>

የባልደራስ አመራሮች ባስቸኳይ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ይፈቱ ሲል ፓርቲው ዛሬ ጠየቀ!

የባልደራስ አመራሮች ባስቸኳይ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ይፈቱ ሲል ፓርቲው ዛሬ ጠየቀ!

መረጃ ባልደራስ
በወግደረስ ጤናው

ከዛሬ ጀምሮ (ጥር 1 2013 ዓ.ም) እስክንድርን ጨምሮ ባጠቃላይ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ለአንድ ወር የሚቆይ የአለም አቀፍ ንቅናቄ ዘመቻ ዛሬ በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሉት !
ባልደራስ በዋና ፅ/ቤቱ ለሚዲያዎች ዛሬ በሠጠው መግለጫ የባልደራስ አመራሮች ባስቸኳይ እንዲፈቱ ከመጠየቅ ባሻገር ኦህዴድ ብልፅግና …….
~ በዋናነት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የሚያደርገውን የተረኝነትና የመሰልቀጥ ጉዞ ባስቸኳይ እንዲያቆም
~ ሱዳን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ጥሳ መግባቷን መንግስት በንዝህላልነት መመልከቱ እጅግ ተገቢ እንዳልሆነ እና ባስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቋል
~ በመተከል ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁ ዜጎች ባስቸኳይ ጊዚያዊ የምግበና አልባሳት እርዳታ እንዲደርስላቸው እና በዘላቂነት በቀያቸው እንዲቋቋሙ እና አስቸኳይ መፍትሄ እንዲያገኙ
ባጠቃላይ አለም አቀፍ ንቅናቄውን ህዝቡ ዛሬ መጀመሩን ተረድቶ ከባልደራስ አመራሮች ጎን በመቆም ንቅናቄውን በማህበራዊ ሚዲያ እንዲቀላቀል በዛሬው መግለጫ ባልደራስ ጥሪ አቅርቧል።
ፍትህ  በግፍ ታስረው ለሚሰቃዮ የህሊና እስረኞቸ!
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ!
ጥር 2013
Filed in: Amharic