>

ውድ የኢትዮ ሪፈረንስ አንባቢዎቻችን:- እንኳን ለብርሃኑ ልደቱ አደረሳችሁ!!!

ውድ የኢትዮ ሪፈረንስ አንባቢዎቻችን:-

እንኳን ለብርሃኑ ልደቱ አደረሳችሁ!!!

መልካም የልደት በዓል እንዲሆንላችሁም እንመኛለን።

 

ጸሎት 

*~★★~*

ህሊናችንን ሰብስብ አድርገን ጸሎታችንን ከፍ ባለ ድምጽ እንዲህ በማለት እንጀምር !!

•••

ፍጹም በሆነ ሙሉ እምነት፥

ፍጹም በተመሰጠ ልቦና ፥

በፍጹም መጸጸት ፥ በንፁህ ልቦና

እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ (አሐተ ስግደተ)

እንዘ አሐዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ አሐዱ

ይሤለሱ በአካላት ወይትወሐዱ በመለኮት

እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ

እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር

መስቀል ኃይልነ፥

መስቀል ጽንዕነ፥

መስቀል ቤዛነ፥

መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ፥

አይሁድ ክህዱ ንኅነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ።

•••

አምላኬ ሆይ

ስላደረግህልኝ ነገር

ስለምታደርግልኝ ነገር

ስላላደረክልኝ እና ስለማታደርግልኝም ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ።

ምንም ብበድልህ በፍጹም ቸርነትህና ፍቅርህ ጠብቀህ፥ በሕይወቴ ላይ ይህችን ሰዓት ጨምረህ፥ በተቀደስው ስፍራህ ስላቆምከኝ አመሰግንሃለሁ።

መላእክትን በጽርሃ አርያም፥

ሰማዕታትን በደም፥

ሐዋርያትን በአጽናፈ ዓለም፥

ጻድቃንን በገዳም ያጸናህ አምላክ፥ እኔንም በሃይማኖት፣ በጾም፣ በጸሎትና በምግባር እንድታጸናኝ እለምንሃለሁ።

አምላኬ ሆይ ምንም ዓይነት ፈተና እና መከራ ቢመጣብኝ እስከ መጨረሻዋ የህይወቴ ህቅታ ድረስ አንተን በማመን እንድታጸናኝ፣ በሕይወቴ ሁሉ አንተን በመፍራት እንድኖር፥ ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና ዕድሜ ለንስሐ ለቅዱስ ቁርባንም እንድታበቃኝ እለምንሃለሁ፡፡

•••

እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ፥ የእናት ልመና ፊት አያስመልስ፥ አንገትም አያስቀልስምና ከልጅሽ ከወዳጅሽ ተማልደሽ አማልጅኝ።

ለአባ ህርያቆስ

ለአባ ኤፍሬም

ለቅዱስ ያሬድ

ለቅዱስ ደቅስዮስ

ለበላኤሰብ የተለመንሽ እመአምላክ ለእኔም ለደካማው ለጎስቋላው ባርያሽ ተለመኝኝ።

እናቴ ሆይ ምስጋናሽ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው፤ እንደ ምግብ ተመግቤው፤ እንደ ውኃ ጠጥቼው እኖር ዘንድ እርጅኝ።

የኔ ኃጢአት ያንቺን ንጽህና አያረክሰውምና በብርሃን እጆችሽ ዳሰሽ ለነፍሴ የድኅነት ምክንያት ሁኚያት።

•••

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት መርተህ ያወጣህ እኔንም ከዚህ ዓለም ባርነት ነፃ እንድታወጣኝ እለምንህሃለሁ።

የባህራን ወዳጅ፣ የአፎምያ ረዳት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እኔ ደካማው አገልጋይህን እርዳኝ። የሚፈታተነኝን ሰይጣን ዲያቢሎስንም በበትረ መስቀልህ ቀጥቅጠህ ከእግሬ ስር እንድትጥልልኝ፣ በሄድኩበትም ሁሉ እንድትጠብቀኝ እማፀንሃለሁ፡፡

•••

አምላከ ነቢያት፥

አምላከ ሐዋርያት፥

አምላከ ደናግል፥

አምላከ መነኮሳት

ለቅዱሳንህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ ፥ ለያዕቆብ የገባኸውን ቃልኪዳን አስበህ እንደ ክፋቴ፣ እንደ ጥፋቴ፣ እንደ በደሌ ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ትምረኝ ዘንድ ቤተሰቦቼን፣ ሃገራችንን ህዝባችንን፣ ቤተክርስቲያናችንንና ሃይማኖታችንን ትጠብቅልን ዘንድ

ዝማሬ ዳዊትን፣

ተልዕኮ አርድዕትን ፤

ቅዳሴ መላዕክትን ፤

መስዋዕተ አቤልን ፤

ዕጣነ ዘካርያስን የተቀበልክ አምላክ የኔንም ጸሎት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ

• አባታችን ሆይ……

 

እነሆ እናንተ ቀጥሉ……….

(በመምህር ዘመድኩን በቀለ)

 

 

Filed in: Amharic