>

"በኢትዮጵያ ላይ ክፉ አትናገር፣ክፉ አትመኝ፣ክፉ አትስራ" ተራራ አንቀጠቀጥኩ" ብትልም ሰርጥ ውስጥ ተወሽቀህ ትገኛለህና!!! (ሔቨን ዮሐንስ)

“በኢትዮጵያ ላይ ክፉ አትናገር፣ክፉ አትመኝ፣ክፉ አትስራ” ተራራ አንቀጠቀጥኩ” ብትልም ሰርጥ ውስጥ ተወሽቀህ ትገኛለህና!!!
ሔቨን ዮሐንስ

* እኔ የምለው ምነው ሰዎቹ በስተርጅና እንደ ዝንጀሮ የገደል ሩጫ አሰኛቸውሳ…..  ?!?
ኢትዮጵያን ሲበሉ ሲግጡ የኖሩ ህውሃቶች በስተርጅና አልበላችው ብሎ ጥጋብ ሲተናነቃቸው የገጠማቸውን ውርደት አያድርስ ነው። የዘንድሮ የህውሃት ቅሌት ጉድ ነው! በእውነት ያ ሁሉ ድንፋታ ከሽሮ ድንፋታ ማነሱ አጅቦኛል። ስብሃት ነጋ ዝንጀሮ ገደል ውስጥ እንደ ዝንጀሮ ተወሽቆ መያዙን እና የሃየሎም ሚስት ክፉ ስራዋ ሲያስደነብራትና ስትሸሽ ስትሹለከለክ ገደል ገብታ መሞት አጅቦኛል።
ያ የውሸት አለቃ ስዩም መስፍንም መከበቡ እርግጥ ሆኗል። እኔ የምለው ምነው ገደል ለገደል ተርመጠመጡሳ? እጅ መስጠትም ወግ ነው፤ ራስን ማጥፋትም ክብር ነው!
ይሄን ውርደት ሳይ አባት አለም #መይሳው_ካሳ ዘርህ ይግዛኝ ስለ ክብር ማሞትን አስታምረኸናል ነው ያልኩት! የመይሳውን ፈለግ ተከትለው እነ ጀነራል ተሾመ ተሰማ ስለ አገርና ህዝብ ክብር ሲሉ ለጠላት እጅ አንሰጥም ብለው ራሳቸውን በምፅዋ ሰውተዋል።  ኮ/ል ዳመቀ እጅ አልሰጥም አንድ ጥይት እስክትቀረኝ እታኮሳለሁ በመጨረሻም አንዷን ለራሴ ብሎ ታግሏል። ጀነራል ሙሉዓለምም ደሜን ትጠጣለህ እንጂ እጅ አልሰጥህም ብሎ እስከ መጨረሻው ተዋግቷል። ነገሩ ቢከብደው ራሱን የሚሰዋበት አንድ ጥይት አስቀምጧል። አማራ አንድ ሽጉትና አንድ ክላሽ የሚኖረውን ሚስጥር አንዱ መታኮሻ አንዱ ራሱን ማጥፊያ ነው ሲባል እሰማም ነበር።
የሆነው ሆኖ እንዲህ ተዋርዶ እንደ ሳዳም ሁሴን እና ጋዳፊ ከመያዝና ገደል ገብቶ ከመሞት አንዲት የሽጉጥ ጥይት ጠጥቶ መሞት በስንት ጣሙ ድንግልን! ባለፈው አንድ ጋደኞየ ጋር ስናወራ እገሌ ራሱን ያጠፋል እላለሁ ጋደኞየም “ኖው አያጠፋም” ይላል ቀጠልኩና እገሊት ጀግና ትመስላለች ራሷን ታጠፋለች ስል “በጭራሽ አታጠፋም” ይላል። በመጨረሻም ጋደኞየ “ማወቅ ያለብሽ ነገር ከእነሱ ውስጥ ማንም ድፍረት ኖሮት ራሱን የሚያጠፋ አይኖርም። ለጠላት እጅ አልሰጥም እልህ አማራ ላይ ነው ያለው በታሪክም የምንሰማው።  ራስን ማጥፋት ከፍተኛ የሞራል እድገትና ጀግንነት ወኔ ይጠይቃል። ይህንን ታሪክ በእነሱ ታሪክ በጭራሽ ሆኖ አያቅምና አያደርጉትም ከፈለግሽ እንወራረድ”! አለኝ። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን የተረገሙ ሰዎችና ድርጅታቸውን አውግዞ ፋይሉን መዝጋት አለበት! ሁልጊዜም ማልቀሻውና ማስለቀሻው ሊያደርጋቸው አይገባም አለኝ።
