>

ከጅምላ ፍጅት የተረፉት አማሮች የሰቆቃ ድምጽ...!!! (አሻራ ሚድያ))

ከጅምላ ፍጅት የተረፉት አማሮች የሰቆቃ ድምጽ…!!!

አሻራ ሚድያ

 

*…. መሙዘን ቀበሌ አማራ፣አገው እና ሽናሻዎችን አርደው ስጋቸውን በሉት••
ከድባጤ ወደ ቻግኒ ይጓዙ የነበሩ 53 አማራ/አገው መካከል (4) ሰዎች ብቻ መትረፋቸው ይታወሳል።
•ስንጓዝበት የነበረውን መኪና ጉምዞች አስቆሙት ወዲያውኑ በያዙት ነገር ሁሉ ጨፈጨፉን ጨረስናቸው ብለው ሄዴ በአስከሬን ስር ተደብቀን አራት ሰዎች ብቻ ተረፍን።ልጄንም ገደሏት “ከጭፍጨፋው የተረፉ “
•ባለቤቴን በጥይት ከመቱት በኋላ አረዱት የሱቃ ድምፁን እየሰማን የልጆቼን አባት አጣሁት••
•መሙዘን ቀበሌ አማራ፣አገው እና ሽናሻዎችን አርደው ስጋቸውን በሉት••
 ከግድያው የተረፉት ጋር ቆይታ አድርገናል ሙሉ ቆይታችንን ከዩቲዩብ ቻናላችን ያግኙ
በተያያዘ ዜና
በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ (ኦሜድላ) ቀበሌ የታጠቁ የጉምዝ እና ኦነግ ጥምር ጦር (11) ንፁሃንን ገደሉ!!!
 ዛሬ ሌሊት ከ11:00 ሰዓት ጀምሮ በጉባ ወረዳ ኦሜድላ ቀበሌ የኦነግ እና ጉምዝ ጥምር ጦር በነዋሪዎች ላይ ከበባ በመፈፀም አስራ አንድ ( 11) ሰዎችን ሲገድሉ ከ(20) ሃያ በላይ የነዋሪዎችን ቤት አቃጥለዋል።
እነዚህ የጥፋት ሀይሎች እና ሌላ ተጨማሪ ሀይል በመጨመር  በሌሎች ቀበሌዋች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም ተጠቂዎች  ከቦታው ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል።
ቀጣይ የጥቃት ኢላማቸውም አልመሐል፣ቤጎን እና አብለሆንስ እንዳደረጉም የገለፁልን ሲሆን የአካባቢው ነዋሪ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
Filed in: Amharic