>

ይሉሽን በሰማሽ-----" (አሰፋ ታረቀኝ)

ይሉሽን በሰማሽ—–“

አሰፋ ታረቀኝ


በርና መስኮትህን ዘግተህ ድመትህን መግረፍ ብትጀምር፣የተፈጥሮ መቷን ለማስከበር ስትል ጥፍሮቿን አውጥታ ወደ ዐይኖችህ ትወረወራለች፡፡ በቅውድሞወ ብአደንና በአረመኔዋ ህዋህት መካከል የሆነው እንድህ ነበር፡፡ ህዋህት በአማርኛ ተናጋሪ የትግራይ ተወላጆች አማካይነት ጠፍንጎ የያዘው ብአደን ከጫናው ብዛት የተነሳ ወደ ህዋህት ጉረሮ ሊወረወሩ የሚችሉ ጥፍሮቹን ማሳየት መጀምሩ፣ በረከት ስምዖንንና ጓደኞቹን ሰላም አልሰጣቸውም፡፡ አዲስ ማደናገሪያ የአማራ ድርጅት ለመፍጠር ፍለጋ ሲኳትኑ በገባየው ላይ ያገኟቸውን ሰባስበውና ለመደራጃ የሚሆን ጠቀም ያለ ራብጣ በማሸክምአብንየሚባል ተለጣፊ ጠፈጠፉ፡፡አብንየአማርኛ ተናጋሪውን ሕብረተሰብ የስነልቦናና ኢትዮጵያ ጋር ያለውን የታሪክ ቁርኝት በማይመጥን መልኩ አክራሪ ጎሰኛ ሆኖ ፊጥፊጥ ማለት እንደጀመረ፣ ብአደን የኦሮሞ ወንድሞቹን በማስተባበርና ሀይሉን በማጠናከር፣ የህዋህትን የመተንፈሻ ቧንቧዘጋው፡፡ የዶ/ አብይ ለጠቅላይ ሚንስትርነት መመረጥ የህዋህት መልካም ፈቃድ ሳይሆን አማራጭ የማጣት ውጤት ነበር፡፡አብን አደራጆቹ ወደመቀሌ ሲሰበሰቡ፣ ሌላ የሚያቀርበው አማራጭ ስላልነበረውና በወቅቱ ገባያ ላይ ሸማቱ ሳይጠይቅ የሚገዛውን ሸቀጥ ይዞ ብቅ አለ፡ አማራ ብሄረተኝነት፡፡ 

“አብን”ለብዙ ጊዜ የተጀመረውን ትግል የሚያግዝና የሚያበረታታ ርምጃ ሳይሆን የሚያጥላላ አቋም ሲያራምድ ቢቆይም፣ ከቅርብ ጊዜ ወድህ መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃወች የደገፈበትም አጋጣሚ ታይቷል፡፡ በአመራሩ ላይ የቦታ ሽግሽግ ከተደረገ ወድህ ለዘብ ያለ አቋም እያሳየ ቢመጣም፣ ከአክራሪ አመለካከቱ የተላቀቀ አይመስልም፡፡ ሰሞኑን የቀድሞው የ “አብን” ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከሥልጣን ይውረዱ የሚል ሀሳብ ወርውረዋል፡፡ ክቡር ዶ/ር ደሳለኝ፣  በርግጥ በዚህ ሰአት የዶ/ር አብይ ሥልጣን መልቀቅ መፍትሄ ነውን ? ነገሩ የጤና ነው? አለቆቸወም ይሉት የነበረውኮ ዶ/ር አብይ ይውረዱ ነበር፡፡ ለምን አሁን አነሱት? ወደ ትግራይ ሸለቆወች ከመበተናቸው በፊት አብረው አይጮሁም ነበር? ነገሩኮ ከተበላሸ ቆየ፡ በህዋህት ትንተና መሠረት ‘አማራ’ የተባለው ህዝብ በእርስወ አይነት የፖልቲካ ሰው ሲወከል፣ ‘ኦሮሚያ’ የተባለው ደግሞ በነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ አይነት ሲመራ የኢትዮጵያ ችግር እድሜው አጭር እንደማይሆን አመልካች ነው፡፡

 በዚህ አስጨናቂና ሁሉም ጉሮሮችንን ለማነቅ በጣደፍበት ሰአት ጠቅላይ ሚንስትሩ ሥልጣን ይልቀቁ ማለት፤ እነ ሕዝቃኤል ጋቢሳ ካዘጋጁት የ ‘ኢትዮጵያ ትውደም’ ሰልፍ በምን ይለያል? ዶ/ር ደሳለኝ፣ ዶ/ር አብይ ወረዱ እንበል፣ ማነው ቦታውን የሚሸፍነው??? 