ኢትዮጵያውያን ለምን ህውሃትን ያወግዛሉ? የምንል እንኖር ይሆን? ካልንም የሰዎች ማህበራዊነት ከሰበዓዊነትም ሆነ ከሕዝብነት ጋር በተፃራሪነትና በአመፅ በበለፀገ የመንግስት ስርዓታዊ /ድርጅታዊ/ ፍላጎት ስር የማቀቀና የተሸማቀቀ በመሆኑ፣ በማህበራዊ ህይወት በነፃነትና በእኩልነት፣ በመተሳሰብና በመረዳዳት ያልኖረ ያልዳበረ በመሆኑ፣ የህውሃት መንግስትና የመንግስታቸው ስንክሳር ሁሉ በሀብትና በስልጣን የአምባገነንነት ሱስ የተለከፈ በመሆኑ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ስለሚያውቁ እና የችግሩም ገፈት ቀማሽ ስለሆኑ ህውሃትን አብዝተው ይረግማሉ ይጠላሉ፣ ያወግዛሉ፡፡
የህውሃታውያን ድንቁርና የትውልድ ማነቆ ቢሆንም የቴክኖሎጂያዊ ጥበቦች መርቀቅ የእነሱን ድርጅታዊ ማይምነትን /አላዋቂነትን/ የማስፋፋት ፍላጎት አጎላ፡፡ ህውሃቶች ከቴክኖሎጂ ጋር ያልተግባቡ ከዘመኑ ጋር የሚዘምን ሃሳብ ያልነበራቸው ብቻ ግን በስድብ፣ በራስ ወዳድነት፣ በግትርነት እና ባረጀ ባፈጀ ሴራ ግደለው፣ ፍለጠው፣ ቁረጠው የተካኑ ብቻ ነበሩ። በዘመነ ህውሃት ሰው በሰውነቱ፣ ህዝብ በህዝብነቱ፣ አገር በአገርነቱ ያልታፈረበት፣ ያልተከበረበት፣ ያልተወደሰበት፣ ይልቁንም የተናቀበት፣ የተዋረደበት፣ የረከሰበት ሆነ፡፡ በውስብስቡ የህውሃት መንግስት ሴራ ውስጥ ሰዎች በራሳቸው ላይ የሚመሰክሩ የዋሆች ለመሆን በቁ፡፡ ታዲያ ይህንን አለማውገዝ ይቻላልን? ዛሬ ግን ነበሩ ለማለት በቅተናል።
ይህም የሆነው አማራው ተራራው ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ ደምና አጥንቱን ውድ ነፍስ ገብሮ ያመጣውም ድል መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል! ግፍ ቢደራረብብን፣ የግፍ ፅዋ ብንጎነጭም እነሱ ያደረጉትን ክፉ ስራ አንሰራም በግፍ አንውልም። የተመረጠ ቦታ ላይ የምንገኝ፤ የተመረጠውም የሚስማማን ንስሮች ነንና ከፍ ብለን እንበራለን!
በመጨረሻም ራ

ሳቸው ረክሰው አገርን አርክሰው እና አቅልለው የነበሩ ወንበደዎች፤ የአገራችን መከላከያ ሰራዊት ላይ ፍም እሳት ሲያወርዱ በለኮሱት እሳቱ ተቃጥለው ግብዓት መሬት እንዲገቡ #የአገራችን_መከላከያ_ሰራዊት አድርጎል። አገርና ህዝቡንም ታድጎል!
ክብር ለአማራ አርበኞች
ክብር ለአገራችን መከላከያ ሰራዊት
ክብር ለአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ
ባለተራዎችና ግብረ-በላዎቻቸው  ልብ እያላችሁ …. ነግበእኔ ማለት አይከፋም
አባዲ ዘሙ፣ ዶር ሰለሞን ኪዳኔ፣ ቅዱሳን ነጋ….
Filed in: Amharic