>
5:26 pm - Tuesday September 17, 5495

ከንቱዎች አይደለንም፣ እናደርገዋለን‼ (ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ)

ከንቱዎች አይደለንም፣ እናደርገዋለን‼

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

 

* ..  «ብልጽግና» መራሹ የአማራ ጭፍጨፋ ዘመናት ውስጥ በአማራነታቸው የተጠቁ፣ በቀስት የተወጉ፣ የውስጥ አካላቸው እንደ ከብት ስጋ የተበላ፣ አንገታቸውን የታረዱ፣ በጅምላ በጥይት የተረፈረፉ፣ ከነነፍሳቸው ወደ እንቁፍቱ ገደል የተከተቱ፣ ቤታቸው በውጭ ተዘግቶ በሳት የነደዱ፣ የታሰሩ፣ ሰቆቃ የተፈፀመባቸው አማሮች ታሪክ፣ የምስል፣ የድምጽና የቁስ ማስረጃቸው በትልቅ ሚውዚየም ተሰነዶ፣ በአማራ ላይ የተፈፀመው እልቂት አለም እንዲማርበት ተደራጅቶ የሚቀርብበትና፣ በአማራ ላይ የደረሰው በምንም ታምር አይደገምም የምንልበት ጊዜ ይመጣል!
 
1) በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ፣ ያስፈፀሙ፣ ያቀዱ፣ ያቀነባበሩ፣ ማስቆም ሲገባችው ያላስቆሙ፣ በንዝህላልነትና በቸልተኝነት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ ሁሉ በፍርድ አደባባይ ቆመው እንዲጠየቁ እናደርጋለን።
በአማራ እልቂት ወንጀል ተሳትፈው በህይዎት የሌሉትን ደግሞ ፎቶአቸውን «በአማራ የጅምላ ፍጅት ሚውዚየም» ውስጥ ግድግዳ ላይ ሰቅለን፣ የፈፀሙትንና ያስፈፀሙትን ወንጀል ከፎቶው ማብራሪያ ጋር አያይዘን እኩይነታቸውን ለልጅ ልጆቻችን እናስተምራለን። አማራ በደመኛ ጠላቶቹ የታወጀበትን ጅምላ እልቂትና ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዘመቻ እንዴት ቀልብሶ ህልውናውን እንዳስከበረ፣ ያካሄደውን የህልውና ትግል፣ ያስመዘገባቸውን ድሎች፣ በመንገዱ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች ሁሉ በሚገባ ተደራጅቶ ለልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችን እንነግራለን።
2) በአማራነታቸው ከአማራ ጠሉ ፋሽስት ሞሶሎኒና ወኪሉ ግራዚያኒ ጀምሮ እስከ «ብልጽግና» መራሹ የአማራ ጭፍጨፋ ዘመናት ውስጥ በአማራነታቸው የተጠቁ፣ በቀስት የተወጉ፣ የውስጥ አካላቸው እንደ ከብት ስጋ የተበላ፣ አንገታቸውን የታረዱ፣ በጅምላ በጥይት የተረፈረፉ፣ ከነነፍሳቸው ወደ እንቁፍቱ ገደል የተከተቱ፣ ቤታቸው በውጭ ተዘግቶ በሳት የነደዱ፣ የታሰሩ፣ ሰቆቃ የተፈፀመባቸው አማሮች ታሪክ፣ የምስል፣ የድምጽና የቁስ ማስረጃቸው በትልቅ ሚውዚየም ተሰነዶ፣ በአማራ ላይ የተፈፀመው እልቂት አለም እንዲማርበት ተደራጅቶ የሚቀርብበትና፣ በአማራ ላይ የደረሰው በምንም ታምር አይደገምም የምንልበት ጊዜ ይመጣል።
3) ይህን ለማድረግ ግን አማራ ሆ ብሎ ተነስቶ በሃያል ክንዱ ገዳዮችንና አስገዳዮቹን ደቁሶ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ህልውናውን ያስከብራል። አማራ ትልቁ ድክመቱ መንግስት ለተባለው አካል ያለው እምነቱ ነው። መንግስት ግን ሞቱን እንኳ ሊያስቆምለት ይቅርና በቅጡ እንኳ የክብር ቀብር አልሰጠውም። ስለዚህ አማራው በታላቅ ሀይል ተነስቶ ገዳዮቹን አፈር ከድሜ ይቀላቅላቸዋል። በዚህም የህዝባችን ህልውና ይከበራል!
«በአማራ የጅምላ ፍጅት ሚውዚየም» ውስጥ የእያንዳንዱ የአማራ ሰለባ ስም፣ አጭር ታሪክ፣ የምስልና ድምጽ ማስረጃና የተጨፈጨፈበት ሁኔታ አንዲደራጅ ይደረጋል። በነገራችን ላይ በአማራ ላይ የተፈፀሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን መረጃዎች፣ የምስል፣ የድምጽና የሰነድ ማስረጃዎችን የማሰባሰብና በዌብ ሳይት የመሰደር ስራ ውጭ አገር በሚኖሩ ብሩት የአማራ ልጆች እየተከናወነ ነው። ስራው ሲጠናቀቅ ወደፊት ለህዝባችን ይፋ ይደረጋል።
ተጎጂዎችን መቼም አንረሳቸውም፣ የተደረገብንንም መቼም አንረሳውም !
Filed in: Amharic