በመተከል- የተፈናቃዮች ቤቶችን ኦነግ ወረራ እያካሄደባቸው ነው…!!!
(አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013 ዓ.ም)
* መተከል ዛሬ አልተረጋጋም፡፡ የተፈናቃይ ቤቶችም በኦነግ እየተያዙ፣ ያልተያዙትም በኦነግ ቀለም እና አርማ እያሸበረቁ ነው!!!
መተከል ከ2011 ዓም ጀምሮ በባሰ ሁኔታ የደም ምድር ሆኗል፡፡ ከሰሞኑ በሁለት ወር ውስጥ ብቻ 170 ሺ የመተከል ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፡፡ አንድ ሺ በግፍ አካባቢዎች ተገድለዋል፡፡ 2 ሺ ያህል ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡
በስጋት የተለቀቁ ቤቶችን ኦነግ እየገባባቸው ነው፡፡ ኦነግ ያልገባባቸውን ደም ቀለም እየቀባ ይገኛል፡፡ ገጠሩ የመተከል ክፍል በኦነግ ቀለም አሸብርቋል፡፡ ከመተከል ለአሻራ የሚመጡ ምስሎች እንደሚያሳዮት፣ አብዛኛዎቹ የተፈናቃይ ቤቶች በኦነግ እየተያዙ ነው፡፡ ያልተያዙትም ቀለም እየተቀባባቸው ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን የቢሻንጉል ጉምዝ አመራሮች የሚሉት የለም፡፡
ከመተከል መፈናቀል ጀርባ ዋና ተዋናዮ ብልፅግናዊዉ ኦነግ እንደሆነ ከመተከል የሚሰሙ ድምፆች ለአሻራ በተደጋጋሚ እየደረሰ ነው፡፡
መተከል ዛሬ አልተረጋጋም፡፡ የተፈናቃይ ቤቶችም በኦነግ እየተያዙ፣ ያልተያዙትም በኦነግ ቀለም እያሸበረቁ ነው፡፡
ኦነግ አዲስ ጁንታ ሆኖ እያለ፣ ህዝቡ በአሮጌው ጁንታ ሁነት ላይ መጠመዱ የመተከልን ጉዳይ መፍትሄ አልባ አድርጎታል፡፡ በቢሻንጉል ያሉ አማፂዎች ከኦነግ ጋር ሆነው የነፃነት የሚሉትን አርማም እያውለበለቡ ነው፡፡ መከላከያው እስካሁን መሰረታዊ እርምጃ አልወሰደም፡፡ ከመተከል መፈናቀል አለ፡፡ መረጃው የደረሰን ከመተከል ነው፡፡ ከታች ያለው ምስል የኦነግ መምከርያ በድባጤ ወረዳ ነው፡፡ ኦነግ እንደ ፅህፈትቤትም ይጠቀምበታል፡፡ https://m.youtube. com/channel/ UCsfBw4xrhJzdMTzhWk_uX2A?sub_ confirmation=1