>

ይህን ቀን እነሱም ሊያዩት ይወዱ ነበር፡፡ (ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ)

ይህን ቀን እነሱም ሊያዩት ይወዱ ነበር፡፡ 

/ በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ


የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እያከበርን እንገኛለን፡፡ ይህንን በዓል በደመቀ ጎጃቸው የዛሬ ዓመት ያከበሩ ወገኖቻችን ዛሬ ግን ይህንን በዓል ለማክበር አልታደሉም፡፡ መንግስት ነኝ ብሎ የተሰየመው አካል ህግን ማስከበር ተስኖት እና የሴራ ፖለቲካ ሰለባ ሁነው ዜጎቻችን የክፋት ኃይል በሚገለጥባቸው ኃይሎች በማንነታቸው ምክንያት የጥቃት ሰለባ ሁነው ይህንን ቀን ማየት አልቻሉም፡፡ አብዛኛዎች ደግሞ ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያው ተመፅዋች ሁነዋል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ በፍትህ እጦት ለእስር ተዳርገዋል፡፡ 

በማንነታችሁ ምክንያት ህይወታችሁን ላጣችሁ ወገኖቸ በአፀደ ነፍስ እግዚአብሄር የእረፍት ቦታ እንዲሰጣችሁ፤ ከሞቀ ጎጃችሁ ተፈናቅላችሁ የሰው እጅ ለምትጠባበቁ እና ያለወንጀላችሁ በእስር ላይ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ እግዚአብሄር ፍትህን እንዲሰጠን የዘወትር ፀሎቴ ነው፡፡ የስልጣን ትልቅነታቸውን ተጠቅመው ይህንን ግፍ የጠነሰሱ እና የፈፀሙ ግለሰቦች ለዘመናችን የፍትህ ብልሽት ተጠያቂ መሆናቸው አይቀርም፡፡

Filed in: Amharic