ዓይነት የተንደላቀቀ  ም/ቤት  ማስራት መቻል ነው ።    

 ከዘመናችን ሃያል መንግሥታት አንዱ ከሆነው  ሪፐብሊኮ ኦፍ ቻይና ም/ቤት ሞዴል ወይም ናሙና ተስርቶ  ለ30 ዓመታት ተጋሮ ባልሆነ በማን ኢትዮጵያዊ/ዊት ባልተረገጠ አስጎምጂ (tantalizing) መቀመጫዎች፤ ጠ/ሚ/አብይና የጦር መኮነኖቻቸው  ተቀምጠው በታዩበት ሁኔት ማየት በርካታ የህይወትና የተፈጥሮ ተቃርኖ  ክስተቶችና ኩነቶች እንድንማርና እንድናስተውል ይጋብዘናል። 

ምክንያቱም ትላንት በዚህ የቅንጦት መቀመጫዎች  ተቀምጠው ሲታዩ ዘላዓለማዊ ይመስሉ የነበሩ ሚኒስተሮች፣ ሹማምንቶች፣ባለልዩ ልዩ ማዕረጎች፣መሬት ተጠያፊዮች ወዘተ..ዛሬ፤

 ምንበላቸው?ምንዋጣቸው?  ትላንትና ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተዘረፈ ገንዘብ  ይህንን ቦታ ያሰሩ፣ የዚህን ቦታ ባለቤት፣ባለእርስት ወዘተርፈ ይመስሉ  የነበሩ  ማን አለብኞች፣የትአሉ? የትሄዱ?  ይህ እንዲሆን እንዴት ፈቀዱ? ይህ እንዲሆን ምክንያት የሆነው ማነው? 

ከላይ ከጠቀስኩት -የህይወትና የተፈጥሮ ተቃርኖ  ክስተቶችና ኩነቶች ጥቂቶች ለምሳሌነት ፥

ሀ) የማሸነፍ ገጸባህሪና ታይታ – ክብር ፣ ግርማ ሞገስ፣ስነልቦናዊ እርካታ፣ውጫዊ ግዝፈት ወዘተርፈ። ጠ/ሚ አብይ ከጦር  መኮነኖቻቸው  ጋር በዚያ ቦታ ሲታዩ  ፤ እየተፋለመ የሚያስቸግረውን ሌላ አውሬ አድኖ ከጣለ በኋላ ግራና ቀኙን እያየ የሚንጎዋለል  አንበሳ ይመስሉ ነበር ። 

ለ) የመሸነፍ ገጸባህሪና ታይታ – መዋረድ፣መንኮታኮት፣ዝቅ ማለት ፣እንዳልነበረ መሆን፣ከበትረ ሥልጣን በውርደት መወገድ ፣ ከባላንጣው ተፋልሞ እንደተሸነፈ አውሬ አቅመቢስ መሆን ወዘተርፈ 

-ትላንት አብሮን ሲኖር፣ ሲጫወት ፣ሲበላ ወዘተርፈ የነበረ -የቤተሰብ አባል፣ዘመድ፣ጓደኛ፣ጎረቤት ዛሬ ከአጠገባችን በሞት ተለይቶን አፈር ሲሆን

– የጠዋት ጤዛ  በረፋድ ፀሃይ ረግፎ እንዳልነበረ ሆኖ መገኘት

-የቀን ፀሃይ ለማታ ጨለማ ቦታው ሲለቅ

-ክረምት ቦታው  ለጥቢ ሲለቅ

-ጥቢ ቦታው ለበጋ ሲለቅ

-በጋ ቦታው ለክረምት ሲለቅ

-አንድ ትውልድ በሌላ ትውልድ ሲተካ

-ትላንት የነበረው ደስታ ዛሬ  በሃዘን ሲተካ

-በክረምት ሞልቶ ሰው አላሻግር ያለ ወንዝ በበጋ ፀሃይ ሲደርቅ

-ትላንት የነበረ ሥልጣን፣ ማዕረግ፣ክብር ዛሬ እንዳልነበረ ሁኖ ሲገኝ ወዘተ..