እግዚአብሔር ዶር/ር አብይን ከህዋህትና ከኦነግ የተቀናጀ ሴራ እየጠበቀ እስካሁን ያቆያቸው እንድሁ ይመስለወታል? ይመኑኝ እንድሁ አይደለም፡፡ የሰሞኑን የጠቅላይ ሚንስትሩን የተውካዮች ምክርቤት ንግግር አዳምጠውታል? ከዚያ ሁኔታ ውስጥ  የወጡት በጌታቸው አሰፋ መልካምነት? በዶ/ር አብይ ልዩ ጥበብ? ሁለቱም አልነበሩም፡፡ ዳዊትን ከሳኦል ማሳደድና ከሚወረውርምበት ጦር ያተርፈው የነበረው አምላክ አሁንም በሥራ ላይ ስለሆነና ስለሚጠብቃቸው ነው፡፡

ህዋህትና ኦነግ ለጊዜው የሚመጥን የፖለቲካ ቀመር ባለመቀየሳቸው፣ ወደ ታሪክ ትቢያነት/Antiquity/ እየተቀየሩ ነው፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ፣ አለመሸም ለኢትዮጵያ የሚመጥን ፕሮግራም መንደፍ ትችላላችሁ፡፡ ሀገሪቱ ከበቂ በላይ ጎሰኞች ስላሏት፣ በአማራ ስም የተደራጀ ጎሰኛ አያስፈልጋትም፣ ለአማራውም አያምርበትም፡፡ በአጭር አባባል ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ሀገር እንጅ፣ የማይተዋወቁ  ጎሳወች ተሰብስበውና ሲፈልጉ ሊበታተኑ ተስማምተው የፈጠሯት ዕድር አይደለችም፡፡ አስተያየቴን በቅንነት ካዩልኝ አንድ ነገር ልጨምር፣ መስቀል ጦርነት ዘመን ሰዎች ሁለት አይነት ምልክት ያለው ጃኬት ነበራቸው አሉ፡፡ እስላሞቹ እያጠቁ ሲመጡ የጨረቃውን ምልክት አዙረው ይለብሳሉ፡፡ ክርስቲይኖች ሲበረቱ የመስቀሉ ምስል ያለበትን አዙረው በመልበስ ዘመኑን አለፉት ይባላል፡፡ 

ከኦሮሙኛ ተናጋሪው የህብረተስብ ክፍል የወጣውና ተምሬያለሁ ባዩ፣ ብዙ ጃኬቶች አሉት፡፡ ኦነግ፣ ኦሆዲድ፣ ኦፌኮ፣ ብልጽግና፟ ኦነግ ሸኔ ሌላም ሌላም… ሲፈልግ አንዱ ሰው ሁሉም ጋር ሊገኝ ወይ ሁለቱ ላይ ሊቆም ይችላል፡፡ የተለያዩ ቢመስሉም አመቺ ሰአት ሲገኝ ሁሉም አንድ አይነት አቋም ለመያዝ አይቸገሩም፡፡ ሁሉም በኦሮሞ ስም የተደራጁ የፖልቲካ ድርጅቶች፣ በግልጽ ያልነገሩን ሁለት ስትራቴጂ ግቦች አሏቸው፡፡ የመጀመሪያው፣ ኦሮሞ በቁጥሩና በስፋቱ ልክ የሚመጥን የበላይነት እንዲኖረው ማስቻል፣ ያ የማይሠራ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ኦሮሚያ የምትባል አድስ ሀገር መመሥረት ናቸው፡፡ ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ፣ የተዛባውን አቅንታ፣ የሻከረውን አለስልሳ፣ በዕኩልነት መቀጠል ትችላለች ብለው የቀጠሉት ዶ/ር አብይና ጥቂት ደጋፊወቻቸው ናቸው፡፡ የሰሞኑ የአቶ ታየ ደንደአ ወለምዘልም የሚጠቁመን፣ የ “ኦሮሚያ” ክልል ብልጽግና ከኦነግ ወደ እሆድድ ከእሆድድ ወደ ብልጽግና ጃኬቶች እንደተቀያየሩ ነው፡ ከድርጅት ወደ ድርጅት ፈጥኖ በመቀየር ቅልጥፍና ደግሞ ኦነጎች ትክነውበታል፡፡ ከኦነግ ወደ መኢሶን፣ ከመኢሶን ወደ ኢጭአትና ማሌርድ፣ በመጨረሻም፣ አብዛኞቹ ኦሮሞኛ ተናጋሪ የመኢሶን ካድሬወች ተመልሰው ኦነግ ሆኑና ህዋህትን አጅበው አዲስ አበባ ገቡ፡፡ አሁንም ኦነጎች ጃኬታቸውን ገልብጠው ብልጽግና ውስጥ በመመሸግና የለውጡን ግሥጋሴ በማደናቀፍ ሥራ ላይ እየተረባረቡ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን ቀጣይነት የሚመኝ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሊያደርግ የሚገባው የመጨረሻው ውለታ ቢኖር፣ አስፈላጊ በሆነው ነገር ሁሉ ከዶ/ር አብይ ጋር መቆም ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው  አበው “ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” ዕንዳሉት ነው፡፡

Filed in: Amharic