የስልቀጣው ፖለቲካ ሌላኛው ጠርዝ – 66 የኮንሶ ተወላጆች በግፍ ተጨፈጨፉ…!!!
ሂሩት ሀይሉ
ኮንሶ የኦነጋውያን የጥቃት ኢላማ !! …
– በ10 ቀናት ውስጥ 66 የኮንሶ ብሔር አባላት በኦነግ ታጣቂዎች ተገድለዋል። በእነ ሽመልስ ኢላማ ከተደረጉ ቦታዎች ውስጥ አንዱ የኮንሶ አካባቢ ነው።
– ነጭ ሣር ፓርክ የአደጋ ቀጠና ውስጥ ከገባ ቆየ።
– ታጣቂዎችን ከእነ ትጥቃቸው አስገብተውና በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ፈቅደው አልፎም በተቀናጀ ሁኔታ በመስራት ንጹሐንን በየቦታው እያስገደሉ ነው።
በመላ ሀገሪቱ ያለውን ችግር ለመፍታት ከባድ ያደረገው ከላይ እስከ ታች በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ ባለሥልጣናት የሚመራና የሚቀናጅ መሆኑ ነው።
ኮንሶዎች የሀገራቸውን ሠንደቅ አላማ የሚወዱ ኢትዮዽያዊነታችን የሚያስቀድሙ ዜጎች ናቸው። አንዱም የጥቃት ኢላማ ያስደረጋቸው ይሄ ነገር ነው።
ኦነግ ሸኔ በሚል የቅጥል ስም እየተሰጠው የሚቆላመጠውና የኦዴፓ የተስፋፊነትና የወረራ አጀንዳ አስፈፃሚ የሆነው ቡድን በኮንሶ ተወላጆች ላይ የዘር ጭፍጨፋ ፈፅሟል! ለነሱ ማን ይጩህላቸው? መቼ ነው ደም መፍሰስ የሚቆመው? መቼ ነው ሰው እንደ ደሮ መታረድ የሚቆመው? የመንግስት ሚዲያዎች የዜጎችን ሞት በእኩል የሚያየውስ መቼ ነው? አንድ ሀጫሉ ተገደለ ተብሎ ያ ሁሉ ያገር ሚዲያ 24/7 ሰአት ሲያለቅስና ሲያስለቅስ የነበረው ምነው በመቶዎች የሚቆጠሩ ነፍሶች በጨካኞች ሲቀጠፉ አፉ ተለጎመሳ? የሽናሻዎች የባህል ዘፋኝ የነበረው ድምፃዊ በኦነግና በግብረ አበሮቹ ሲገደል ለምን ሚዲያ ስለሱ አልዘገበም? እሱስ ድምፃዊ አይደል እንዴ? ድንቄም የብሄር ብሄርሰቦች ጠበቃ! ድንቄም ፌደራሊስት! ድንቄም የፌደራሊዝሙ ጠበቃ!