የዕብደት  ፖለቲካ  (political cynicism) ፦ይህ በሰው ልጅ ታሪክ ከተፈጸሙ  አስከፊ የዕብደት ፖሊቲካዎች አንዱ ነው።  የተመኙትን ቀርቶ ያልተመኙትን መከሰት፣የታሰበውን ቀርቶ ያልታሰበውን ማግኘት፣አሸንፋለሁ ተብሎ የታሰበውን በመሽነፍ መጠናቀቅ፣ ለማትረፍ የተወሰደው የተንኮል እርምጃ  በመክሰር መጠናቀቅ፣ ሳልቀደም ልቅደም በማለት በተጀመረ እርምጃ ተቀድሞ ጉድ መሆን፣እገለብጧልለሁ/እገለብጣታለሁ ተብሎ የታሰበውን ተገልብጦ መገኘት ወዘተርፈ  የዕብደት ፖለቲካ  ባህሪዎች  ናቸው ።  ዕብደታዊ ፖለቲካ ምን እንደሚመስል በደንብ ለማወቅ   (Lost to theWest: The Forgotten Byzantine Empire, by Lars Brown worth , 15 September 2009) መጽሃፍ አንብቡ

    What is political cynicism? It is an absence of trust. ..at the level of the institutions and the regime as a whole (Miler,1974).A cynic is one who believes that human conduct is motivated wholly by self interest. person who expects nothing but conduct the worst of human conduct (webster1s dictionary).Cynicism has been defined as oppositional to political efficacy (political power to produce an effect) (Niemi et al.1991).political cynicism is recognized as an important political sentiment, point of view, way of thinking (Wiley on Library).Political cynicism is the negative end of the political trust continuum or dimension(Deker,H. &Meijerink,F.2012) etc..

በቅድመ መንግሥቱ ነዋ የነበሩትን የሥልጣን ግብግቦችን ሳናካትት፤ ኢትዮጵያ በምክንያታዊነትና በቅርጽ የተለያዩ  -በርካታ  ሥልጣን ተኮር መተላለቅ  አስተናግዳለች ። የ 1953 ዓ.ም ታህሳስ ወር የመንግሥቱ ነዋ  የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጋር በተያያዘ ፣ እነጀነራል አማን አንዶምን ፣ የ60 ሚኒስተሮችና ባለ ልዩ ልዩ ማዕረጎችን ፣የጀነራል ተፈሪ ባንቲን ፣ የኮሎኔል አጥናፉ አባተን ፣መንግሥቱ/ሃ ከስልጣን ሊባረር ሁለት ዓመት ሲቀረው የተገደሉትን 60 ጀነራሎችና ባለ ልዩ ልዩ ማዕረጎችን፣ የዶክተር አምባቸውንና ጓደኞቻቸውን መገደል ሁሉ  የዕብደት ፖለቲካ ምሳሌዎች ናቸው ።

ሰዎች በገዢና በተገዢ  መደብ  ከተከፋፈሉበት ታሪካዊ ወቅት አንስቶ አሁን እስከደረስንበት ዘመን -ለስልጣን፡ – ሲፋለሙ፣ ሲገዳደሉ.ሲካካዱ፣ መፈንቅለ ሥልጣን  ሲደራረጉ ፣ሲጫፋጨፉ ወዘተ.. ኖሮዋል፣ እየኖሩም ነው ። የዚህ ማብቄው መቸ እንደሚሆን መገመት ያስቸግራል። ምናልባት በዚህ ዓለም የሚኖር ማኅበረስብ ሁሉ በዲሞክራሲያዊ መርህና ሥርዓት መተዳደር ሲጀምር ይሆናል።

Filed in: Amharic