>

ባሁኑ ሰዓት "ዶክተር ዐቢይ" የሚባል አምባ ገነን መንግሥት እንጂ "ብልጽግና" የሚባል ድርጅት የለም...!!! (አሳዬ ደርቤ)

ባሁኑ ሰዓት “ዶክተር ዐቢይ” የሚባል አምባ ገነን መንግሥት እንጂ “ብልጽግና” የሚባል ድርጅት የለም…!!!
አሳዬ ደርቤ

 ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሰርግ ላይ ይለቀስ” የሚል ትዕዛዝ ካስተላለፈ እንባቸውን የሚያንዠቀዥቁ እልፍ አእላፍ ደቀ መዛሙርቱ የተባሉትን ይፈጽማሉ።
“አስከሬን ላይ ጨፍሩ” ብሎ ካዘዘም ኀዘናቸውን ደብቀው ዳንኪራቸውን የሚያወርዱ ነፍ አረጥራጮች አሉት።
አቶ ሙስጠፌ ግን ከብልጽግና መንጋ መሀከል የተገኘ የእውነት ጠበቃ ነው።
ስለሆነም
ገዳይና አስገዳዮቹ “አልሰማንም” ብለው ሲቀልዱ፣ ሌሎቹ የአማራን የቀን ተቀን መታረድ እንደ አዘቦት ጉዳይ አድርገው ሲያዩት በይፋ ሀዘናኑን የገለፀው በእነ ሙስጦፌ የሚመራው  የሶማሊ ክልል ብቻ ነው። ሌላው ከእነ ሙስጦፌ አይቶ ስላዘነ ሳይሆን በምን ይሉኛል ሊከተል ይችላል። ዋናው ግን ማዘን ነው፣ ከወገን ጎን መቆም ነው!
ሌላው በሞት በሚቀልድበት ወቅት፣ የሶማሊ ክልላዊ መንግስትና ሕዝብ ከወገናቸው ጎን ስለቆሙ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል።
የፌደራል መንግሥቱ “ክልሎች የኀዘን መግለጫ ማውጣት አይችሉም” ብሎ ባልተፃፈ ደብዳቤ ቢከለክልም በአቶ ሙስጠፌ የሚመራው የሶማሌ ክልል ግን ይሄን ትዕዛዝ አሽቀንጥሮ በመተከሉ እልቂት ዙሪያ የተሰማውን ኀዘን የገለጸ ብቸኛ ክልል ሆኗል።
እናመሰግናለን ክቡር ፕሬዘዳንት
Filed in: Amharic