>
5:13 pm - Monday April 20, 1170

ወንጀልን ለመሸፈን የሚደረግ ሌላ ወንጀል መስራት ይቁም ...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ወንጀልን ለመሸፈን የሚደረግ ሌላ ወንጀል መስራት ይቁም …!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

“መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር”፤ የኢትዮጽያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአርቲስት ሀጫሉን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተፈጸመውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በተመለከተ ያወጣው ሪፖርት ርዕስ ሲሆን ክስተቱም በሰው ዘር ላይ ያነጣጠረ ወንጀል (Crime Against Humanity) መሆኑን አረጋግጧል።
እንግዲህ ለዚህ ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አንስቶ በየደረጃው ያሉ ባለሥልጣናትን መመርመር እና ተጠያቂ ማድረግ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጏላፊነት እና ግዴታ ነው። ይህ አካል ጏላፊነቱን በአግባቡና በአጭር ጊዜ ውስጥ ይወጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
የቀበሌና የዞን ሹማምንትን ብቻ እያሰሩ በመንግስት አካላት በኩል ያለውን ተጠያቂነት ማድበስበስ ግን አሁንም ዜጎች መንግሥት ያለ እንዳይመስላቸው ያደርጋል። አጥፊን ለፍርድ ማቅረብ እና ተጠያቂ ማድረግ ሲገባ የክብር ካባ ማልበስ ግን ወንጀልን ለመሸፈን የሚደረግ ሌላ የወንጀል አድራጎት ነው።
Filed in: Amharic